በ አሸናፊ በሪሁን
የመንን እና ሶማሊያ የሚለየው የኤደን ባህረ ሰላጤ የአለማችን ትልቁ የባህር ላይ የንግድ መስመር ነው፡፡ በእስያ እና የ አውሮፓ ሀገራት ትልቁ የንግድ መገናኛም ይህ መስመር ነው፡፡ ይህ የንግድ መገናኛ መስመር ታዲያ ህገ ወጥ ሰው አዋዘዋሪዎች ስደተኞችን ውደ አረብ ሃ እና ወደ አውሮፓ ሀገራት ለማሻገር የሚጠቀሙበት ዋነኛ መስመር ነው፡፡ ክፋቱ ታዲያ ከዚህ ትልቅ ኤደን የባህረ ሰላጤ አካባቢ የሚወጡ ዜናዎች ግሁሌም ሞትን የሚያበስሩ መሆናቸው ነው ፡፡ ከሞች ስደተኞች መካከል ደግሞ በርካታውን ቁጥር የሚይዙት የእኛው ዜጎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የበለጠ ሀዘንን ያጭራል፣ አንገትንም ያስደፋል፡፡ ከዚህ በፊት በነሀሴ 2009 ዓ.ም በየመን አድርገው ወደ ሌሎች አገሮች ለመሄድ በነበረ ጉዞ 160 ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ባህረ ሰላጤ ተወርውረው አሽዋ ሆነው ቀርተዋል፡፡ ይህ ዜናም ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይ ደግሞ ለሞች ወላጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ነበር ።ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በግንቦት 2010 ዓ.ም ሌላ አሳዝኝ ዜና ሰምተናል፡፡ 100 ስደተኞችን ይዛ ስትጎዝ የነበረች ጀልባ በመስመጦ የ46 ኢትዮጵያውያን ህይዎት አልፎል፡፡ የተለያዩ መስመሮች በመጠቀም ከኢትዮጵያ ወደ ተቀረው_ዓለም_የሚደረግ_ህገ_ወጥ_ስደት_የብዙ ኢትዮጵያውያንን ህይዎት መቅጠፉን እንደቀጠለ ነው፡፡ በቅርቡ እንደሰማነውም 57 ኢትዮጵያውን ይህን መስመር ተጠቅመው ለማለፍ ሲሞክሩ ባጋጠማቸው አደጋ ህይዎታቸውን አጥተዋል ፡፡
በየመን _በሚካሄደዉ_የርስበርስ ጦርነት_ሳቢያ_የደረሰዉ_ሰብዓዊ_ቀዉስ እነዚህን_ስደተኞች_በህገ_ወጥ ሰው አዘዋዋሪወች እጅ እንዲወድቁ እያደረጋቸዉ_ ነዉ። እንደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ዘገባ ለስደተኞችን ክፍት በተተወ ድንበር ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ስደተኞችን እንደ ልብ እያስገቡበት በመሆኑ ዛሬም በወር 7,000 የሚሆኑ ስደተኞች ይህንን አደገኛ የባህር ላይ ጉዞ በመጋፈጥ በየመን አቆርጠው ለማለፍ ይሞክራሉ፡፡ እስከ ሞት የሚያደርስ አደጋ እያጋጠማቸዉም ቢሆንም ባለፈዉ_ዓመት_ብቻ_ ወደ 87 ሺህ የሚጠጉ ሰደተኞች የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ባህር አቋርጠዉ ወደ የመን ጉዞ አድርገዋል።በዚህ_ጉዞም_በርካቶች_የኤደን ባህረ ስላጤ አሽዋ ሆነው ቀርተዋል ፡፡ በባለፈው የጎርጎሮሳዊው 2018 ዓም ብቻ በሜዴትራንያን ባህር አድርገው የአውሮፓ ህብረት ደቡባዊ ድንበር ወደ ሆኑት ጣልያን፣ ግሪክ ፣ማልታ እና ስፔን የገቡ ስደተኞች ቁጥር ከ 112 ሺህ በላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ዘገባ ያስታውሳል ። ሌሎች ከ6700 በላይ ስደተኞች ደግሞ_በእግር ስፔን ገብተዋል። እነዚህ ከአደገኛ የበረሃ እና የባህር ጉዞ አሽዋ ሳይበላቸው እንደ ዕድል በህይወት ተርፈው አውሮፓ መድረስ የቻሉት ብቻ ናቸው። በአንጻሩ መንገድ ላይ የባህር አሽዋ ሲሳይ ሆነው የቀሩትን ቤት ይቁጠራቸው።የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በዚህ የጉዞ መስመር የሞቱ እና የደረሱበት ያልተወቀ ስደተኞች ቁጥር 2262 በላይ መሆኑን አስታውቋል። ታዲያ ይህን እየሰሙና እያዩ አሁንም ሰዎች በህገ- ወጥ መንገድ ይሄዳሉ። የስደተኞች ስቃይና መከራም በዚያው ልክ ቀጥሎል።ምክንያቱም የሚደረገው በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ስደተኞች ገና እግራቸው ከቤት ከመውጣቱ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች እጅ ውስጥ ይገባሉ፡:፡ ከዚያም በእነዚህ ሰብአዊነት የማይሰማቸው ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ስቃይና መከራ እንዲያሳልፉ ይገደዳሉ። ሲከፋም ህወታቸውን እስከመንጠቅ ይደርሳሉ።
ከእንግዲህ ይብቃ ስቃይ በምድርሽ ላይ
ሄዶ ከመሆን የባዳ አገር ሲሳይ …………
እንዳለው እኛ ኢትዮጵውያንን ባህር ላይ የአሽዋ ሲሳይ ከመሆንን ይብቃ ማለት ይኖርብናል፡፡ ታዋቂው ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “እኛ “በሚል ግጥሙ ላይ የእኛ የኢትዮፕያውያንን የስደት ስቃይ እንዲህ ሲል አስፍሮታል፡፡
ኖረን እኮ አናውቅም
ከባህር ጠርዝ ላይ
እንደ ክቡር ድንጋይ
እሬሳ ስንለቅም።
ከሙሴ ተምረን
ባህር መግመስ ሲያምረን
በታንኳ ሄድንና በሳጥን ተመለስን…….
በቅርቡን 32ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሪዎቹ ስደትን ለመከላከል እና ተመላሽ ስደተኞችን ለማቆቆም የሚረዱ ስትራቴጀዎችን በመንደፍ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ፡፡ ሁሉም ህገ ወጥ ስደትን ለመከላከል በርትቶ ከሰራ ከስደት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያን የሞት ዜና የማንሰማበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም እላለው፡፡ ያኔም እኛ ኢትዮጵያውያን የአውሬ ሲሳይ እና የበርሀ አሽዋ ከመሆን እንተርፋለን ፡፡
(አሸናፊ በሪሁን seefar በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ተቆም ውስጥ የሚዲያ ባለሙያ ናቸው)