>

ጉምዞችን በሚመለከት የተለየ ፖሊሲ አስፈላጊነት!!! (ውብሸት ሙላት)

ጉምዞችን በሚመለከት የተለየ ፖሊሲ አስፈላጊነት!!!
ውብሸት ሙላት
* በመተክል ዞን የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ጉምዞች አማራን በያገኙበት በቀስት በመዉጋት እየገደሉ ነዉ!!!
 
ይህ የምትመለከቱት አሰቃቂ ምስል የተነሳው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ነው። እየተባባሰ ስለመጣው አረመኔያዌ ድርጊት ከቀናት በፊት ጀምሮ የአማራ አክቲቪስቶች ብቻ ሳይሆኑ እኔ የማናውቃቸው ( ያስተርማኳቸው እና ዳኛም ዓቃቤ ሕግም)  የጉምዝ ተወላጆች የችግሩን አሳሳቢነት በይፋ አሳውቀዋል። ሥራቸው ሕግና ሥርዓት ማስከበር የሆነው የክልሉና የፌደራል ፖሊስ፣ መከላከያ ሠራዊት ፣ ብሔራዊ ደኅንንት ወዘተ እየተነገራቸውም ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል። እነዚህ የጸጥታ ተቋማት ላይ የተሠራው ሪፎርም “የተወሰነ ሰው ሕይወቱን ሳያጣ፣ ሳይገዳደል፣ ምንም ዓይነት የመከላከል እርምጃ እንዳትወስዱ” የሚልም ጭምር ሳይሆን አይቀርም።
 
አሳዛኝ ነው!!!!
 
ጉምዞችን በሚመለከት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የፌደራል መንግሥት የተለዬ ፕሮጀክት በመንደፍ የአኗኗር፣የሥርዓት ገብ፣  የሕግ አክባሪነት ወዘተ ባህላቸዉን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ብዙ የጉምዝ ተወላጆች ማኅበራዊ ኑሯቸዉን፣ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸዉን፣ ከሌላዉ ማኅበረሰብ ጋር የአኗኗር ዘዴያቸዉን፣በሕግና ሥርዓት የመተዳደር ዝንባሌያቸዉን ወዘተ እየለወጡ መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ፣ የዚያኑ ያህል የሚቀሩ ጉዳዮች የትየለሌ ናቸዉ፡፡ በጣም ጥቂቶቹን ብቻ ልጥቀስ፡፡
በአመጋገብ ረገድ የእርሻ ሥራ አለመሠማራትና በአደን መኖር አንዱ ነዉ፡፡ ለአደን የሚመርጧቸዉ እንስሳት ደግሞ ከሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ብዙም እያቀራረባቸዉ አይደለም፡፡ ለአደን የሚመርጧቸዉ አይጥ፣ ጥንቼል፣ ሽኮኮ ወዘተ የሆኑ rodents ናቸዉ፡፡ ይሄ ከሌሎች ብሔሮች ጋር የሚኖርን ግንኙነትና መስተጋብር ሊያፋጥነዉ አልቻለም፡፡ ሌሎች ብሔሮች (ሽናሻ፣ አገዉ፣ በርታ፣ አማራ፣ ኦሮሞ….ወዘተ) ጋር በጋብቻ መተሳሰር፣ መዛመድ የመሳሰሉት ሊፋጠኑ አልቻሉም፡፡
የጉምዝ ተወላጆች የያዙትን መሬት በራሳቸዉን አርሰዉ ከመመገብ፣ ለኑሯቸዉ ደፋ ቀና ከማለት ይልቅ በስፋት ከያዙት መሬት ለሌሎች ብሔሮች ተወላጆች በማከራየት ወደመተዳደር ያዘነብላሉ፡፡ ከኪራይ በሚገኝ ገንዝብ ብቻ ለመተዳደር መምረጥ ሥራፈትነትን ያበረታታል፡፡ ይሔን ዓይነቱ የኑሮ ይትባሃል፣ከኪራይ የተቀበሉት ገንዝብ ሲያልቅ ተጨማሪ ገንዝብ መጠየቅ፣የተከራዮችን አዝእርት መቀማት፣ተከራዮችን ማባረር የተለመደ የግጭት መንስኤ ነዉ፡፡ በዚያ ላይ፣ ብዙ ሥራ የሚከናወነዉ በሴቶች በመሆኑ ብዙ ወንዶቹ ሥራፈት ስለሚሆኑ፣ (ስለሆኑ) ለጠብ ይፈጥናሉ፡፡  ሃብትና ንብረቱን የሚነጠቀዉ ተከራይ ለፍቶ አዳሪ ንብረቱን አልሰጥም በማለት ግጭት ሲፈጠር በድንገት አንድ የጉምዝ ተወላጅ አንድ አካባቢ ቢሞት (ቢገደል)፣ ሌሎች ጉምዞች በአካባቢያቸዉ ያገኙትን ከጉምዝ ዉጭ የሆነ ሌላዉን “ቀይ” ሰዉ ሁሉ የመግደል ማኅበራዊ ልማድ አላቸዉ፡፡
በዚያ ላይ፣ጉምዞች ለአደን ሳይሆን ለሰዉ መግደያነት የሚጠቀሙት ቀስት የሚባለዉ ባሕላዊ የጦር መሳሪያ መርዝ የተቀባ ስለሆነ በዚያ የመቱት የመሞቱ ነገር ሳይታለም የተፈታ ነዉ፡፡ ስለሆነም የቀስት አያያዝ ቁጥጥርም አስፈላጊ ነዉ፡፡ ቀስት መጠቀምን እንዲተዉ፣ ቀስት ይዞ የተገኘን የሚቀጣ ሕግ ማወጣትና እንደ ሕጉ መፈጸምም መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡  በነገራችን ላይ ጫካ ዉስጥ የገባን የጉምዝ ባለ ቀስት ለመከላከያ ሠራዊትም ከባድ ፈተና ነዉ፡፡ ብዙ ጉዳት አድርሰዉም ያዉቃሉ፡፡
በአንዳንድ ቦታ በጫካ የሚኖሩ በአደን የሚተዳደሩ እንዲሁም በቀስት እየገደሉ ወደ ጫካ መግባት ልማድ ስላደረጉት ይህንን የአኗኗር ዘያቸዉን የሚቀይሩበት አሠራር መዘርጋት ግድ ነዉ፡፡ በአንድ አካባቢ ማስፈር፣ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ፣ተመልሶ ወደ ጫካ የሚሄድን በወንጀል ተጠያቂ ማድረግና መቅጣት፣ በቋሚነት ሠፍረዉ ከሚኖሩበት አካባቢ እየጠፉ እንዳይሄዱ ማለማመድም መቆጣጠርም አስፈላጊ ሳይሆን አይቀርም፡፡
በዚያ ላይ የሃይማኖት ተቋማትም (የፕሮቴስታንት፣የካቶሊክ፣የኦርቶዶክስ፣የእስልምና ወዘተ) በአካባቢዉ በስፋት በመንቀሳቀስ ሃይማኖተኛ እንዲሆኑ ማድረግም ተገቢ ነዉ፡፡ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ፣ሲኦልና ጀሃነብ፣ገነትና ጀነት እንዳለ ማስተማር የምግባር ለዉጥ ለማምጣት ጠቃሚ ነዉ፡፡ በነገራችን ላይ በጉምዝ ባህል አንዲት ሴት የወር አበባዋ ሲመጣ ከቤት ዉጭ  ነዉ የምታሳልፈዉ፡፡
ጉምዞችን ሃይማኖተኛ ማድረግ፣በሕግና ሥርዓት እንዲተዳደሩ ማለማመድ፣ለዚህ ዓይነቱ አካሄድ የሚሆን ፖሊሲ የክልሉና የፌደራሉ መንግሥት በጋራ መቀየስ አለባቸዉ፡፡ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥርም ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ አንዳንድ ግጭት ይኖር ዘንድ የሚፈልጉ ሰዎችም በቀላሉ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ እስከዛሬ በጭራሽ እንዲጻፍ አልመረጥኩም ነበር፡፡ አሁንም መጻፌ፣ መንግሥት የሁኔታዉን አሳሳቢነት ቢረዳዉ በማለት ነዉ፡፡
ታሪኩ እንዲህ ነዉ፡፡ ከ2009 ዓ.ም. በፊት አል መሃል ላይ ሰፊ የእርሻ መሬት የወሰደ  አንድ የሻለቃ ማእረግ ያለዉ ባለሃብት (ስሙን ላለመጥቀስ ነው) የተወሰኑ የጉምዝ ተወላጆች አማራን እንዲገድሉ ያሰለጥናቸዋል፡፡ በገደሉት ልክም ገንዘብ ሊከፍላቸዉ ይስማማሉ፡፡ ሥልጠና ሰጣቸዉ፡፡ መግደልም ጀመሩ፡፡ ግዲያዉ በጅምላ ሳይሆን በመምረጥ፣ እንዲሁም በድብቅ እንዲሆን ነዉ የሠለጠኑት፡፡ መግደላቸዉን ለማረጋገጥ፣ የገደሉትን ሰዉ እጅ ቆርጠዉ ለሻለቃዉ መዉሰድ አለባቸዉ፡፡ እጅ ሲሰጡ ይከፈላቸዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ እየገደሉ እጅ እየወሰዱ ገንዘብ መቀበል ጀመሩ፡፡ የተቀበሉትን ገንዘብ ባንክ ወስደዉ ሲየስገቡ ብሩ ፎርጅድ ነበርና የተወሰኑ ጉምዞች ይያዛሉ፡፡ ምርመራ ሲደረግ፣ ብሩን የሰጣቸዉን ሰዉ ይናገራሉ፡፡ ለምን እንደሰጣቸዉም ሲጠየቁ ታሪኩን ተናገሩ፡፡ ሻለቃዉ ተይዞም ተከስሶም እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ በአጭሩ ለማለት የፈለግኩት የብሔር ደርዝ ያለዉ ግጭት ለመቀስቀስ የሚፈልጉ ሰዎችም በቀላሉ እየተጠቀሙባቸዉ ነዉ፡፡
የክልሉም የፌደራሉም መንግሥት፣የሃይማኖት ተቋማትም፣ በተለይ ሴቶች ላይ የሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ጭምረ የጉምዞችን የአኗኗር ዘየ ለመቀየር መረባረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ፣ ጉምዞችም መግደላቸዉን አያቆሙም፡፡ መከላከያ ሠራዊት እንደፈለገ ገብቶ አረጋግቶ ቢወጣም ጉምዞች ነገም ይገድላሉ፡፡
 እዉነታዉን በመጋፈጥ ችግሩን ለመቅረፍ መጣር ነዉ መፍትሔዉ!
(ለሦስት ዓመታት ያህል፣99 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወላጆችን ደሴ ሥራ አመራርና ቢዝነስ ኮሌጅ ሕግ አስተምሬያለሁ፡፡ 4 ወይም 5 ማኦና ኮሞ፣ ወደ 30 የሚደርሱ ጉሙዝ፣ ወደ 20 ገደማ ሺናሻ እና ቀሪዎቹ የበርታ ተወላጆች ነበሩ፡፡ እንደ እዉነቱ፣ በብዙ ጉዳይ ላይ እንደ አስተማሪ ብቻ ሳይሆን እንደ ወንድምም አንዳንዴም እንደ አባትም ነበር ከተማሪዎቹ ጋር የነበረኝ ግንኙነት፡፡ )
Filed in: Amharic