የጣልያን መሸነፍ ለኦነግና ለሕወሃት ቁስል ሆኖ ወደ ሕዝቡ ተሸጋግሮ የኦሮሞናን የትግሬ የሚሆንበት አምክንዮአዊ ተጠየቅ አይገባኝም።
መምህር ፋንታሁን ዋቄ
ኃይሉ ጎንፋ የተባለው የአብይ አህመድ የዘር ማጥፋት ፕሮጄክት አስፈጻሚ በዚህ ቪድዮ የሚናገረውን እንስማ።↓
እነዚህ ሁለት ድርጅቶች የኦሮሞን እና የትግሬን ወጣት ፶ ዓመት ሙሉ አታለው፣ አእምሮ አጥበው በኢትዮጵያዊነት ላይ ያዘመቱት እና ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብሯ ለመመለስ ከአውሮፓ ከበባ ተሻምተው አገር ያቆዩልንን ምንልክን፣ ንጉሡን እና መኳንንቶቹ የተገኙበትን ማኅበረሰብ፣ ያነጸቻቸውን ኦርቶዶክሳዊት እምነትን በመዋጋት እጅግ እንቅልፍ ያጡት፣ አሁን ደግሞ ዘር የማጥፋት ተግባር ላይ የተጠመዱበትን የዘር ፖለቲካ አምላኪዎች መግታት አንገብጋቢ አጀንዳ ነው።
“ገድለውን ነበር” ብሎ በመተረክ ዛሬን የሚገድል፣ “እጅና ጡታችንን ቆርጠውን ነበር” ብሎ ዛሬን የሚከታትፍ፣ ወረውን ነበር ብሎ ዛሬን ፍጅትና ማፈናቀል የሚፈጽምን አረመኔ ማስቆም የሁሉም የጤናማ አእምሮ ባለቤቶች ግዴታ ነው
በቃ!!
ልብ በሉ ኦሮሞን ሁሉ ጠቅልሎና ወክሎ “ምን ልክ ቁስላችን ነው” ይላል። ይህ የእኔን ቅድመ እያለች እነ ራስ ጎበና ዳጬን በኦርቶክሳዊነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው በመወንጀል አዲሱን ኦሮ-ዑማ/ሙማ የጥቁር ናዚ ዘር የማጥፋት ሂደቱን ለማጠናከር ነው። እኔ ምን ልክ ቁስሌ ሳይሆን የዛሬ ከ5-6 መቶ ዓመታት በፉት ወገኖቼ የፈጸሙትን ድምሳሳሴና አገር ከግራኝ አህመድ ቀጥሎ በሥልጣኔ ሺ ዓመት የመለሰውን ታሪካዊ ቁስል ለመሻር ምክንያት የሰጠኝና የኢትዮጵያ ገናና የታሪክ ዥረት ውስጥ የጨመረኝ ነው።
የጀርመን ሙሽነሪዎችንና የዉሀብያን የተቀናጀ የጥላቻና የመለያየት የሐሰት ትርክቱን ወዲያ ጥለን የኤነጋውያን ኦሮ-ዑማ/ሙማነት እና የእኔ ኦሮሞነት እዚህ ላይ ይለያያል።
በተግባር የጥላቻ፣ የሐሰት፣ የስግብግብነት፣ ዘራፊኑት፣ ደም አፍሳሽነት፣ ነውረኝነት፣ የአረመኔነት መገለጫ የሆነው ፖለቲካ-ሠራሹ አሁን ሥልጣን ላይ ቂጥ ያለው ኦሮ-ዑማ/ሙማ የምን ልክ ዘመን የእነራስ ጎበናና ሌሌቹን ኢትዮጵያዊ፣ ኦርቶዴክሳዊ፣ ሰብአዊ፣ ጥበባዊ ኦሮሞነትን አይወክልም። እና መፍታት አለበት።
ምንሊክ ያዋረደው ቅኝ ገዥ ጣሊያንን ነበር። ይሁንና የባእድ መሣሪያ ኦነጋዊው ኦሮ-ዑማ/ሙማ ግን ‘’የጣልያን ቁስል የኦሮሞም ቁስል ነው ‘’ ይላል።
ይህም ብቻ አይደለም። ተላላኪነቱንና የባርነት ናፋቂነቱን ሲያስረግጥ ለተሸናፊው ወራሪ ጠበቃ ሆኖ እና አሸናፊውን ኢትዮጵያዊነትን በወቅቱ የመሩትን ንጉሥና አስተሳሰብ ጠልቶ ይንቀጠቀጣል።
ባርነት ቀረብኝ ብሎ ፶ ዓመት ሙሉ ከታሪክ መጋጨትና ደም ማፍሰስ የወያኔን ኦነግ የጋራ የጨለማ ቃል ኪዳን ይመስላል። ሻዕብያም የ፷ ዓመት ከኡትዮጵያ ተለይቶ በጣልያን ቅኝ ሥር የማቀቀበት የባርነት ዕድሜው ከ፫ሺ ዘመን ኢትዮጵያዊ ጸጋው በልጦበት ፴ ዓመታት ደም አፍስሶ “መለያየትን” ልክ ላኪዎች በቀለኛ ተሸናፊዎች አስተምህሮ መሠረት “ነጻነት” ብሎት ሕዝቡን ለሥቃይ ዳረገ።
ዛሬ ላይ ለምን መልካምና ክፉ ተግባር በአለፉት ትርክቶች ላይ ተመሥርተው ዛሬ ለሚፈጽመው ወንጀልና እልቂት ሕጋዊነት የሚሰጡ ሆነው ይቀርባሉ ስንል — በናዚ ጀርመንም አይሁድን ለማጥፋት ባለፈው ታሪክ ላይ የሐሰት ትርክት በመትከልና በመተካት ነበር።
ይህ ያለፈውን ታሪክ ለዛሬ ግፍ መፈጸሙያ ሕጋዊና ሞራላዊ ለማድረግ መሞከር አጸፋውን አለማሰብ ነው። ይህ ለሁሉም ወገን ይሠራል ከተባለ እና ልምድ ከሆነ የግራኝ አህመድን ውድመት ተኩትሎ ከመዳ ወላቡ እስከ ጎንደር ለ፺፪ ዓመት ዓመትት ሉባዎች እየተፈራረቁ በኦሮሞ መስፋፋት ያስከተሉትን የሰአዊና ለስልጣኔ ውድመት፣ እልቂት ቆጥሮ ሒሳብ ለማወራረድ የሚነሳ ሌላ የዘር ፖለቲካ ከተከሰተ ዕዳውን ማሰብ ይጨንቃል።
ኦሮ-ዑም/ሙማ ግን ኃላፊነት የማይሰማው ወንበዴ ስለሚመራው በ፳፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተ መንግሥትን በዘረኝነት ይዞ እንኳ ከ፭፻ ዘመናት አስቀድሞ “ኦሮሞ” የፈጸመውን እና በዚህ ዘመን ፍትህና ሞራል ሚዛን ታላቅ ነውር እንደ ክፉ ትምህርት መውሰድና ይቅርታ እንድንጠይቅ ያንኑ የሚደግመውን መንግሥት ለመሸፋፈን መሞከር መዘዙ ብዙ ይሆናል።
እንደዚህ ሴትና ሕፃን እያረዱ ” የማይታውቁ ሰዎች” በማለትና ፍትሕ በመንፈግ አይቀጥልም።
እንደዚህ እንደ ኃይሉ ግጎንፋ ያሉ ከፍተኛ የሐሰት ጫና ያደናበራቸው ደንቄሬዌች እና የስነልቦና መቃወስ ያጋጠማቸው ሰዎች የዘር ማጥፋት ፕሮጄክት ሽፋን ሰጭዎች በመሆናቸው በቃችሁ የሚባልበት ጊዜ ላይ ነን። በኦሮሞ ስም ግፍና ነውራችሁን ሕዝባዊ በማድረግ እልቂት አታስቀጥሉ ማለት የኦሮሞ ሕዝብ ግዴታ ነው።
አሁን በመላው ሀገሩቱ የሰው ደም እያፈሰሰ እና ትኩስ ደም ውስጥ ቆሞ ስላለፈው ለዚያውም በሐሰት ታሪክን በ፻፶ ዓመት ጎምደው ኦነግና ወያኔ በሤራ የፈጠሩትን ትርክት እንደ እውነትና መነሻ አድርጎ በንዴት ሲናገር ለሚሰማው የእርሱ ቢጤ ዕውቀትና እውነት ያለው ይመስላል። እርሱ በሚናገረው ሐሰት በአሁኑ ሰዓት ኦርቶዶክስውያን በኦሮምያ መንግሥት መዋቅርና ታጣቂዎች እየተጨፈጨፉ ነው።
ኃይሉ እና ኦነግ-ወለድ እፕእምሮዌች ስለሚያልቁት የሰው ልጆች እንዳነጋገር ስለ ስሙ ከቶሎሳ ወደ ኃይሉ ተቀይሮ ፊደል መቁጠርን ጉዳይ አጀንዳ ሊያደርግ ይጥራል።
ይህ ስሜታዊ አጀንዳዎችን ከሰው ልጅ ደኅንነት እና ክብር በላይ አድርጎ ማቅረብና እልቂትን ን ለተራዘመ ጊዜ ማስቀጠል የማንኛውም ዘር አጥፊ ቡድን ስልት ነው።
ወንጀላቸውን በተራና ርካሽ ጉዳይ ሥር ይደብቁታል። ይህን ለ፴፰ ዐመት ፈጽመዋል። የአብይ አህመድ ፓርላማ፣ ሲኖዴስ መጅልስና የምክክር ኮምሽን የመሳሰሉት ሁሉ የዚህ ሰውን በሌላ አጀንዳ የመተካት ድራማ አካል ናቸው።
ኦናጋውያን የሠሩት ኃይሉ የሞቱትን ጠቅሶ የቆሙትን የማጽዳት ፕሮጀክቱን በዚህ አይነት የድንቁርናና የአረመኔ አቀራረብ ለ፴፰ ዓመት ተደብቆ እንደፈጸመ ዛሬም ይህንኑ ይወቅጣል። አሁን ግን መገታት አለበት!!!
