>
5:14 pm - Wednesday April 30, 5873

አቶ ለማ መገርሳ -ገለቶማ ብለናል !! (ሀብታሙ አያሌው)

አቶ ለማ መገርሳ -ገለቶማ ብለናል !!
ሀብታሙ አያሌው
የሃሳብ ከፍታ እንዲህ ነው፤ ከዘረኝነት አዙሪት መውጣት የተሳናችሁ ጊዜው የኛ ነው ባይ የፖለቲካ ድኩማኖች ሆይ ከህመማችሁ መፈወስ ትፈልጉ እንደሁ  ይህው መድሃኒት…  “ዛሬ ኦሮሞ ቤተመንግስት የገባው ቤተመንግስቱን የኦሮሞ   አድርጎ ሊጨፍርበት ሳይሆን ቤቱን የሁሉም የኢትዩጵያ  ህዝቦች የፍትህ የእኩልነትና የሀቅ ቤት ለማድረግ ነው።
እኛ ይህን ቤተመንግስት የኛ ቤት አደረግን ብለን   የምንዘፍን ከሆነ ከሌሎች በምን ተሻልን ታድያ? እኛ ግን እንደዝህ አይደለንም። የታገልነው ለስልጣን ሳይሆን  ለፍትህ እና እኩልነት ለህዝቦች ነጻነት ነው።”
• ከሰማይ በታች እጅግ ይፈሩ የነበሩትን አስረን የህግ የበላይነትን አሳይተናል
• ወንበር ይዘን አልተቀመጥንም ።
• እንደ ግለሰብ ድርጅት ነበር ስርዓቱ የተገነባዉ።
• ስርዓት አፍርሶ አዲስ ለሁሉም የሚያገለግል ስርዓት መገንባት ጊዜ ይፈጃል።
• ከሰማይ በታች እጅግ ይፈሩ የነበሩ፤ እንኳን ለማናገር ቀና ብሎ ለማየት ይፈሩ •የነበሩ ሰዎችን አስረን ህግ ከማናችንም በላይ እንደሆነ አሳይተናል፡፡
“የታለ ለዉጡ? ይሉናል?/?? እኛ የታገልነዉ ለማን ፕሬዝዳንት ለማድረግ አብይን ጠ/ሚኒስትር ለማድረግ ነዉ ወይ? ይሉናል፡፡ ምን አረጋችሁ መቀመጫችሁን ይዛችሁ ቁጭ አላችሁ እንጂ ይሉናል??
መቀመጫ አልያዝንም!!!  አልተቀመጥንም፡፡ ችግሩ የስርዓት ችግር ነዉ!!! ስርዓቱን እንትና የሚባል ሰዉ ለራሱ እንዳመቸዉ እንደ የግል ድርጅቱ ነዉ ።  የገነባዉ፡፡ ገንብቶ እየተጠቀመበት የነበረ ስርዓት ነበር፡፡
ያንን ስርዓት ማፍረስን ይጠይቃል!!!   ይሄን ህዝብ፣ ብሄርና ብሄረሰቦችን በሚያገለግል መልኩ ለማቆም አፍርሶ መገንባትን ይጠይቃል፡፡ ለማፍረስ ጊዜ ይጠይቃል፤ ለመገንባትም ጊዜ ይጠይቃል፡፡
 የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ
Filed in: Amharic