**ይድረስ ለቲክቶከኛ ትውልድ -*
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን እንዲህ ብለው ነበር።
***
” ቃል አይሞትም ይሏል እንጂ፥
እስትንፋስ ይሞታል ቅሉ
ቃሌ በፅንሱ በነነ፥
እፍ አልሺውና በሽሉ።”
ቃል ቃተተ ፲፱፻፶፮
ጸጋዬ ገብረ መድኅን
***

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን እንዲህ ብለው ነበር
” … አሜሪካ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን ብዙ ጊዜ ይፈጅባታል ፡፡ … እኛ ግን ጣይቱን ተከትለን ነው አድዋ የሄድነው፡፡… “
(10:10) ጸ.ገ.መ.
“ሰው ወደ ማርስ የሚሄደው መሬት ፍለጋ ነው፡፡ … መሬት በጣም ጠቧል። … ወልቃይት የመሬት ነገር ነው፡፡ ገና እሳት ሆኖ ይወጣል። … የቴዎድሮስ አገር ነው። … እንደዚህ ቀላል ነገር የለም። …”
(31:55) ጸ.ገ.መ.
“ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ጥሩ አርአያ አልሆነችላቸውም። ለኮለኒያሊዝም ጥሩ አርአያ አልሆነችላቸውም። ምኒሊክን አይወዱም። ቴዎድሮስን አይወዱም።… ና ውጣ ብሎ ጠርጎ ያስወጣ የለም። በጥቁር ዓለም ውስጥ በታሪካቸው የለም።”
(33:05) ጸ.ገ.መ.
” … ሕዝብ አውቋል። …ሕዝብ ቀድሞ መንግሥት ጭራ ሆኖ ኋላ ይጎትተዋል። … reverse ነው ሲትዌሽኑ … ብዙ ችግር አለ በኢትዮጵያ … ግን የዓለም ሕዝብ ያልተቸገረውን ተቸግረን አናውቅም። … ስለቻልነውም ነው የምንቸገር ይመስለኛል። … ላይችል አይሰጥም። እና ይችላል። ግን እኔ እንደሚያሸንፍ አልጠራጠርም።”
(50:57) ጸ.ገ.መ.
” … ጴጥሮስ … ወቅት የፈጠረው ሰው ማለት ነው። … ያ ዓይነት ሰው ለዛሬም መድኅኒት ነው። … በድንጋይ ሐውልት አስሮ ቁጭ ማለት ሌላ ጉዳይ ነው። … አንደበቱን ግን መድረክ ላይ አውጥቶ ማንቀሳቀስ መስማት የትውልዱ መብት ነው። … በተለይ ቤተ ክህነት በእንዲህ ዓይነት ጣር ውስጥ ባለችበት ጊዜ የፖለቲካ ካድሬዎች መጫወቻ ስትሆን እንደ ጴጥሮስ ዓይነቶቹ ናቸው ያባቴን ቤት የንግድ የቁማር ቤት አታድርጉ ብለው ጅራፋቸውን የሚያነሱት። … “
(53:50) ጸ.ገ.መ.
” … ኩሽ ነው ምድሩ። እሳት ነው አርማው። … ካም ሰላም ማለት ነው። … ካም ጥቁር ሆኖ ግን የውጭ ደም አለበት። እንደኛ ዓይነት ማለት ነው። … ኢትዮጵያዊ በሙሉ ጥቁር ሆኖ የውጭ ደም አለበት። … ኩሽ ጥቁር አፍሪካዊ አባት ነው መሠረቱ። ስለዚህ ከኩሽ ሥልጣኔ ተነስቶ ከሌላ ደም ጋር ፊዩዝድ የሆነው ካም ተደምሮበት ነው የግብፅ ሥልጣኔ ሰማይ የደረሰው። የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ የኑብያ ሥልጣኔ፣ የሜሮን ሥልጣኔ፣ … በመሠረት ምድሩ ላይ የነበረው የምድሩ ባለቤት ኩሽ ነው። … የሰው ዘር መጀመሪያ ሲፈጠር የተፈጠረበት ቦታ ያ ነው። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ አካባቢ። … አውሮፓውያን … ግንዳቸው እኛ መሆናችንን ፈልፍለው አግኝተው ያሳወቁን እነሱ ናቸው። … የዓለም ግንድ እኛ መሆናችንን…”
(56:20) ጸ.ገ.መ.
“… ሰው የተማረ ይግደለኝ ይላል። እኔ ወሎዬ ይግደለኝ እላለሁ ብዙ ጊዜ። … ወሎ እስላሙ ያርዳል። አንድ በግ አርዶ ያ በስመአብ ወልድ ይላል። ያ ቢስሚላኢ ይላል። … አንድ ቃል እኮ ነው። … ብሎ አንዱን በግ ቆርጠው … በሰላም አብረው … ይሄ ብስለት ነው። ርቀት ነው።…”
(1:05:05) ጸ.ገ.መ.
” …ኦሮሞ ነኝ ማለትህ አማራ አይደለሁም ማለት አይደለም። አማራ ነኝ ማለትህ ትግሬ አይደለሁም ማለት አይደለም። አማራ ሲል ሀም ሀራ አዲስ ሀም … ለምን አዲስ ጨመርክበት? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ተቀበልኩኝ ሀዲስ ኪዳንን … ሀም ነኝ ግን አዲስ ሀም ነኝ ። … አማራን አማራ የሚያደርገው አዲስ ካም መሆኑ ነው። ሀይማኖተ አበውን ክርስትናን መቀበሉ ነው።… ሦስተኛ በአማርኛ መናገሩ ነው። … “
(1:06:40) ጸ.ገ.መ.
” … ሬቮሊሽን ነው አማርኛን የፈጠረው። … ፊደሉ የግዕዝ ፊደል ነው። ከሳባውያን ነው የመጣው። ሳባውያን ደሞ የኢትዮጵያ ናቸው።… ሳውዲ አረቢያ ትላንትና ነው የወሰደው። …”
(1:09:55) ጸ.ገ.መ.
” … እኛ ማንነታችንን ማወቅ ያስፈልገናል። …ኦሮሞ የትግሬ ወንድም ፣ ትግሬ የአማራ ወንድም ፣ አማራ የጉራጌ ወንድም ፣ ጉራጌ የሶማሌ ወንድም ፣ … የኩሽ ልጅ – የካም ልጅ አንድ መሆኑን መጀመሪያ ማረጋገጥ … ችግር የሚፈጥሩት ጎሰኞች ጠባቦች ለሥልጣናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አፈር ድሜ ቢበላ ግድ የላቸውም። …”
(1:11:40) ጸ.ገ.መ.
“… አባቶቻችን አብሮ መኖር ስለሚያውቁ ነው የስምንት ሺህ ዓመት ሥልጣኔ ያቆዩን። … ስለዚህ ይኼ የኔ ዘር ካንተ ይበልጣል የሚል የሰይጣን ጨዋታ ቢቀር ይሻላል። … ማንም ከማንም አይበልጥም። … “
(1:25:55) ጸ.ገ.መ.
“… የጎሳ የበላይነት የባርነት አገዛዝ ነው። … የአንድ ጎሳ ፈላጭ ቆራጭነት ነው ባርነት። … አንተ አትበላም አንተ ከበላህ እኔ አፈር እበላለሁ ማለት ሰይጣናዊ ነው። የሰው አይደለም። አመራርም አይደለም። ጭለማ ነው።… “
(1:27:40) ጸ.ገ.መ.
“… ሆሞ ሳፒያን ሰው ቃላት መፍጠር የጀመረው በአንደበቱ አፍሪካ ውስጥ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። የመጀመሪያው ሰው። … “
(1:31:30) ጸ.ገ.መ.
” …የበላበትን እጅ መብላት መካድ መካካድ … ኢትዮጵያን የሚገል ይኼ ነው። አገር የሚያጠፋ። … ይዋሻል። ይቀጥፋል። ተንሰራፍቶ ቁጭ ብሎ አፉን እየው ተመልከተው ገፁን ቅጥፍ እያደረገ እግዚአብሔርን አይፈራም። …”
(1:40:45) ጸ.ገ.መ.
” … ዓለምን አታክቷል የእኛ አበሳ ። አበሳ ፋብሪኬት በማድረግ በጭራሽ የሚችለን ጠፋ። … “
(1:44:50) ጸ.ገ.መ.
” … የአሁን የጥቁር የአፍሪካ መሪ ጭንቅላቱ ሌላ ነው። ጭንቅላቱ ወይ የአረብ ነው። ወይ የአይሁድ ነው። ወይ ጣልያን ነው። አፍሪካዊ እኮ አይደለም። እና የእዚያኛውን ፍላጎት ነው እዚህ እሚያሟለበት ።… እና የሕዝቡ መከራ ነው የኾንነው ። … መሪ ማለት ገደል እሚያገባ ማለት አይደለም ። እኛ አገር ሕዝቡን ገደል ነው የምናገባው። ስለዚህ የሕዝቡን ፈቃድ ሙሉ። ትልቁ ፈተናችሁ ያ ነው። አንድ ሕዝብ ፈቃዱ ተሟልቶለት በሰላም ካደረ በቃ። … ሲከለክሉት ነው ጦር የሚነክሰው። ድንጋዩን ማሾል ይጀምራል።…”
(1:50:40) ጸ.ገ.መ.
” … እኔ ምን አደረገኝ የሱዳን ኩሽ? ለምን መጥቶ አዲስ አበባ ተንቀባሮ ብሩ ካለው … ምንድነው ችግሩ? ምንድነው ጣጣው? ወንድሜ እኮ ነው። …”
(1:52:16) ጸ.ገ.መ
” … ክርስቶስ ሄደ አይደለም እንዴ? ግብፅ መጣ አይደል? ግብፅ መጥቶ ተምሮ ሄደ። እየው ሕፃናት ያርዳሉ። ሥርዓት ነው ብለው። ሄሮዶስ የአይሁድ ንጉሥ እረድልኝ ሕፃናቱን አለ። ሕፃናት የሚያርድ ከልቸር ነው ያለው። ሸሸ። ይኼ ልጅ እናቱ እንዲታረድባት አልፈለገችም። የት ሸሸ? አውሮፓ ሸሸ? No they were barbarians … civilization የላቸውም። እዛ ቢሄድ ይገሉታል። የሠለጠነ ቦታ የት ልሂድ ሲል ጥቁር ግብፅ ነው የመጣው። … ሰላም አገኘ አይደለም? ተምሮ ተመለሰ። ሲመለስ አልተቻለም። … ሲመለስ የራሱን ካህናት ባንዴ ዜሮ አደረጋቸው በአሥራሁለት ዓመቱ ። መቅደሳችን እንዳትደርስ አሉት። መቅደስ ባባቴ አትነግዱ ብሎ በጅራፍ። … So he travelled independently … አይምሮ ያለው እዚህ ነው። … ያደገው ከጥቁር ጋር ነው። … They can’t stand his smartness. He is too much for them. They hanged him. These are barbarians. … ሥልጣኔ የሚሰጠው ኩሽ ነው። መጀመሪያ ሰው የተፈጠረው እዛ ነው። ጥበብ የተቀናጀው እዛ ነው። መርከብ የተሠራው እዛ ነው። … ብዙ ተዓምር ሠርተዋል። … እኛጋ … ይታያል። የቤተክህነቱ ሥርዓት ግልጥ ብሎ ይታያል። … ቁልቢ ሂድ ታየዋለህ ሥርዓታቸውን ። … የቅኔ ምሽት ሂድ።… ሼህ ሁሴን … ሌሊቱን ቁጭ ብለው ነው የሚያድሩት ሲቀኙ። ጭንቅላት የሚያዞር fantastic የሆነ ቅኔ ነው የሚቀኙት። …That is why the black mind still exists. … “
(1:52:35) ጸ.ገ.መ