>
6:18 am - Wednesday December 7, 2022

ካምፕ አቋቁሞ ኦሮሞንና አማራን እያጠቃ ያለው ሀይል  መስተናገድ ያለበት  እንደ ሽምቅ  ተዋጊ ነው!!!  (ቬሮኒካ መላከ)

ካምፕ አቋቁሞ ኦሮሞንና አማራን እያጠቃ ያለው ሀይል  መስተናገድ ያለበት  እንደ ሽምቅ  ተዋጊ ነው!!! 
ቬሮኒካ መላከ
ውድ ኢትዮጵያውያን:-
ሰሜን ጎንደር ጭልጋ አካባቢ መሽጎና ወታደራዊ ካምፕ  መስርቶ  አማራን  እያጠቃ ያለውና ቤንሻንጉል ጫካ ካምፕ አቋቁሞ ኦሮሞን እያጠቃ ያለው ሀይል  መስተናገድ ያለበት  እንደ ሽምቅ  ተዋጊ ነው እንጅ እንደ መብት ጠያቂ አይደለም።
Rule of Engagementቱና የጨዋታው ህግ እንደዚያ ነው። ሁለቱም ሀይሎች ከመቀሌ በሚሰጣቸው ወታደራዊ ትእዛዝና መሳሪያ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ናቸው።
እነዚህ ሀይሎች የዘመን ቅዝምዝም  አጠናግሮ ከጣለው ህውሃት ጋር ገደል ውስጥ ለመግባት እየተጣደፉ ያሉ ሀይሎች ናቸው። አለን የሚሉትን የመብት ጥያቄ በውይይትና በሰላም ከማቅረብ ይልቅ ፈረንጆቹ Not the word but the sword እንደሚሉት በከሸፈ የህውሃት ጥይት ጨዋታውን ጀምረውታል።
ቅማንትን በተመለከተ ከዚህ በኋላ የቅማንት ጥያቄ በቀይ እስኪብርቶ ሰርዘነዋል። መንግስት ባለበት አገር ውስጥ ሶስት ወረዳን የጦር ካምፕ ካደረገ ወንበደ ጋር የምንደራደርበት አግባብ ፈፅሞ አይኖርም።
 ከዚህ በተጨማሪም ህውሃት  ግጭትን በመቆስቆስ በሰይጣን  የቆረበ  ስለሆነ በሰሜን በኩል መፈንዳት ያለባት ብጉንጅ ካልፈነዳች ፌደራል መንግስቱን ከዛች ክልል ጋር ያለው የቨርቲካልና ሆሪዞንታል ግንኙነት አክትሞለታል እንዳይባል ህውሃትን የማንበርከክ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።
Filed in: Amharic