>
10:12 am - Sunday January 29, 2023

ኣብርሃ ደስታ ያልታወቀ ስፍራ ተደብድቦ ተወስዶኣል

Abrha Desta 3ኣብርሃ ደስታ የኣረና ፓርቲ ስራ ኣስፈጻሚ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነውና በተለይም በማህበራዊ ድረ-ገጾች (ትዊተርና ፌስ ቡክ) የስርዓቱን መበስበስ በተጨማጭ መረጃ በማጋለጥ የሚታወቀው በዛሬው ዕለት በታጣቂዎች እየተደበደበ ወደኣልታወቀ ስፍራ መወሰዱን በኣካባቢው የነበሩ ሰዎች ለኣረና ጽህፈት ቤት እንደገለጹላቸው ከፓርቲው ኣባላቶች ለማወቅ ችለናል።

የኣረና ፓርቲ ኣባላቶች የኣብርሃ ደስታን ሁኔታና በየት እስር ቤት እንደሚገኝ ለማወቅ ያደረጉት ሙክራ እስካሁን ኣልተሳካላቸውም። ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እናቀርባለን።

Filed in: Amharic