>
5:13 pm - Thursday April 20, 9775

የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ (መንግስቱ አሰፋ)

የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ

መንግሥቱ አሰፋ 

የመንጋ ፖለቲካ እና የመንጋ ፍትሕ የትም ሃገር ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። ተከስቶም ያውቃል።  የዘርፉ ባለሙያዎች ዋነኛ ምክንያቱ “በተቋማት እና በመንግሥት የተቆጣ ሕዝብ፣ ከምሬት እና ከቁጭት የተነሳ ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ በሥሜት የሚወስደው በቀል አዘል “የፍትሕ ጥያቄ” ነው” ይሉታል።
በዚያ መልኩ ስንረዳው መፍትሔው ቀላል ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንጋ ፖለቲካውን እና የመንጋ ፍትሕን በዋነኛነት በሕዝብን ይሁኝታ (ለመልካም እሴት በመገዛት) እና የጸጥታ ኃይሉ በሚወስደው እርምጃ ብቻ ለመቆጣጠር ማሰባቸው ግን ሙሉ አይመስለኝም። 

ነፃነትል መሸከም አለመቻል አድርጎ መሳላቸውም አልተመቸኝም። ብዙ ትክክለኛ ጥያቄዎች “በመንጋው” ተነስተዋልና። ይልቁንስ ሕዝቡ በለውጡ ላይ ከፍተኛ ተስፋን በመጣሉ ዝቅተኛው ካድሬ እና የአስተዳደር አካል ሕዝቡ የሚፈልገውን ለማድረግ አለመቻሉ ነው። በዚህ ረገድም የፍትሕ ሥርዓቱ መሉ በሙሉ የፍትሕ ሥራን ሠርቶ ሕዝብን አገልግሏል ለማለት አያስደፍረም።

የመንጋ ፍትሕ ሌላ ምክንያቱ የዳሸቀ የፍትሕ አካላት ቅቡልነት እና ተዓማኒነት እንደሆነ ይገለፃል። (ሌላ ምክንያት ሊኖረው እንደሚችል ቢታወቅም)

ለረጅም አመታት የፖለቲካ ድርጅት ጠበቃ የነበረው የፍትሕ ዘርፉ አሁንም አንድም የተጠያቂነት አሠራርን ሳያሰፍን (ቢያንስ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ ሳይፈታ፣ የማጎሪያ ቤት አሰቃይ የነበሩ ባለሥልጣናት ላይ ምንም ምርምራ ሳያደርግ) እንዴት ቅቡል እና ተዓማኒ ይሆናል፤ ሕዝቡስ እንዴት “የኔ ፍትሕ ሰጪ” ብሎ ይወሰደው?

Securitization and appealing to unbridled and unprincipled “forgiveness” will be inadequate. Appropriately recognizeing popular demand and making more delivery accordingly is a necessity. 

በሌላ በኩል የመንጋ ፍትሕ ተጨባጭ ምንክያት ዝቅተኛው ካድሬ አለመታደሱ (“አለመደመር”) ነው። ሙሰኛ ዞን እየቀተቀየረለት መሾሙ ነው። ከፍተኛው የሙስና አባቶችም “አለመደመር” ነው። ….…መደመር ማለቴ መቀነስ።

በሌላ በኩል ግን ጥሩ መልዕክት ነው…ሁለት ነጥቦችን ልጨምር.
፩. የጥንት የመልካም እሴቶች እና ሥነ መንግሥት እንደነበሩን ገልጸው ነበር። እጅግ በጣም ጥሩ ነው። ግን እነዚህ እሴቶች እና ሃገር በቀል የሆኑ የመንግሥት ሥርዓቶችን አንኮታኩተው ያደከሙት እና አንዴ ፊውዳል ሌላ ጊዜ ኮሚዩኒኒዝም፣ ሶሻሊዝም እና ካፒታሊዝም (ዴሞክራቲክ ዴቬሎፕመንታል ስቴት LOL) እያሉ ሀገሩን ወደ “STATE” ማሳደግ እንኳን ያቃታቸው ይዚሁ ሃገር ፖለቲከኞች ናቸው (ኢሕአዴግን ጨምሮ)።
፪. “አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚንማኅበረሰብን መፍጠር” ያሉትን ሰማሁት። ይህ ሐረግ በሕገ መንግሥቱ መቅድም ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የቡድን እና የግል መብት ተከብረውላቸው፣ የጋራ ጥቅም ተከብረውላቸው፣ ሠላም እና ዴሞክራሲ የሠፈነበት ሀገርን በጋራ መመሥረትን እንዲህ ብሎ ይገልፃል
” .….መጪው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል…. 
የሕገ መንግሥት ባለሙያ ስላልሆንኩ ብዙም አስተያየት ባልችልም ግን ባለፉት 27 ዓመታት በዚህ ረገድ ምንል እንዳልተሠራ ለመናገር አሁን ያለንበት እርስበርስ ያለን ጥላቻ፣ መነቋቆር፣ መገዳደል ማየቱ በቂ ነው።

ምን ለማለት ፈልጌ ነው?

አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ”…ወይም በቀላሉ STATE ለመገንባት ብዙ ርቀት ይቀረናል…የጠቅላይ ሚኒስትሩም ትልቅ ፈተና እንደሚሆን አስባለሁ። 

Tactical Alliances (ካለ LOL)  ወደ strategic integration ይደጉ፤ እንትግሬሽንም አቃፊ ይሁን፣ ኢኮኖሚው ይነቃቃ፣ የሥራ ዕድል ይፈጠር፣ ያኔ መንጋ በሥራ ይጠመዳል (የፌስቡክ መንጋንም ጨምሮ)።
ግን ግን ቆይ የሕዝባዊ አመጹ ዋነኛ ጥያቄ ምን ነበር?

(እኔ ራሴው እንዳልረሳው ለማስታወስ ያህል ነው እንጅ እርስዎ “ጊዜ” ብለዋል)።

ከምንም በላይ ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ  ኢሕአዴግን ማስተዳደር፣ መለወጥ ይቅናዎት። ካልሆነም እሱ ግትር ሆኖ አልቃና ብሎ ሲሰበር ኢትዮጵያን አደራ

 

Filed in: Amharic