>
5:00 pm - Wednesday November 30, 2022

የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት (ታማኝ በየነ)

የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት

ታማኝ በየነ

በ 1953 ዓ/ዓም ጄኔራል መንግስቱና ወንድማቸው ገርማሜ ነዋይ ከሌሎች ጋር በመሆን የቀዳማዊ ህይለስላሴን መንግስት በሃይል ለመገልበጥ የክብር ዘበኛን ጦር ይዘው ተንቀሳቀሱ ፡፡ እቴጌ ታመዋልና ወደ ቤተመንግስት ኑ በማለት ብዙዎቹን ባለሰልጣናት ከጠሩ በኋላ በግፍ ረሸኗቸው ፡፡ በሌላ በኩል ሌሎች የንጉሱ ታማኞች ደግሞ የምድር ጦርን ይዘው ተንቀሳቀሱ ፡፡ በሁለቱ መካከል ውጊያ ከተካሄደ በኋላ የአመጹ መሪ የነበሩት ጀኔራል መንግስቱ ነዋይ ቆስለው ተያዙ ፡፡ ጀኔራሉ ከተያዙ በኋላ ከነክብራቸው ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ተደርጎ እስኪያገግሙ ድረስ ተገቢው ህክምና ሲደረግላቸው ከሰነበቱ በኋላ ሲሻላቸው ፍርድ ቤት ቀርበው እስከመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ድረስ ተከራክረዋል ፡፡

የመጨረሻው ውሳኔ ትክክል ነበር አይደለም እያልን ልንከራከር እንችላለን ቢያንስ ግን ኋላ ቀር እያልን በምንተቸው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ዘመን አመጽ አካሂደው ብዙዎች እንዲሞቱና እንዲቆስሉ ያደረገው አመጽ መሪ የነበሩትና ቆስለው የተያዙት ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ ህክምናቸው ሳይጓደል ለፍርድቤት ቀርበዋል፡፡ያ ተግባር ከ57 አመት በፊት የነበረውን የኢትዮጵያዊያንን የሞራል ለዐልና ያሳያል፡፡ ዛሬ ከ57 አመት በኋላ ሻሼመኔ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ሳይ ግን ምን ያህል ወደኋላ እንደተጓዝን አመልካች ነው፡፡ማንም ይሁን ማን ወንጀል የፈጸመ በህግ ብቻ መዳኘት አለበት የህውሃትን ስርአት የምንቃወመው ያለህግ ስላሰረ ስለገደለና ህግን የራሱ መግደያ ስላደረገ ነው ፡፡ በየትኛውም የሃገራችን ክልል የሚፈጸም ድርጊት በህግ ብቻ መፈጸም አለበት ፡፡
የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት፡፡

የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት

ሰላም ለሁላችሁም የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበትበ 1953 ዓ/ዓም ጄኔራል መንግስቱና ወንድማቸው ገርማሜ ነዋይ ከሌሎች ጋር በመሆን የቀዳማዊ ህይለስላሴን መንግስት በሃይል ለመገልበጥ የክብር ዘበኛን ጦር ይዘው ተንቀሳቀሱ ፡፡ እቴጌ ታመዋልና ወደ ቤተመንግስት ኑ በማለት ብዙዎቹን ባለሰልጣናት ከጠሩ በኋላ በግፍ ረሸኗቸው ፡፡ በሌላ በኩል ሌሎች የንጉሱ ታማኞች ደግሞ የምድር ጦርን ይዘው ተንቀሳቀሱ ፡፡ በሁለቱ መካከል ውጊያ ከተካሄደ በኋላ የአመጹ መሪ የነበሩት ጀኔራል መንግስቱ ነዋይ ቆስለው ተያዙ ፡፡ጀኔራሉ ከተያዙ በኋላ ከነክብራቸው ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ተደርጎ እስኪያገግሙ ድረስ ተገቢው ህክምና ሲደረግላቸው ከሰነበቱ በኋላ ሲሻላቸው ፍርድ ቤት ቀርበው እስከመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ድረስ ተከራክረዋል ፡፡ የመጨረሻው ውሳኔ ትክክል ነበር አይደለም እያልን ልንከራከር እንችላለን ቢያንስ ግን ኋላ ቀር እያልን በምንተቸው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ዘመን አመጽ አካሂደው ብዙዎች እንዲሞቱና እንዲቆስሉ ያደረገው አመጽ መሪ የነበሩትና ቆስለው የተያዙት ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ ህክምናቸው ሳይጓደል ለፍርድቤት ቀርበዋል፡፡ያ ተግባር ከ57 አመት በፊት የነበረውን የኢትዮጵያዊያንን የሞራል ለዐልና ያሳያል፡፡ ዛሬ ከ57 አመት በኋላ ሻሼመኔ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ሳይ ግን ምን ያህል ወደኋላ እንደተጓዝን አመልካች ነው፡፡ማንም ይሁን ማን ወንጀል የፈጸመ በህግ ብቻ መዳኘት አለበት የህውሃትን ስርአት የምንቃወመው ያለህግ ስላሰረ ስለገደለና ህግን የራሱ መግደያ ስላደረገ ነው ፡፡ በየትኛውም የሃገራችን ክልል የሚፈጸም ድርጊት በህግ ብቻ መፈጸም አለበት ፡፡የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት

Posted by Tamagne Beyene on Sunday, August 12, 2018

Filed in: Amharic