>
8:03 am - Wednesday July 6, 2022

"ኢትዮጵያ ምናልባት ትጎሳቆል አንደሁ አንጅ ያለጥርጥር አትሞትም" …ይድረስ ለደ/ር አብይ አህመድ (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

“ኢትዮጵያ ምናልባት ትጎሳቆል አንደሁ አንጅ ያለጥርጥር አትሞትም” …።
ይድረስ ለደ/ር አብይ አህመድ፤የኢ/ፌ/ዲ/ሪ/መ፤ጠ/ሚንስትር

 

መንገሻ ዘውዱ ተፈራ

 

ክቡር ጠ/ሚንስትር፤በእውነቱ እረስዎ ካለዎ የትምህርት ዝግጅት፤ከመጡበት የሥራና ሕይዎት ተሞክሮ፤ከልጅነትዎ ጀምሮ አሰከ ዕለተ ርዕሰ መንግሥት ስልጣነ መብቃተዎ ድረስ፤ካሳደጉዎ፤የእድሜ ልክ አለቆችዎና፤ባለውለታዎችዎ፤ህወኃት ግዞት፤እራሰዎን ነጥለው፤ይህን ያህል ጊዜ ማምጣተዎ፤ በእራሱ ትልቅ ሊያስመሰግነዎ የሚገባ ሥራ አንጅ የሚያስነቅፈዎ ሊሆን አይገባም።መንቀፍ ካስፈለገ፤ በዘር ፖለቲካ፤በኢሰባዊ ግድያ፤በሰብአዊ መብት ጥሰት፤የሙስናና ሌብነት ስርዓት፤ነግሶባት በነበረች ሐገር፤እርሰዎም ከእነዚህ ግፍ ፈፃሚ ስርዓት ዘዋሪዎች ውስጥ መውጣተዎንና፤ሰውነትዎን እንኳ ዘንግተን፤በመላዕክታን መደብ ያስቀመጥነዎ፤ከዳር አስከ ዳር፤ያለነው እኛ መላው ኢትዮጵዊያን ነን። ምክንያቱም እኛስ ምን ይጠበቅብን ነበር፤ብለን እራሳችን ሳንጠይቅ፤ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም፤ እንደሚባለው የእራሳችን ኃላፊነት ረስተን፤”አይጥ ድመትን በይ ልጄን ጠብቂልኝ ብላ አንደሄደችው”ሁሉን ለእርሰዎ አሽክመን በእርሰዎ እጣት ቅስራ ተገቢ አይሆንም። አንደ ሰውኛ እርሰዎም አሰከ አሁን ላደረጉት አሁን የተከሰተው ችግር፤አሁን ካለው ሳይብስ በጧት ስለተደረሰበት፤ ምስጋና እንጅ መወነጃጀል አያስፈልገውም።ታዲያ እርሰዎም በዚህ ግራ ሳይጋቡ፤ከእርስዎ በፊት ካለፉት ሁለት የመንግሥት ፍፃሜ አስረጅዎች በመማር ኢትዮጵያን ከዚህ ጉድ የሚታደግ ስራ በመስራት ሁኔታዎችንን ለመቀየር መጣር ነው።
በአንድ ወቅት አንደሰማሁት፤አፄ ኃይለስላሴ የመሬት ላራሹ ጥያቄ፤ከ1960ዎቹም ትንሽ ቀደም ብሎ ሲያይልባቸውና፤በተማሪው ሲስተጋባባቸው፤ይህን በኃይል ለማፈን፤ለነባሩ ወታደር የደብድቡ ትዕዛዝ ይሰጣሉ። ነባሩ ወታደር ደግሞ ልጆቻችን ምን አደረጉ?አንደበድብም፤ብሎ ትዕዛዛቸውን እንዳልፈፀመ ይረዳሉ።አፄ ኃይለስላሴም፤ይህን ትዕዛዝ የሚፈፅም፤በወር ባለ5 ብር ደመወዝተኛ (ባለ ቡጅ)፤ብሔራዊ ጦር የሚሉትን አቋቋሙ።ይህ ጦር በዓመት አንድ ጊዜ ሐምሌና ነሐሴ፤በተወሱ ማሰልጠኛ ገብቶ ቆይቶ፤ለዓመት የተጠራቀመችለትን 60 ብር፤ይዞ መመለስና የተለመደ ግብርና ሥራውን እየሰራ፤ ተማሪ ሲያምፅና ጥሪ ሲደረግለት ከቶ ተማሪን ደብድቦ አመፁን ማስቆም ነበር ግዴታው።ነገር ግን አፄ ኃይለስላሴ ስልጣን ይብቃቸው የሚለው ጉርምርምታና አመፁ፤ወደ ቤተሰብም ተሸጋገርና፤ቤተሰብ አሰኪ ልጆቻቻን በሎ ለአመፅ የሚነሳ ሆነ።ታዲያ ይህ ያላዋጣቸው ንጉሱ፤በሉ ይህ የመሬት ላራሹ ጉዳይ አልባት ይሠጠው ብለው በመምከር፤በምክር ቤትና፤ህግ መወሰኛው ፀድቆ፤ለአፈፃፀም ለሚንስትሮች ምክር ቤት ተመርቶ ነበር አሉ።ነግር ግን አፄ ኃይለስላሴ፤ማዘዝ አቅቷቸው የነበርው፤ወጣቱን ከነወላጁ፤ ፖሊስ ሰራዊቱን፤ብቻ ሳይሆን፤ሚነስትሮቻቸውንም ሰለነበር፤የመሬት ላራሹን የምከር ቤትንና፤ህግ መወሳኛ ውሳኔ፤ሚነስትሮቻቸው ትግሎ የሚንቀሳቀሰው፤በአዲስ አስተሳሰብ፤በሰለጠነ ትውልድ መሆኑን፤መረዳት ባለመቻላቸው፤ይሁን በማን አለብኝነት፤ሌላ ጥገናዊ የአፈፃፀም ስልት ነድፈው፤ ተገልሎ ለነበረው የኢትዮጵያ እርበኛና ባላባት፤በአይኑ እንኳ ሊያየው የማይችለውን፤ከሦሰት፣አስከ አምስት ጋሻ መሬት፤ከሊሻን ጋር ሰጠንህ በማለት ለማለዘብ፤ያልሆን ነገር ሲሰሩ፤ምናልባትም በዓለም ለመጀምሪያ ጊዜ በሚባል፤አይደለም ሰውን፤አጠቃላይ ፍጥረትን በሚያስደነግጥ፤ሊገደሉ ቀርቶ ሊታዩ፤ግርማቸው ይፈሩ የነበሩ 62 አዛወንት ሰዎች፤አንዳልሆነ ሆነው የተገደሉበት፤የአፄ ኃይለስላሴ ስርዓቱም፤በሚያሳፍር ሁኔታ፤እንዳልሆነ ሆኖ የተገረሰሰበትን፤ማስታወስ አንዱ ነው።
“ኢትዮጵያ ትቅደም ያለምንም ደም”፤እያለ ምንም አንኳን ወንጀለኞች ናቸው ቢባል፤በዚያ መልክ መገደል ባልነበረባቸው፤62 አዛውንቶች ደም እጁን ታጥቦ የጀመረው ደርግም፤ብዙውን እንተወውና በ1980 ጀምሮ የነበረውን የደርግ ሰልጣን ወደ ገደል ማኮብኮብና፤ቀን የሰጠው ቅል ደንጋይ ይሰብራል እንደሚባለው፤ወያኔ ወደ ስልጣን አፋፍ ሰትሙጨለጨል፤የነበረውን ክስተት ብናይ፤በ1982 ዓ/ም፤የጊዜ ስህተት ካለ ይቅርታ፣ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣የባለ አደራ መንግሥት ይቋቋም የሚል ኃሳብ ለደርግ ያቀርባሉ።ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ደርግ እንደ ወደቅ ያውቁ የነበረው ከ1980 ዓ/ም ጀምሮ ስለነበር፣የወያኔን መዳረሻ ተደብቆ፤ከሬዲዮ ጣቢያቸው ማዳመጥ የጧት ቁርስ ማወራራጃ፤የማታ እራት መጀመሪያ ተግባር ነበር።ደርግ የፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያምን ኃሳብ ቢቀበለው ኖሮ፤ሲሆን ሊደንበት፤አለበለዚያ ደግሞ አድሜውን የሚያራዝምለት።የወያኔን ለድል ማኮብኮብን ደግሞ የሚያዘገይ፤ምንልባትም የማይቻል የሚያደርግ ነበር።ነገር ግን ደርግ ለዚህ ኃሳብ ቁብ ሳይሰጠው፤ወያኔን ግን አንዴት አንዲህ ያለ ኃሳብ አቀረቡ ብለው፤በፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ላይ ውርጅብኝ ሲያውረዱና፤ አንደ አብድ ሲያደርጋቸው፤ከሬዲዮ ጣቢያቸው ይሰማ ነበር።ታዲያ ደርግም፤አንደነዚህ ያሉ ጥሩ አጋጣሚዎችንም ሳይጠቀምባቸው፤ከአጤው ሰህተት ሳይማር፤አህል ውሃው እንዳልሆነ ሆኖ እኛንም ለዚህ መከራ ዳርጎን ማለቁ ሁለተኛው ነው።

ክቡር ጠ/ሚንስትር፤ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት አጣብቂኝ፤አጅግ ፈታኝ፤የህግ የበላይነት ለማስከበር የከበደበት፤ታይቶና ተስምቶ በማይታወቅ ሁኔታ፤ዜጋ ከገዛ መሬቱ በሐገሩ ውስጥ የሚፈናቀልበት፤ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ተስፋ የጣልንበት፤እርሰዎ የመጡበት ድርጅት፤ኦዴፓም፤በመሬት ባለቤትነት ሽፍጥ፤የጨረቃ መሬት ወረራ፤ስራ መገኘት፤ዋና ዋናዎቹና ጥቂቶቹ ናቸው።ታዲያ ይህ ግራ አጋቢ ሁኔታ አስጨንቆዎትና አሳፍሮዎት፤እርሰዎ ስልጣን በቃኝ ቢሉ፤ይታየዎ ሊተካዎ አንኳን የሚችል ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ፤ግለሰብ ባልታሰበበት፤ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእርሰዎ ተስፋ ጥለን በምንገኝበት፤መሆኑ ነገሮችን የባሰ ውስብስብ ያደረገዋል።እርሰዎም ደግሞ ሁኔታዎችን ዝም ብለው መጎተቱና፤አላስፈላጊ ጊዜ ማጥፋቱ፤ከትርፉ ኪሳራው አንደሚሚዝን መገመት ከባድ አይደለም።

ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ ይላሉ፤የጥንት ሊቃውንት አባቶች፤ተስፋ ያጣን ነገር ሲገልፁና፤የልቅ በቶሎ በስዓቱ አዋጭ ስራ አንዲሰራ ሲመክሩ።አንደተባለው፤እረስዎም ነቅተዋል፤ህዝብ እንደሚጠራጠርዎ ይገምታሉ፤እኛ ህዝቦችም ነቅተናል፤እርሰዎ ከአንግዲህ ያለ አድልዎ ይመሩናል ብልን ለማመን አንቸገርአለን፤ታዲያ በእንደዚህ ተነቃቅቶ፤ልብ ለልብ ሳይገናኙ፤አብሮ መጓዝ ደግሞ፤የብልጣ ብልጥ፤እባባ ለእባብ ይሄዳሉ ካብ ለካብ፤ውጤት አልባ ልፋት ነው።

ሰለዚህ በዚህ መልክ ለከፋ ችግር ከመዳረጋችን በፊት፤አሁንም እርሰዎ የአሻጋሪ መሪነቱን እንደያዙ፤ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅት፤ከህዝብ አደረጃጀት፤ከህዝብ ከእራሱ፤በአጠቃላይ ከሚመለከታቸው የተውጣጡ፤አባላት የሚገኙበት፤የሽግግር መንግሥት፤ለሦሰት ዓመት አድሜ ቢያቋቁሙና፤በገለልተኛ ሰራዊት፤በገለልተኛ አገልግሎት ሰጭ ሰራተኛ፤በገለልተኛ ሰብዕአዊ መብት ተከራካሪዎች በነፃነት መንቀሳቀስ አድል፤በገለልተኛ ሚዲያ፤የለበጣ ሳይሆን በፍፁም እውነተኛ ዲሞክራሲ በተመሰረተ፤ ስራዎችን በማደራጀት፣በመሥራትና፣በመምራት፣ከሦስት ዓመት በኃላ፤በፖለቲካ ውድድር፤ላለፈ ስልጣን የማስረከብና ኢትዮጵያነ የማዳን አድለዎ አሁንም በእጅዎ ነው።

ክቡር ጠ/ሚንስትር፤አፍሪካዊ ስልጣን የመውደድ አባዜ፤እርሰዎንም ካልተጠናዎተዎት በስተቀር፤ በእርግጠኝነት ኢትዮጵያን ማዳን፤ብሎም ይህን አሰከአሁን ሁላችንም ያፈዘዘውን፤ስብዕናዎንና ሰምዎን፤አንደ አጤ ቴዎድሮስ፤ብሎም አንደዘመኑ መሪ ፕሬዘዳንት ኔልሰን ማንዴላ፤ለሐገር፣ለእኛ ዜጎችዎና፣ለልጆችዎ፤ጥሎ የማለፍ አድሉ በእጅዎ ነው።ይህን ባያደርጉ ግን እርሰዎ ይቀርበወታል እንጅ፤”ኢትዮጵያ ምናልባት ትጎሳቆል አንደሁ አንጅ ያለጥርጥር አትሞትም” ወደፊትም ትቀጥላለች።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላዓለም ትኑር።

Filed in: Amharic