>
4:47 pm - Tuesday July 5, 2022

በሚስጥር ተደብቆ የቆየው የመለስ ኑዛዜ  ከዓመታት በሗላ ተጋለጠ!!! (መሰረት መኮንን)

በሚስጥር ተደብቆ የቆየው የመለስ ኑዛዜ  ከዓመታት በሗላ ተጋለጠ!!!
መሰረት መኮንን
የመለስ ራዕይ የተባለው የሀገሪቱ የኢህአዴግ መመሪያ ሆኖ ለ5 ዓመታት ያለው መመሪያ /ዶክትሪን/ ለካ የመለስ ዜናዊ ኑዛዜ ነው፡፡
በሪስሌስ ሆስፒታል ህክምና ላይ እያለ የተደረገ የመለስ ዜናዊ ኑዛዜ፡- ኑዛዜውን የሰጠው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ እያለ አለመትረፉን ሲያረጋግጥ ሊሞት 18 ቀናት ብቻ ሲቀረው ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በህይወት እያለ ያቀደውን ሲሞትም እንዲቀጥል በሚል የሰጠው ኑዛዜ ከ ዓመታት በሗላ ይፋ ሆኗል፡፡ ኑዛዜውን ቀርቦ በወቅቱ የተቀበለው አቶ ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ ነው፡፡
ኑዛዜው ስምንት ዋና ርዕሰ ያለውና በስሩ ደግሞ በርካታ ንዑስ ክፈል ያለው ነው፡፡ አቶ ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ ኑዛዜውን ፅፎ ከተረከበ በሗላ እንዲያስረክብ የታዘዘው የአድዋ ልጆች ለሆኑ እና “ንግስት ሳባ” በሚል ማህበር ለተደራጁት ነው፡፡ እነዚህ የአድዋ ልጆች የመለስን ኑዛዜ ፈፃሚና አስፈፃሚ ሲሆኑ በማንኛውም መንገድ ለተፈፃሚነት ተግተው የሚሰሩ ናቸው እነሱም:-
1. ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
2. አቶ ስብሃት ነጋ
3. አቶ እርከበ እቁባይ
4. አቶ አባይ ፅሐዬ
5. አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ
6. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ነጋ
7. አቶ ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ  ናቸው፡፡
ስምንቱ ኑዛዜዎች
1. የአድዋ ትግራይ የበላይነትን ማስፈን
2.  በራስ ሰዎች መታጠር
ሀ. የአድዋ ተወላጆችን በከፍተኛ ስልጣን እርከን ላይ ማስቀመጥ ፣ ከእነሱ ወጪ የሆኑ ሹሞችን ግን ከጀርባቸው ሆነው መቆጣጠር
3. ስትራቴጂ መንደፍ ፣
ሀ/ በመከላከል በማንኛውም ጦር ክፍል አዛዥ ጀነራሎች፣ በፖሊስ እና በደህንነት ውስጥ የበላይ ባለስልጣን
ለ/ በውጭ ጉዳይ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ
ሐ/ በአጠቃላይ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ኑሮ ለመምራት ብቃት ያለው ደ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ስለሆነ እሱ በማንኛውም ሚኒስትር መ/ቤትና በማንኛውም ተቋማት ከጀርባ ሆኖ እንዲመራ
4. በሽፋን መጠቀም….
ሀ/ ጠቅላይ ሚ/ር ኃ/ማርያም ሲምቦል በማድረግ ደብረፅዮን ያዘዘውን ብቻ እንዲሰራ ማድረግ
5ሀ/ ብሔርን ከብሔረ ጋር ማጋጨት፣ ብሔርን ብቻ ሳይሆን አንዱን ብሔርም በመከፋፈል እርስበርስ እንዳይግባቡ ለማድረግ በጥቅም መለያየት 
ለ/ በተለይ አማራው ትምክህተኛ የድሮውን ስርዓት ናፋቂ ብሎ በአደባባይ መውቀስና መዝለፍ
ሐ/ አማራው ከውጭ ጠላት የበለጠ ጠላት ስለሆነ በማንኛውም መንገድ ማዳከም
መ/ በኢኮኖሚ እንዲዳከምና የትግራይ ጥገኛ ሆኖ የትግራይን ኃያልነት አምኖ እንዲቀበል መድረግ
ሠ/ በተለይ የአማራውን ምሁር ማሳደድና ሞራሉ እንዲወድቅ ማድረግና ፣ ሀገር ጥሎ እንዲሰደድ ማድረግ ትልቁ ስራችሁ ይሁን፣
ረ/ ትግራይን ለሪፈረንደም ማዘጋጀት፣ በኢኮኖሚ ማሳደግ፣ በእርሻው አዲስ በተቀየሰው ክልል መሰረት ግብርናን በቤንሻንጉልና በጋምቤላ ማስፋፋት
ሰ/ ኢንዱስትሪውን በትግራይ ብቻ እንዲስፋፋ ማድረግ
ሸ/ ታላቋን ትግራይን ለመመስረት ምዕራብ ጎንደርን ፣ ቤንሻንጉልንና ጋምቤላን የአባይ ግድብን ጭምር እንዲካተት ማድረግ
ቀ/ ይህንን ማፕ/ካርታ ዓለም አውቆ እንዲቀበለው ማድረግ
በ/ ከአጎራባች ክልሎች የተወሰዱ ቦታዎች ላይ የሰፈሩ ኑዋሪዎችን የትግራይ መታወቂያ በግድ እንዲወስዱ ማድረግ ፣ አንወስድም ካሉ ማዋከብ፣ ማስጨነቅ ፣በኢኮኖሚ እንዲወድቁ ማድረግ ማሰር፣ በጣም የሚያስቸግሩ ካሉመግደል፡፡
ተ/ በአካባቢው ያሉ የሀገር ተቆርቋሪዎች ፣ ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎችና ለህዝብ አሳቢዎችን ማጥፋት
6.ሀ/ ከሱዳን ጋር ደንበርተኛ ለመሆን ሱዳን የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ 
ለ/ የትግራይና ሱዳን ደንበርተኝነት በዓለም ህብረተሰብ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ
ሐ/ የዓለም ኃያላን  ህ/ሰብ በትግራይ ካርታ እውቅና እንዲሰጥ ለእነሱ መታዘዝ፣ ለምሳሌ ወታደር ማዝመት፣ መሬት መስጠት (ለደቡብ ሱዳንና ለሶማሊያ )
መ/ በባንዴራው ላይ ያለውን የኢሉሚናት ማለትም የግብረሰዶም ምልክት የሆነውን በባንዴራ ላይ አርማ እንዲሆን ማድረግ
7.ሀ/  የአድዋ ተወላጅ የሆኑትንና የሳባ ማህበር አባል ፣ የስርዓቱ ታማኝ አድርጎ በትምህርትና በሙያ ማሰልጠን
ለ/ አሰልጥኖ ወደ መሀል ሀገርና ወደ ተለያዩ ክልሎች በመላክ በተለይ በደህንነት ስራዎች ላይ ማሰማራት
ሐ/ ውትድርናም የሌላውን ብሔርሰብ ከመቅጠር ይልቅየትግራይ ወጣቶችን ብቻ በብቃት አሰልጥኖ በየክልሉ ተልዕኮ እየሰጡ ማሰማራት
መ/ የሳባ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት አድዋ ሲሆን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ ቦሌ የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ ሌፍ ሃውስ በሚል የሚታወቀው መ/ቤት የመንግሥቱ አመራሮች የሚቀረፁበት ሲሆን፣ በዚህ መስሪያ ቤት የተነደፉ የአስተዳደር ፣ የአሰራርና የአተገባበር እቅዶች በሙሉ ተቀርፀው ወደ ታች የሚፈሱ ናቸው፡፡
ሠ/ ጠ/ር ሚ/ር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለፊርማ ብቻ የሚጠራ ሲሆን የሚፈርምበትን ወረቀት የማንበብ ስልጣን እንዳይኖረው አድርጎ መቅረፅ ፣የስብሰባቸው ሰዓት ከቀኑ12 ሰዓት እስከ ምሸቱ 1 ሰዓት ሲሆን ከዚያ በሗላ በአካካባቢው ሰው ዝር የሚል አይኖርም ፣ የሚጠበቀው በስናይፐርና በዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪያ ይሆናል፡፡
8 ሀ/ ኦሮሞ ጠባቦች ናቸው፡፡ ቢሆንም እንደ አማራው አስቸጋሪ አይደሉም፡፡ ቢሆንም እነሱም ቢሆን አይታመኑም በተለይ ከአማራው ጋር ለማጣላት በርትታችሁ ስሩ፡፡
ለ/ አማራና ኦሮሞ አንድ የሆኑ ቀን የትግራይ ጉዳይ ያልቅለታል፡፡ ስለዚህ የማጋጨትናየማጣላት ስራችሁን ከማንኛውም ስራ በፊት ቅድሚያ ስጡ፡፡
ሐ/ የትግራይ ማንነት የሚመሰረተው በጎንደር መሬት ነው፡፡ የአማራው ከፍተኛ ኃይል ደግሞ ጎንደር ስለሆነ ጎንደርን በመከፋፈል እንዲዳከም ማድረግ
 መ/ የጎንደር መከፋፈያ መንገድ ዋናው በውስጡ የተለያዩ ብሔሮች ስላሉ እነሱን የራሳቸውን ክልል እንዲመሰርቱ የብሔር ጭቆና አለብን በማለት ሪፈረንደም እንዲጠይቁ ማነሳሳት እናንተም ያንን ጥያቄ በመደገፍ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካና የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ እንዲነሳሱ መገፋፋት
ሠ/ አሁን የተደራጀው የቅማንት ማንነት ጥሩ ጅምር ስለሆነ ሌልችም እነሽናሻ የመሳሰሉትን መቀስቀስ እና እርስበርስ እንዲፋጁ ማድረግ
ረ/ ሌላው ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደርና ምዕራብ ጎንደር በማለት ከፋፍሎ አንዱን ማገዝና በሌላው ላይ እንዲዘምት ማድረግ
ሰ/ ትልቁ ስራ ደግሜ ደጋግሜ አደራ የምለው አማራው ከኦሮሞው ጋር እንዳይስማሙ ጥረት ማድረግን ነው፡፡
ሸ/  ኦሮሞውን በትምህርት ደካማ ማድረግ፣ በተለይ ከአማራው ጋር እንዳይግባቡ ማድረጊያው ትልቁ መሳሪያ የኦሮሞ ልጆች አማርኛ እንዳይናገሩና ብሔራዊ ቋንቋ እንዳያውቁ ማድረግ
ቀ/ ትግራይ በሪፈረንደም ራሷን እስከምትችል አገር የሚወጣውን ኦሮሞ እግሩን መቁረጥ ፣ በኢኮኖሚ ማዳከምና ኦሮሞ ከሌላው ብሔር ጋር እንዳይግባባ ማድረግ
በ/ ኦሮሞን ከአጎራባች ክልሎች ጋር በግጦሽ መሬትና በውኃ እንዲጣሉ ማድረግ
ተ/ በየጊዜው ኦሮሞ ሊገነጠል ነው በማለት ማስወራት፣ ኦህዴድን እንዲገነጠል አድርጎ ከትግራይ ጋር ሪፈረንደም እንዲጠይቅ ማድረግ፣ ከዚያም አማራው ስለማያስችለው የራሱን ሪፈረንደም እንዲጠይቅ ማድረግ
ቸ/ ቀጥሎ ቤንሻንጉልና ጋምቤላ ሪፈረንደም እንዲጠይቁና ከትግራይ ጋር እንዲሰሩ ማድረግ
ኀ/ ደቡብ ብሔረሰቦች አብረው እንዲገነጠሉ ማግባባትና ግፊት ማድረግ፣ በዚህ ጊዜ ሀገሪቱ እንድትበታተን ፣ የትግራይ የበላይነት ሰፍኖ ትግራይ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጣ በመቃብር ውስጥ ሁኜ አያታለሁ።
—-
እንግዲህ ያ ሊቀ ሰይጣን ይህን በእነርሱ አገላለጽ “ራእይ” በእኛ እሳቤ ክፉ ቅዥት  ተናዝዞ አልፏል
የኑዛዜውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ እስካሁን በሀገሪቱ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ከኑዛዜው ጋር እያመሳከሩ ማየት ብቻበቂ ነው፡፡ ምክንያቱም የኑዛዜውን ቃል ማንም ሳይሸራርፍ እየተተገበረ ይገኛል ፡፡ የኑዛዜውን እውነተኛነት አመሳክሮ ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ጉድህን ሰማህ ፣ ታሪክህን አወክህ ፣ አሁንስ አይበቃም? የኑዛዜውን ተግባራዊነት ትጠብቃለህ ወይስ ሀገርህን ለማዳን ተባብረህ ትሰራለህ? እንደ ክረምት ፀሐይ ብልጭ ድርግም እያልክ ለገዳዮችህ አትመች፡፡ ለውጤት በየተራ መነሳት ሳይሆን ሁላችንም በአንድ ጊዜ መነሳት ይበጃል ፡፡ የተባበረ ክንድ አሸናፊ ነው፡፡ ተባብረን የሰይጣንን ስራ እናጥፋ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ ፡፡ ለፋኖና ለቄሮ ኃይል፣ ብርታቱንና አንድነትን ይስጠን፡፡ ወጣቶች ሆይ!የኢትዮጵያ ህዝብ በእናንተ ተስፋ አለውና በርቱ!!ኃይሉ የአምላክ እሱ ይደግፋችሁ ፡፡ አሜን!!!!!!!!!!
Filed in: Amharic