>

እዉን 1 ሚሊዮን ኦሮሞ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅሏልን? (ውብሸት ሙላት)


እዉን 1 ሚሊዮን ኦሮሞ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅሏልን?
ውብሸት ሙላት
በ1999ኙ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት መሠረት በሶማሌ ክልል የሚገኘዉ  ኦሮሞ ብዛት 20,263 (ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ስድሳ ሦስት) ነዉ፡፡ በአስር ዓመት ጊዜ በምን ፍጥነት ቢባዛ 1 ሚሊዮን ደረሰና ተፈናቀለ? ሶማሊያ ክልል የሚገኘዉ አማራ ከኦሮሞ ይበልጣል፡፡ በዚሁ ወቅት በተደረገዉ ሕብና ቤት ቆጠራ መሠረት 29,525 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ሃያ አምስት) ነዉ፡፡  ከ1999 ዓ.ም. ወዲህ ከኦሮሚያ ወደ ሶማሌ የተደረገ የኦሮሞ መፈናቀል ይም ስደት መኖሩ አልተሰማም፡፡ ታዲያ በአስር ዓመት ጊዜ ዉስጥ ሃያ ሺህ ሰዉ በምን የወሊድ መጠን ተዋልዶ አንድ ሚሊዮን ደረሰ ?
 እንድህም ሆኖ፣ ሁለት መላ ምቶች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪዉ፣1 ሚሊዮን ኦሮሞ አልተፈናቀለም፡፡ በእጥፍ ቢጨምር እንኳን ከ50 ሺህ አይበልጥምና፣የሌለ ሰዉ አይፈናቀልም፡፡ ሁለተኛዉ መላ ምት፣ በተጨማባጭ 1 ሚሊዮን ኦሮሞ ከተፈናቀለ፣ በወቅቱ ኦሮሞዎቹ ሶማሌ ነን ብለዉ ተቆጥረዋል ማለት ነዉ፡፡ (በነገራችን ላይ የአዳማ፣የድሬዳዋ፣ የሀዋሳ፣የባህርዳር ሕዝብ ተደምሮ 1 ሚሊዮን ገደማ ነዉ የሚሆነዉ፡፡ ይሄን ያህል ሕዝብ ተፈናቅሏል ማለት ነዉ፡፡)
ጌዴዮ….
……..
በደቡብ ክልል የሚገኘዉ የጌድዮ ሕዝብ ብዛት 731872 ሲሆን ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ጌዲዮዎች ደግሞ 242, 529 ነዉ፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ በጠቅላላዉ የሚገኙት  975,506 ናቸዉ፡፡ ከኦሮሚያ ክልል፣ ከጉጂ ዞን ብቻ እንዴት 1 ሚሊዮን ገደማ ጌዲዮዎች ተፈናቀሉ? ከአስር ዓመት በፊት ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚገኙት ጌዲዮዎች ከሩብ ሚሊዮን በታች ከሆኑ እንዴት አድርጎ፣ ለዚያዉም በአንድ ዞን ብቻ ከአራት እጥፍ በላይ አደጉ? ሁለት መላምቶችን ላስቀምጥ፡፡ መላምት አንድ፣ በ1999 ዓ.ም. በተደረገዉ ቆጠራ፣ በጉጂ ዞን የሚገኙት ጌድዮዎች ኦሮሞ ተብለዉ ተቆጥረዋል፡፡ መላምት ሁለት፣ በ2010 ዓ.ም. 1 ሚሊዮን ገደማ ከጉጂ ዞን ተፈናቀሉ የተባሉት ጌዲዮዎች ዉሸት ነዉ፣ ቁጥራቸዉ ዝቅተኛ ነዉ፡፡ (አጥንታችሁ ድረሱበት!)
(ጌዲዮም ኦሮሞንም በሚመለከት ወይ የዉሸት ቆጠራ ነበር፣ ወይ የዉሸት የመፈናቀል ቁጥር ቀርቧል!)
አዲስ አበባ
……………..
በዚሁ በ1999ኙ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የአዲስ አበባ ነዋሪ ብዛት 2,739,551 ነዉ፡፡ ከእዚህ ቁጥር በሕዝብ ብዛት ከ1 እስከ 5 የሚይዙት ብሔሮች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1ኛ. አማራ- 1,288,895
2ኛ. ኦሮሞ-534,547
3ኛ. ጉራጌ- 447,777
4ኛ. ትግሬ- 169,182
5ኛ. ስልጤ- 80,660
6ኛ. ጋሞ –  45,985 ናቸዉ፡፡
የስድስቱ ድምር 2,567,046 ነዉ፡፡ ቀሪዉ 170 ሺህ ገደማ ደገሞ ቀሪዎቹ ሰማኒያ ገደማ ብሔሮች ይይዙታል ማለት ነዉ፡፡
የአዲስ አበባ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ መብት እንዳለዉ ሕገ መንግሥቱ በማያወላዳ መልኩ አስቀምጦታል፡፡ ይሁን እንጂ፣በየክልሎች ፓርቲ እየተገዛች ነዉ፡፡ እንደዚያም ከሆነ፣ የአማራ ዉክልና ከኦሮሞ ከሁለት እጥፍ በላይ፣ የደቡብ ከኦሮሞ በአንድ ተኩል ከፍ፣ የትግራይ ደግሞ የአማራን አንድ ስድስተኛ ገደማ መሆን ነበረበት፡፡
(የሥልጣን ድልድሉ፣ የንግድ ባንክ ለተፈናቃይ ርዳታ ያከፋፈለበት ስታይልም መሆኑ ነዉ፡፡ ንግድ ባንክ በሬሽዮ ያከፋፈለዉን የተቀበለ፣ አዲስ አበባ ላይ ሥልጣኑን በሬሽዮ መሆን የለበትም የሚል ያለ አይመስለኝም)
(ሌላ ቅንፍ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ fake news መግለጫና ምክር ሰጥተዋል ከሰሞኑ፤ Fake news እንዲህ ዓይነቱንም አይጨምር ይሆን?)
Filed in: Amharic