>
6:24 am - Tuesday July 5, 2022

ሌላኛው ታከለ ኡማ በንግድ ባንክ!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ሌላኛው ታከለ ኡማ በንግድ ባንክ!!!

ጌታቸው ሽፈራው

* የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ወደ ኦሮምያ ባንክ የማሸጋገሩ ሂደት እየተሳለጠ ነው !!!

ጠ/ሚ ዐቢይ በቃሉ የተባለን ሰው አንስቶ የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ምክትል ፕሬዝደንት የነበረውን አቶ ባጫ ጊኒን የንግድ ባንክ ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ይህ ሰው እንደተሾመ ያደረገው የኦሮሞ ባለሀብቶች ሌላ ባንክ ላይ የተበደሩትን ብድር  መግዛት ነው። የሌሎች ባንኮች የብድር ወለድ ጣሪያ እስከ 18 በመቶ ይደርሳል። የንግድ ባንክ ደግሞ 11 ነጥብ 5 ነው። 18 % የብድር እርከን ካለው ባንክ ለንግድ ባንክ ብድር የተገዛለት ባለሀብት ከ7% በላይ ብድር ቀነሰለት ማለት ነው።  ይህ አንዱ ማሳያ ነው።

ንግድ ባንክ ላይ በሁለት ሶስት ወራት እየተሰራ ያለውን ነገር የሚገልፀው አፓርታይድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሊባል አይችልም።  ጠ/ሚ ዐቢይ ባጫን ከሾመ በኋላ ንግድ ባንክ ላይ እየተሰራ ያለው ጉዳይ ቢጣራ ሕወሓት ሲሰራው ከኖረው ቢብስ እንጅ የሚያንስ አይደለም።

ታከለ ኡማ መታወቂያ ሲያድል፣ የከተማዋን የሕዝብ ስብጥር ለመቀየር ቀና ደፋ ሲል ሌላኛው ታከለ ደግሞ የባንክ ስርዓቱ ለመቀየር እየሰራ ነው።  ዛሬ 7 ምክትል ፕሬዝደንቶች በባጫ ምክንያት መልቀቃቸው ታውቋል።

ከንግድ ባንክ የማፅዳት ዘመቻ ሰለባ የሆኑ ምክትል ፕሬዝደንቶች !

ጠ/ሚ ዐቢያ ባጫ ጊኒ የሚባል ሰውን የንግድ ባንክ ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ይህ ሰው ፀሐፊውን ጨምሮ ብዙ አመራሮችን ድሮ ይሰራበት ከነበረው የኦሮሚያ ባንክ ነው ይዞ የመጣው። ይህ ሰው በሚከተለው ዘረኝነት እና ግልጽ መድልዎ ምክንያት ከአንድ ሰው በቀር ቀሪዎቹ ምክትል ፕሬዝደንቶች በፈቃዳቸው ከስራ ለቅቀዋል!! በፕሬዝደንቱ ምክንያት ከስራቸው ከለቀቁት ምክትል ፕሬዝደንቶች መካከል:_

1) አቶ ዓባይ መሃሪ የብድር አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት፣

2) አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ የደንበኞች ሒሳብ አካውንትና ትራንዝአክሽን ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት፣

3) አቶ ሰይፉ ቦጋለ የሰው ኃይል አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳነት፣

4)አቶ አትክልት ኪዳነ ማርያም የፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት፣

5)ወ/ሮ መሠረት አስፋው የፋሲሊቲዎች አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት፣

6) አቶ ወንድአለ በላቸው የብድር ግምገማና የፕሮቶኮል ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት  ይገኙበታል፡፡

ከምክትል ፕሬዝደንቶች መካከል ከስራ ያልለቀቁት ወ/ሮ ሚልኪያ በድሪ ብቻ መሆናቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ንግድ ባንክ ላይ እየተሰራበት ያለው አፓርታይድ አዲስ አበባ ውስጥ በገፍ ከሚታደለው መታወቂያ የከፋ ነው።

Filed in: Amharic