>
4:23 pm - Sunday August 7, 2022

ምድራዊ ግሀነብ!!!  (አቶ ገብረመድህን አርአያ) 

ምድራዊ ግሀነብ!!!
  አቶ ገብረመድህን አርአያ 
ግሀነብ… የሚባል ከመሬት በታች ሁለት መቶ እስር ቤት አለ።ይህ ቦታ ከሰሜን ጎንደር ከወልቃይት፣ጠለምት፣ጠገዴ አማሮች ይያዙ እና እዚህ ጨለማ ቤት ይታሰራሉ።እስር ቤቶቹ ውስጥ መታሰር ብቻ ሳይሆን እስረኛ የሰሜን ጎንደር ሴቶች ከሆኑ እሳት ተቃጥሎ በማህፀናቸው ውስጥ ይቃጠላሉ፣ወንዶችን ደግሞ በሆዳቸው እሳት ይለቀቅባቸዋል።በዚህ እስር ቤት ከ40 ሺህ በላይ እስረኞች አሉ።
የሚያሳዝነው እስር ቤቶቹ ውስጥ የታሰሩ ሰዎች ከመገደላቸው በፊት የራሳቸውን መቃብር እንዲቆፍሩ ይደረገል። ከዛ ይረሸኑ እና ድንጋይ እና አፈር ሌሎች ተረኛ እስረኞች እንዲያለብሱዋቸው ይደረጋል።
ባጠቃላይ ባዶ ስድስት አሁንም ተቃዋሚዎችን፣ጋዜጠኞችን፣አርሶ አደሮችን የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች እዚህ ውስጥ ነው ስቃይ ሲቀበሉ እየተቀበሉ ያሉት።
እኔ እስከ 1990 ዓ.ም. ድረስ እዚህ ቦታ ላይ ይህ እንደሚፈፀም በእርግጠኝነት አይቻለሁ።  እኔ ራሴ የዓይን ምስክር ነኝ።  የእስር ቤቱ አዛዥ ደግሞ ብስራት አማረ ይባላል።
ወልቃይት ጠገዴ የሰሜን ጎንደር ቦታ ነው
 ወልቃይትን ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ቋራ የትግራይ ናቸው ብሎ ነው በረሃም የገባው።
ይህ ሀሰት ነው ምንም የታሪክ መሰረት ማስረጃ የሚሆን የለውም። ህውሃት እነዚህን ቦታዎች የራሱ ለማድረግም ግድያ፣እስር እና እንዳይወልዱ ሲደረግ አይቻለሁ።እኔ ይህን አውቃለሁ አረጋግጣለሁ።
ፍየል ውሃ 1973
ግህነብ በ1972 ዓመተ ምህረት የተሰሩ አሰቃቂ እስር ቤቶች ናቸው ።  እነዙህ እስር እና ስቃይ ቤቶች ምን ያክል አስተማማኝ ናቸው እዩ ተብለን ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሬ ሄጄ እኔ ራሴ አይቻቸዋለሁ።
 ወልቃይቶች ፣ጠለምቶች፣ጠገዴ የአማራ ነው ስለ ማንነታቸው የሚያነሱት ጥያቄ ትክክል ነው።ከተከዜ ወዲያ ትግራይ ከተከዜ ወዲህ ጎንደሬ አማራ ነው።
Filed in: Amharic