>

የ ኢ.ዜ.ማ  የፖለቲካፕሮግራም  (ናትናኤል መኮንን)

የ ኢ.ዜ.ማ  የፖለቲካ ፕሮግራም
 ናትናኤል መኮንን
የኢ-ዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በወሳኝ መልኩ ያልተማከለ አስተዳደር (ፌዴራላዊ) ሥርዓትን መከተለን ምርጫው ያደረገ ነው፡፡ ከፍተኛው የመንግሥት ሃላፊነት በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ የሚመረጥ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት እንዲሆን አበክሮ ይሰራል፡፡ ኢ-ዜማ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በማረጋገጥ፤ ዜጎች ከማህበራዊ ፍትህ እሳቤ የሚመነጩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲዎች የሚከተል ፕሮግራም ከሚገኝ ትሩፋት ተጠቃሚ ይሆናሉ ብሎ ያምናል፡፡ ኢ-ዜማ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ በሥርዓት በማድረግ፤ ዜጎች ያለተፅእኖ ተሳትፎ ያደረጉበት፣ የመንግሥትን ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን በትጋት ይስራል፡፡ ዝርዝር የፖለቲካ ምልከታችን ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
1.1. የፖለቲካ ሥርዓቱ አደረጃጀት
1.1.1. ኢ-ዜማ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ መደረግ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ ሕገ መንግስቱ የግለሰብ መብትን የመብቶች ሁሉ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ እንዲወስደው፣ የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩ መሆናቸውን የሚቀበል፣በዘር ወይም በእምነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ያልተማከለ ፌዴራላዊ አስተዳደር እንዲኖር ይስራል፣
1.1.2. የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ከህዝብ ይሁንታ የሚገኝ መሆኑን በማመን በነፃ ፍትሓዊ ምርጫዎች ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ አማራጮቹን ለህዝብ ያቀርባል፤ ይህም የሕዝብ የሉዓላዊነት መገለጫ አንደሆነ እና ሥልጣን በሕዝብ ይሁንታ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጫ አድርጎ ይወስደዋል፡፡ የትግል ስልቱም ሰላማዊ ትግል ይሆናል፡፡
1.1.3. ማንኛውም የፖለቲካ ጥያቄዎች በውይይት እና በዴሞክራሲያዊ ስርኣት እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ወደ ህዝብ ውሣኔ እንዲሄዱ ስርዓት በማበጀት የህዝብን ውሣኔ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
1.1.4. የኢ-ዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን የኤኮኖሚ ነፃነት፣ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሁም የመኖሪያ ምድራችንን ከባቢ ሊጎዳ በሚችል መልኩ አይቀረፅም፡፡
1.1.5. ዜጎች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎችንም መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር በጋራ የመደራጀት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸው ይከበራል፣
1.1.6. የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሊገሰስ የማይችልና የማይገሰስ መሆኑን፤ በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም የተፈጥሮ ሃብት የሃገሪቱ ዜጎች ሁሉ የጋራ ሃብት መሆኑን ኢ-ዜማ ያምናል፣
1.1.7. ዜጎች በመላው ሃገሪቱ ያለምንም ገደብ መንቀሳቀስ መስራትና መኖር፣ ሃብት ማካበት፣ ባካባቢያቸውም ሆነ በሃገሪቱ ፖለቲካ ያለምንም ገደብ መሳተፍ የሚችሉበትን ያልተሸራረፉ መብቶች ያስከበረ፣
1.1.8. የዜጎችን ህይወት ነጻነትና ንብረት መከላከል የሃገሪቱ መንግስት ተቀዳሚና ፍጹማዊ ግዴታ መሆኑን ያምናል።
1.2. አጠቃላይ የመንግስት አደረጃጀት
1.2.1. የመንግስት አደረጃጀት ፌዴራላዊ ይሆናል፡፡ የፌዴራል መንግስትና የአካባቢ አስተዳደሮች ይኖራሉ፡፡ የአስተዳደር አካባቢዎች አወቃቀር በሚከተሉት መርሆዎች የተመሰረተ ይሆናል፤
1.2.1.1.
1.2.1.2. 1.2.1.3. 1.2.1.4.
መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ ቋንቋ፤ ባህል; ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን፤ የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት
ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠርን፤ መሠረት ባደረገ ሁኔታ ይሆናል፡፡
1.2.2. ፌዴራላዊ አወቃቀሩ አንዴ ተሰርቶ የሚያበቃለት ሳይሆን የተቀመጡትን መርሆዎችን ጠብቆ በህዝብ ውሣኔ ከኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገታችን ጋራ በመግባባት መንፈስ እየዳበረ የሚሄድ ይሆናል፡፡
1.2.3. የፌዴራል መንግሥቱና በአካባቢ መስተዳድር የሚሾሙ የመንግስት ባለሥልጣናት በሕግ የተወሰነ የየራሳቸው የሥልጣን ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ አንዱ በሌላው የውስጥ ጉዳይ እንዳይገባ ይደረጋል፡፡ የየራሳቸው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ ይኖራቸዋል፡፡ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸው የወንጀል መቆጣጠሪያ የፖሊስ ተቋም ይኖራቸዋል እንጂ ከዚያ ያለፈ ወታደራዊ ኃይል ማደራጀት አይችሉም። የፌደራል መንግሥቱ ብቻ ነው የተደራጀ የጦር ኃይል የሚኖረው።
1.2.4. አማርኛ የፌዴራል መንግስቱ የሥራ ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል፡፡ እንዲሁም በሕዝብ ውሳኔ ሲፀድቅ ከአማርኛ ሌላ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎች የፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲኖር ይደረጋል፡፡
1.2.5. የአካባቢ መስተዳድሮች የሥራ ቋንቋ በአካባቢው በሚኖረው ሕዝብ በሚያደርገው ሕዝበ ውሳኔ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ የአካባቢው መስተዳድር የዜጎችን በፌዴራል ስርዓት በቂ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ የፌዴራሉን የሥራ ቋንቋ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ማድረግ ይኖርበታል ብሎ ያምናል፡፡
1.2.6. የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ይሆናል፡፡ የመንግሥት ዓርማ የሚያስፈልገው ከሆነ በሕዝብ ይሁንታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ የፌዴራል መንግስት አደረጃጀት
1.3.የፌዴራል መንግስቱ በሕገ-መንግሰቱ መሰረት ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲደራጅ ይደረጋል፡፡ በህዝበ ውሳኔ በሚደረግ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ስርዓት መሰረት አድርጎ የሚከተሉት የፌዴራል ስርዓቶች እንዲዘረጉ ይደረጋል፤
1.3.1.1. 1.3.1.2. 1.3.1.3.
1.3.1.4. 1.3.1.5. 1.3.1.6.
1.3.1.7.
1.3.1.8. 1.3.1.9.
በዜጎች ቀጥተኛ ምርጫ በሚመረጠው ፕሬዚደንት ስር የሚቋቋመው የህግ አስፈጻሚው አካልና ህግ በሚያወጡት ሁለት ምክር ቤቶችና ህግ በሚተረጉመው ሶስተኛው አካል መሃል ግልጽነት ያለው ህገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል እንዲኖር፣ አንዱ በሌላው ስልጣን ጣልቃ እንዳይገባ ማድረግ፣ ለፕሬዜዳንትነት የሚመረጥ ሰው የጠቅላላውን መራጭ 50%+1 ማግኘት አለበት። በመጀመሪያው ዙር ማንም ተወዳዳሪ ይህንን ማግኘት ካልቻለ በሁለተኛ ዙር ሁለቱ ከፍተኛ ደምጽ ያገኙት ተወዳዳሪዎች ብቻ ተወዳድረው ያሸነፈው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ይሆናል።
ሕግ አውጪው አካል ሁለት ክፍሎች (የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት) የሚኖሩት ሲሆን ሁለቱም ሕግ የማውጣት ስልጣን ያላቸው እና በሕዝብ የተመረጡ ይሆናሉ፡፡ የፌዴራሽን ምክር ቤቱ በአስዳደር አካባቢዎች በእኩል የሚወከሉበት እና የአስተዳደር አካባቢዎች በሚኖራቸው ብሔረሰቦች ብዛት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ብሔረሰቦች ተጨማሪ ውክልና የሚሰጥ ሆኖ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲያገኙ ህጎችን የማመንጨት፤ ሕጎችን የመገምገም፤ አፈፃፀማቸውን የመከታተል ሃላፊነት ይኖርበታል፡፡
ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ሥልጣን ሕገ መንግስትን ለመተርጎም ስልጣን ለተሰጠው ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ ምክርቤቶች ሕግን ማውጣት እንጂ ሕገ-መንግስትን ወይም ሌሎች ሕጎችን የመተርጎም ሥልጣን አይኖራቸውም፡፡ የመንግስትን ስራ አስፈጻሚ አካላት እንዲመራ፣ ዜጎች በአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህ የሚመርጡት የሃገር መሪ እንዲኖር የሚያደርግ ፕሬዚደንታዊ የአስተዳደር ስርአት ይሆናል፣ ፕሬዝዳንቱ የሚመረጠው ለአምስት ዓመት ሆኖ በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ ሊመረጥ አይችልም፡፡ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ያልተስማማበትን የሕግ ረቂቅ ለፓርላማ የመመለስና እንደገና ውይይት እንዲደረግበት የማድረግ መብት ይኖረዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ እንደገና እንዲታይ የመለሰው የሕግ ረቂቅ በተወካዮች ምክር ቤትና በፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሦስት አራተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዝደንቱ ባይስማማበትም ሕግ ሆኖ ይወጣል፡፡
በአስፈጻሚ አካል ውስጥ በፖለቲካ ሹመት የሚመደቡ ኃላፊነቶች ተለይተው እንዲወሰኑ ይደረጋል፡፡ ማንኛውም የፌዴራል መንግስት የፖለቲካ ሹመት ሥልጣንና ኃላፊነት [በፕሬዜዳንቱ አቅራቢነት?] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት [ሲጸድቅ] ብቻ የሚወሰኑ ይሆናሉ፡፡ ሹመቱን የማጽደቁ ስራ የእያንዳንዱን እጩ ብቃት በነጠላ በመመርመር ይከናወናል፡፡
[ከፖለቲካ ሹመቱ ውጭ] በአስፈፃሚው አካል ሥር የሚዋቀረው ሲቪል ሰርቪስ ከፖለቲካ ገለልተኛ በሆነ መንገድ በችሎታ እና ብቃት ላይ ተመስርቶ በግልጽነትና በተጠያቂነት መንፈስ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ ይደራጃል፡፡ በሁሉም ያስተዳድር መዋቅር፤ (ቀበሌ፤ ወረዳ፤ ዞን፤ የአካባቢ መሰተዳድር፤ ፌደራል) ያካባቢው ነዋሪ በቀጥታ የሚመርጣቸው ያካባቢ አስተዳደሮች ይኖራሉ።
.1.10. ዜጎችየየአካባቢያቸውንየፍትህናየፖሊስሃላፊዎችበዴሞክራሲያዊመንገድእንዲሾሙናእንዲሽሩተሳትፎ የሚያድርጉበት ሥርዓት ይዘረጋል፣
ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቶች
ኢዜማ በሕገ-መንግሰት እውቅና የተሰጣቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ አገራችን የፈረመቻቸውን የሰው ልጆችን ስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚደነግጉ ስምምነቶችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የአገራችንን ልዩ ሁኔታ ባገናዘበ የቡድን (የብሔረሰብ፣ የሀይማኖት፣ ወዘተ) መብቶች ከግለሰብ መብቶች ጋር ግጭት በማይፈጥረበት መልኩ ጥበቃ የሚደረግለት ሲሆን፤ በጥናት ላይ የተመሰረተ የቡድን ፍላጎታቸውን ለማዳበር እንዲችሉ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም ሲቪል ማህበራት የዜጎችን ስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ለማዳበር በነፃነት እንዲደራጁ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደረግ ይሆናል፡፡
የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ፖሊስና ድህንነትን
1.5.1. የሃገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በሙሉ፤ የሃገሪቱን ሕገ-መንግሥት ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለህግ የበላይነትና ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር በጽናት የሚቆሙ ከፍተኛ እውቀትና ብቃት ባላቸው መሪዎችና አባላት የተደራጁ ተደርገው ይገነባሉ፤
1.5.2. የአገራችን የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት የአገሪቱን ዜጎች እና ሉዓላዊነት ከማንኛውም ስጋቶች ሽብርተኝነትን ጨምሮ ለመጠበቅ እንዲችሉ፤ የአከባቢያችን ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እና የአገሪቱን አቅም ባገናዘበ መልኩ ሙያዊ ጥራቱና ወቅታዊነቱ የተረጋገጠ ሥልጠና እና ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
1.5.3. የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት መንግስት በተቀያየረ ቁጥር የማይቀያየሩ እንደተቋም ቋሚ ሆኖ የመቀጠል ዋስትና ይኖራቸው ዘንድ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ፓርቲ ወገንተኝነት የራቁ ተቋማት እንዲሆኑ ይደረጋል፤
1.5.4. የመከላካያና የፖሊስ አባላት ከመደበኛ ወታደራዊ/ፖሊስ ሙያ ውጭ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ፣ ግዳጆች በሌሉባቸው ሰላማዊ ወቅቶች፣ ህዝብን በጤና፣ በደን ልማት፣ በሌሎች ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት፣ በአደጋ ደራሽነት ስራዎች ለማገልገል የሚያስችለው ብቃት ያለው ተቋም ተደርጎ ይደራጃል፣
1.5.5. የመከላከያ፣ የፖሊስና ደህንነት ተቋማት ለሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች፣ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ ባህል ተላባሾች የእምነት ባለቤቶች ተሳታፊነትን የሚያበረታታና የሚያደፋፍር ፖሊሲዎች ያለውና ፖሊሲዎቹን በተግባር የሚተገብር እውነተኛ ሃገራዊ ተቋም እንዲሆን ይደረጋል፣
2.የኢኮኖሚ ፕሮግራም
ኢዜማ ከሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና/ማህበራዊ ፍትህ/ ጋር የሚጣጣም ለዜጎች ኤኮኖሚያዊ ነፃነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የኤኮኖሚ ፕሮግራም እና ፖሊሲዎችን ይቀርፃል፡፡ ኢዜማ የመንግሰት የኤኮኖሚ ጣልቃገብነት ሊኖር የሚችልባቸውን ዘርፎች በመለየት በግልፅ የሚያስቀምጥ ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ከዜጎች ጋር መንግስት ውድድር ውስጥ ሊገባ የሚችልበት እድል አይኖርም፡፡
2.1. መርሆዎች
2.1.1. የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን የሚቀዳበት ዋና መርህ፤ የአንድ ሀገር ዋና የልማት መሰረትና ሀብት ሕዝቧ ነው ብሎ ይነሳል። የልማት ግብም ሕዝቡ እያደር የተሻለ የኢኮኖሚ ሕይወት እንዲኖረው ማስቻል ነው። ስለዚህም የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን ውጤታማነት የሚለካው ይህንን ያገሪቱን ትልቅ ሀብት ባግባቡና ምርታማ በሆነ መንገድ መጠቀምን፤ የዜጎችን ሁለንተናዊ ነጻነትን ማስፋትን (የፖለቲካ ነጻነት ብቻ ሳይሆን ዜጎች አምራች ዜጋ እንዳይሆኑ የሚገድቡ ማናቸውንም እንቅፋቶች ማንሳትን)፤ የዜጎችን አፍላቂነትና ተነሳሽነትን የሚያበረታታ እንዲሆን ማገዝ፤ ማህበረሰቡ በመሰረታዊ ቁሳዊ ፍላጎት ማጣት ምክንያት መሰረታዊ ነጻነቱን እንዳያጣ ማስቻል ዋና ጥቅል መመሪያዎቹ ይሆናሉ።
2.1.2. ኢዜማ ለዘላቂ ልማትና ብልጽግና ትኩረት በመስጠት የሕብረተሰቡን አጠቃላይ የኑሮ ደረጃና ማሕበራዊ ሕይወት የሚያሻሽል፤ [በመንግሥትና በግል ኢኮኖሚ መስኩ ትብብርና መደጋገፍ ላይ የተመሰረተ በስርዓት የሚመራ ገበያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይከተላል፡፡ የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዋና አንቀሳቃሽ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የሥራ አጥነት ሲከሰት፣ የኢኮኖሚ መቆርቆዝ
ሲያጋጥም፣ የዋጋ ግሽበት ሲመጣ፣ የመንግስት የበጀት ጉድለት እና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ መንግስት
በእውቀትና በጥናት ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ የማረጋጋት እርምጃ ይወስዳል፡፡
2.1.3. ከፍተኛ ካፒታል የሚጠይቅ፣ አዋጪነቱ አጠያያቂ ወይም የሚያስገኘው ጥቅም ከረዥም ጊዜ በኋላ ሲሆን ወይም ተፈላጊነቱ ስትራተጂካዊ በመሆኑ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር በሽርክና ወይም ለብቻው መሰረተ ልማትን ይገነባል፤ የልማት ድርጅቶችን አቋቁሞ ያስተዳድራል፡፡ በግል ባለሀብቶች ሊመሩ የሚችሉ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግሉ ይዞታ ወይም አስተዳደር
እንዲዛወሩ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፡፡
2.1.4. ኢዜማ ለኢኮኖሚ ዘላቂ ልማት ወሳኝ በሆኑ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም የነፃ ገበያ
ኤኮኖሚን እና የሀገር ሉዓላዊነትን ባስጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ዝርዝር ፖሊሲዎች ያውጣል፡፡
2.1.5. ኢዜማ ከዚህም በተጨማሪ ማህበራዊ ፍትህ በሀገሩ እንዲሰፍን፤ በራሳቸው ስንፍና ሳይሆን በገበያ ኢኮኖሚው ተገፍተው ለድህነት የተዳረጉ ዜጎችን ለመታደግ ከሀገሪቱ አቅም ጋር የተናበቡ የኢኮኖሚ
ፖሊሲ እርምጃዎችን ይወስዳል.
ግብርና
2.2.1. ግብርናን በተመለከተ- አብዛኛው የሀገሪቱ ህዝብ ገበሬ በመሆኑና ግብርናም መተዳደሪያው በመሆኑ፣ ከግብርና ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የግብርናውን የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያሳድጉና የገበሬውን ጥቅም የሚያስጠብቁ፣ ከመሬት ባለቤትነት፣ ከግብር፣ ተውፊታዊና ዘመናዊ አስተራረስና ምርት የማሳደግ፣ ከምርት ማከማቸት፣ ከገበያ አቅርቦት፣ ከመሰረተ ልማት እድገት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከምርቶች የአይነት ብዝሃነት ከአምራቹና ከሃገራዊ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ከግብርና ኢንዱስትሪ፣ ከንግድ፣ ከፋይናንስ፣ ከግል ካፒታል ተሳትፎና እንዲሁም ቴከኖሎጂን መሰረት አድርጎ ከእድገት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፖሊሲዎች በማጥናት ተግባራዊ ያደርጋል፣
2.2.2. ሰፋፊ እርሻዎች እንዲስፋፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን፣ በኩታ ገጠም ያሉ በአነስተኛ ማሣ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች በትብብር እንዲያለሙ ማበረታቻ ይሰጣቸዋል፡፡
2.2.3. የእንስሳና የአሳ ሃብትን በተመለከተ- ከግብርና ቀጥሎ የሃገሪቱ አብዛኛው አምራች ሃይል የተሰማራው በከብት እርባታ ላይ ነው። አሳ የሚያሰግሩ ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም በሃገራችን በቀላሉ ለበርካታዎች የስራ መስክና የከፍተኛ ሃገራዊ ሃብት ምንጭ መሆን የሚችል ነው። ከነዚህ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የአርብቶ አደሩንና የዓሣ አስጋሪውን ጥቅም የሚያስጠብቁ ከመሬት፣ ከሃይቆችና ከወንዞች አጠቃቀም፣ከተውፊታዊና ዘመናዊ ምርት የማሳደግ፣ ምርት አሰባሰብ፣ ከገበያ አቅርቦት፣ ከመሰረተ ልማት እድገት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከምርቶች የአይነት ብዝሃንነትና ጥራት፣ ከአምራቹና ከሃገራዊ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ከግብርና ኢንዱስትሪ፣ ከንግድና ከፋይናንስ እድገት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፖሊሲዎች በማጥናት ተግባራዊ ያደርጋል፣
ኢንዱስትሪ/የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
2.3.1. የኢንዱስትሪ/ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አሁን በአገሪቱ ያለውን ከፍተኛ የወጣት ሀይል ወደ ሥራ ለማስማራት የሚችል መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብቶች በዚህ ረገድ ለሚያደርጉት ተሣትፎ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ፖሊሲ ይነድፋል
2.3.2. ሰፊ የአምራች መሰረት ያለው፣ በአነስተኛና በመካከለኛ ደረጃ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አማካይነት ሃገራዊና ከባቢያዊ እንዲሁም አለማቀፋዊ ተፈላጊነት ያላቸውን ምርቶች በጥራት የሚያመርት፣ ቀጣይነት ያለው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ፣ ለጥናትና ምርምር፣ ለፈጠራና ለግኝት በቂ ካፒታል የሚያውል፣ በአከባቢያዊና በአለማቀፍ መድረኮች በምርት አይነትና ጥራት ተፎካካሪ መሆን የሚችል፣ ከገበሬውና ከግብርናው ዘርፍ ጋር በቅጡ የተሳሰረ፣ የአካባቢ ጥበቃን፣ የሰራተኛውን ጥቅምና ደህንነት የሚያስከብር፣ለውጭ ባላሃብቶች ከሃገሬው ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩበትን አግባብ የሚያበረታታ፣ ለሃገራዊ ባላሃብቶች እንክብካቤ የሚያደርግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማኑፋክቸሪንግ ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ ያደርጋል።
የአገልግሎት
2.4.1. የቱሪዝምና የሆቴል እንዱስትሪውን ጨምሮ ሌሎችንም በሃገራችን ያሉ የአገልግሎት ዘርፎችን በአንድ ስንደምራቸው በርካታ ባለሃብቶች ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ የሚሳተፉባቸውና የበርካታ የሃገሪቱ ዜጎች የስራ ምንጭ ናቸው። በአገልግሎት ዘርፉ የተሰማሩት ስራተኞች ቁጥር ከፋብሪካ ሰራተኞች ቁጥር እጅግ ይልቃል። በዘርፉ ጥራትና ልቀት ላይ የተመሰረቱ ለደንበኞቻቸው አስተማማኝ አግለግሎቶች የሚያቀርቡ ድርጅቶች እንዲስፋፉ ማድረግ፣
2.4.2. ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ቦታ እንዲኖራት የሚያስችል፣ አገሪቱ ያላትን ቅርሶችና የተፈጥሮ ሀብት በተገቢው በማስተዋወቅ፣ እንዲሁም በኮንፈረንስ ቱሪዝም ልታገኝ የምትችለውን ጥቅም ባገናዘበ መልኩ ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጠር ሲሆን ትምህርት ቤቶች ለቱሪዝም ሴክተሩ በተጠና ሁኔታ የሰው ሀይል እንዲያቀርቡ ፖሊሲዎች ይቀረፃሉ፡፡
2.4.3. የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ተለይተው በቂ የመሰረተ ልማትና ምቹ መስተንግዶ እንዲኖራቸው በማድረግ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም የተቀናጀ ስራ ይሰራል፡፡
የተፈጥሮ ሀብትና መሬት
በኢትዮጵያ የግዛት ክልል የሚገኝ ማንኛውም የተፈጥሮ ሀብት የሁሉም ዜጎች የጋራ ሀብት ነው ብሎ ኢዜማ ያምናል፡፡ አሁን ያለው የመሬት ፖሊሲ ለኢኮኖሚ እድገት ያለውን እንቅፋት በመረዳት የተለያዩ ዓይነት የመሬት አጠቃቀም እና ይዞታ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ የመሬት ይዞታም በመንግሰት፣ በማሕበረሰብ ወይም በግል ሊሆን ይችላል፡፡
2.5.1. በኢትዮጵያ ግዛት ክልል ዜጎች ያልሰፈሩበትን ቦታ ጨምሮ ሌሎች ፓርኮችና ለመንግሥት አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች በመንግሥት ይዞታነት ሊያዙ ይችላሉ፤ በመንግሥት ይዞታነት ያሉ ቦታዎች ግልፅ በሆነ መሰፈርት እና የገበያ ዋጋ ወደ ግል ሊዛወሩ ይችላሉ፤
2.5.2. በአርብቶ አደር አካባቢ ለግጦሽ፣ በሌሎች አካባቢም ለልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ በማሕበረሰቡ የሚተዳደሩ የወል የመሬት ይዞታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤
2.5.3. ዜጎች መሬትን በግል ይዞታነት በባለቤትነት መያዝ፣ ማከራየት፣ መግዛት መሸጥና መለወጥ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
2.5.4. ኢዜማ የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት ግልፅ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል፡ ፡
የከተማ ልማት
2.6.1. ኢዜማ አሁን አገራችን የምትገኝበትን ዝቅተኛ የከተሜነት ደረጃ ለመለወጥ፣ ቢያንስ በአፍሪካ ደረጃ በአጭር ጊዜ ለመድረስ የሚያስችል የከተሞች መስፋፋትን ያበረታታል፡፡ የአስተዳደር አካባቢዎች በተቻለ ሁኔታ ከአንድ ርዕሰ ከተማ ውጭ ለመፍጠር እንዲችሉ ማበረታቻ ይደረጋል፡፡ ዜጎች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው መስራት የሚችሉበትን ሰላማዊ ሁኔታ በመፍጠር የተለያዩ ከተሞች እንዲፈጠሩ የሚያበረታታ ፖሊሲ ይቀረፃል፡፡
2.6.2. የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከተሞችን ለመመስረት በሚያመች መልኩ እንዲሆኑ በማድረግ በገጠር መሬት ላይ ያለውን ጫና በመቀነስ ምርታማነት እንዲያድግ እገዛ የሚያደርግ ከተሜነት ያበረታታል፡፡
2.6.3. ከተሞች የአረንጓዴ ልማትን ያካተቱ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊነት
2.6.4. በሁሉም የአስተዳደር አካባቢዎች የሚገኙ ከተሞችም ሆነ እንደ ድሬዳዋና አዲስ አበባ ያሉ የፌደራል
ከተሞች ውስጥ በከተማው ነዋሪዎች የሚመረጡና የከተማውን ህዝብ ፍላጎትና ለከተማ ነዋሪዎች የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችን ማቅረብ ዋና ተልእኮአቸው ያደረጉ በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ የተመረጡ ከንቲባዎች የሚተዳደሩ የከተማ አስተዳደሮች ይደራጃሉ።
መስረተ ልማትን
2.7.1. መሰረተ ልማት ባጠቃላይ ኢኮኖሚውን አሳላጭና የሚያሳድግ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የስራ ፈጣሪ የኢኮኖሚ መስክ ነው። ማንኛውም የመሰረተ ልማት ስራ በሃገር ውስጥ ባለሃብቶችና ባለሙያተኞች፣
2.6.
2.7.
ግንቦት 1 ቀን 2011
በሃገር ውስጥ ሰራተኞች በሃገር ወስጥ በሚመረቱ የእቃ አቅርቦቶች የሚሰራበትን አግባብ ማመቻቸት፣ አቅም መገንባት ማናቸውንም የተለያዩ አሰፈላጊ ድጋፎች በማድረግ በከፍተኛ ጥራትና ልቀት የሚፈጽም ይሆናል። የተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተመጣጣኝ የሆነ የመስረተ ልማት ሽፋን እንዲያገኙ፣ በመሰረተልማት መረብ እንዲተሳሰሩ የሚያደርግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የመሰረተ ልማት ፖሊሲ ተግባራዊ ያደርጋል።
ትራንስፖርት፣ ኮምኒኬሽን፣ የዉሃና ፍሳሽ እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ከህዝቡ ገቢ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ በብዙሃን ማጓጓዣ ላይ የተመሰረተ የባቡሮችና የአውቶቡሶች አገልግሎቶች ማስፋፋት፣ ከኤሌትሪክ ማመንጨት እድገት ጋር ተያይዞ የሃገሪቱን የተለያዩ የአስተዳደር አካባቢዎችና ከተሞች በኤሌትሪክ ጉልበት በሚሰሩ ከተማና የአስተዳደር አካባቢ አቋራጭ የባቡር መጓጓዣዎች ማስተሳስር፤ አካባቢንና አየርን የሚበክሉ ማናቸውንም አይነት የመጓጓዣ ዘዴዎችን የሚቀንስ የትራንስፖርት ፖሊሲ መከተል፣
3.
2.8. የፋይናንስ እና የባንክ የአገልግሎት
19.1. ጥብቅ የሆነ የፊስካል እና ሞኒታሪ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ፣ ከአቅም በላይ መንጠራራትን፣ ከሃገሪቱ አመታዊ ገቢ የመክፈል አቅም ጋር ሲነጻጸር አደገኛ የሆነ፣ከውጭ ሃገርም ሆነ ከሃገር ውስጥ በመንግስት የሚወሰድን የብድር ስርአት የማይፈቅድ፣ የዋጋ ግሽበትን የሚቆጣጠር፣ የህዝብ ንብረት ብክነትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የአካውንቲንግና የኦዲቲንግ ሙያተኞችን ሃላፊነትን ያገናዘበ ህጋዊ ጥበቃ የሚደረግለት ነፃና ገለልተኛ የፋይናንስና የባንክ ፖሊሲ ተግባራዊ ያደርጋል፣
19.2. ጥናት ላይ ተመስረቶ ተገቢውን ወለድ በመክፈል የገንዘብ ቁጠባን የሚያበረታታ፣ የቢዝነስ የንግድና የፕሮጀክቶችን አዋጭነት በመገምገም ያለ ማስያዣ ለታታሪ ሰራተኞች ብድር የሚያሰጥ አሰራርን የሚያበረታታ፣ ባንኮች ከወለድ ነፃ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የፋይናንስ ሴክተር በዘር፣ በሀይማኖት ተለይቶ እንዳይደራጅ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡
የማሕበራዊ ፕሮግራም
2.7.2.
የኢዜማ ማህበራዊ ፕሮግራም ዓላማ፤ በተለያየ የተበላሻ የመንግሥት ፖሊስ በመገፋት ከኤኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲርቁ የተደረጉ ብቻ ሳይሆን በዚሁ መነሻ ለከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ ዜጎችን በስርዓቱ ውስጥ ለማካተት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡ ዜጎች በማህበራዊ ዘርፍ ኢዜማ የሚወስዳቸውን ተጨባጭ እርምጃዎች በመጠቀም እራሳቸውን ጠቅመው ለአገር የሚተርፉ ዜጎች ማድረግ የማህበራዊ ፕሮግራማችን ቀዳሚ ትኩረት ነው፡፡ የኢዜማ ፕሮግራም በምንም መልኩ ሥራ ጠልነት እና ድጋፍ ጠባቂነትን አያበረታታም፣ ዝርዝር ፖሊሲዎችም ይህን ታሣቢ ያደረጉ ይሆናሉ፡፡
3.1. ድህነት ማጥፋት
ኢዜማ ድህነት ዝም ብሎ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግር ብቻ ሳይሆን የሰውን ልጅ ነጻነት የሚገድብ፤ እንደፖለቲካ ማህበረሰብ በሰላም ለመኖር የማያስችለን ችግር መሆኑን ተገንዝቦ ድህነትን ከምድራችን ለማጥፋት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ይንቀሳቀሳል።
ኢዜማ ድህነት የመንግሰት ፖሊስ ድክመት ውጤትና በጥሩ ሁኔታ ቁጥጥር ያልተደረገበት ልቅ የገበያ ኢኮኖሚ ድክመት ውጤት መሆኑን ይገነዘባል። በመሆኑም ሥርዓቱ እነኝህን ድክመቶች ተገንዝቦ ድህነትን ከሀገራቸን ለማጥፋት መወሰድ ያለባቸውን ዝርዝር የፖሊሲና ያሰራር አቅጣጫዎች በጥናት ላይ በመመርኮዝ ተግባራዊ ያደርጋል። በተጨማሪም ዜጎች ድህነትን በመጠየፍ የሚወስዱት ተነሳሽነት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ ዜጎች ለስራ ያላቸውን ተነሳሽነት የሚያጎለብቱ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ይሰራሉ፡፡
3.2. የሰው ሀይል ፍልሰትና ስደት
ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ለስደት የሚነሳሱት በሀገር ውስጥ በሚኖር የኤኮኖሚ አማራጭ እጦት፤ በስልጣን ላይ የወጡ ኃይሎች ለደጋፊዎቻቸው ወይንም ለጥቅም ተጋሪዎቻቸው በሚያደርጉት አድሎአዊ አስራር እንዲሁም በነፃነት ተዘዋውሮ ለመስራት በተለያየ መንገድ በሚደረጉ ፖለቲካዊ ገደቦች ናቸው፡፡ ዜጎች በአማራጭ የሰራ በሕክምና ጥራት ደካማነት ምክንያት የሀገሪቱ ባለሀብቶችና የተሻለ የኢኮኖሚ ይዞታ ላይ የሚገኙ ዜጎች ለህክምና ውጭ ሀገር እየሄዱ የሚያጠፉትን የውጭ ምንዛሪ ለማስቆም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ዘመናዊ ሆስፒታሎች እንዲያደራጁ ማበረታታት።
3.5. ማህበራዊ ዋስትና
የማህበራዊ ዋስትና ለዜጎች መስጠት ለአንድ ሀገር ግዴታ መሆኑን በመረዳት፤ ዜጎች ይህን ለማድረግ የሚያስችል ተመጣጣኝ መዋጮ እንዲያደርጉ ይደረጋል፡፡ በፍላጎታቸው በሚያደርጉት መወጮ መሰረትም መብታቸው ሊከበርላቸው የሚችልበት ስርዓት ይዘረጋል፡፡ ማህበራዊ ዋስትና የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ከኢኮኖሚ እድገት ደረጃ ጋር እየተገናዘበ ማስተካከያና ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው በማህበራዊ ዋስትና ስም የግል ተቀጣሪ ሰራተኞች ገንዘብ እንዲያዋጡ፤ ነገር ግን በምንም መልኩ ተጠቃሚ የማይሆኑበት ስርዓት ግልፅነት ባለው አስራር እና ዜጎችን በሚጠቅም መልኩ ይለውጣል፡፡ ዜጎች ሁሉ ወጥ የሆነ የማህበራዊ ዋስትና መለያ እንዲኖራቸው በማድረግ ተጠያቂነት ያለው የማህበራዊ ዋስትና ስርዓት ይዘረጋል፡፡
3.6. ሴቶች
ኢዜማ ሴቶችን ያገለለ ማንኛውም ዓይነት ፖሊስ ውጤታማ እንደማይሆን ይገነዘባል፡፡ በተለይ የሴቶች በፖለቲካው መስክ መሳተፍ የራሳቸውን ጉዳይ በጥልቅ ያገናዘበ ፖሊስ ለመቅረፅ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን ያምናል፡፡ ትምህርት ለእኩል ተሣትፎ ወሣኝ መሣሪያ በመሆኑ ሴት ልጆች ከትምህርት ገበታ የሚያስቀሩ ማነቆዎችን በማስወገድ ዘላቂ የሆነ የሴቶች ተሳትፎን ለማረጋገጥ ይስራል፡፡ ሴቶች አሁን ያለው የፖለቲካ ምህዳር የፈጠረው አፈና ሲነሣ ሙሉ ሀይላቸውን ሊጠቀሙ የሚችሉበት ዕድል እንደሚፈጠር ኢዜማ ያምናል፡፡ ለይስሙላ ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል የሚደረጉ የሴቶች ተሳትፎን ኢዜማ አይቀበልም፡፡
3.7. ወጣቶች
በሀገራችን የሚታየው የወጣት ስራ አጥነት በግልፅ የሚያመለክተው፤ አገሪቱ ያላትን ወሣኝ የእድገት ምንጭ በአግባቡ መጠቀም ያለመቻሏን ነው፡፡ ይህን እምቅ የእድገት ምንጭ የሆነውን የወጣት ሀይል አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል፤ ይልቁንም ወጣቱን ከወላጆቹ ጋር በተጣበበ የግብርና መሬት ላይ የሚያደርገውን የመሬት ቅርምት በማላቀቅ ከግብርና ውጭ ባሉ የስራ እድሎች ተሣታፊ ለማድረግ የተቀናጀ የከተማ ልማት ስትራቴጂዎች ይቀረፃሉ፡ ፡
3.8. አካል ጉዳተኞች
በአሀገራችን ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የተለያየ የአካል ጉዳት ያላባቸው ፤ነገር ግን በአገር ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉ ዜጎች ይኖራሉ፡፡ አካል ጉዳተኞችን ከግምት ውስጥ ያስገባ የመስረተ ልማት ግንባታዎች ያለመኖር፣ አድሎዋዊ የስራ ቅጥርና ምደባ፣አስፈላጊው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አለመኖር፣ ወዘተ፣ ኑሮዋቸውን አስቸጋሪ ያደረገው መሆኑን ኢዜማ ይገነዘባል፡፡ ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመለወጥ የሚያስችል ዝርዝር ፖሊሲ ወጥቶ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
3.9. አረጋውያንና ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት
ተንከባካቢ የሌላቸው አረጋዊያን እንዲሁም ወላጅ ያጡ ህፃናትን መንከባከብ ለበጎ ምግባር በሚዘጋጁ ዜጎች ብቻ የሚተው ባለመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ህፃናትን ለልመና ተግባር ማዋል እንዲቀር የሚያደርግ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
3.10. ስነ ሕዝብን
የተመጣጠነ የህዝብ እድገት ለዘላቂ ልማት ወሣኝ መሆኑን በመገንዘብ ሀገሪቱ የምታስመዘግበውን እድገት በማይፃረር መልኩ፤ የስነ ህዝብ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ የህዝብ ቆጣራ ውጤቶች ከምንም ዓይነት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መንገድ እንዲከናወን እና ውጤቱም ለሰብዓዊ ልማት ብቻ የሚውል ይሆናል . ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች እና መንግስታት ጋር የምታደርገው ግንኙነት የራሷን ደህንነትና ጥቅም ለማስቀደም ቅድሚያ እየሰጠች በረጅም ጊዜ በጋራ ጥቅም፣ በእኩልነት፣ በመከባበር እና በእርስ በርስ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ባለመግባት መርሆች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፤
4.2. ጎረቤት ሃገሮችን በተመለከተ
4.2.1. ኢዜማ ከጎረቤት አጋራት ጋር የሚኖረን ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፣ ከጥርጣሬና ካአላስፈላጊ ውድድር ነፃ ሆኖ በጋራ መልማትና የቀጠናውን ሰላምን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ይስራል፡፡
4.2.2. የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን በአካባቢያችን እየተደቀኑብን ያሉትን ስጋቶች በሚገባ የተገነዘበ፤ ከዚሁ አንጻርም የአገራችንን የረጅም ጊዜ ጥቅምን በሚገባ ለማስጠበቅ የሚያስችል ይሆናል፡፡
4.2.3. ከዓለም አቀፍ ሕግጋትና ከታሪክ አንጻር አገራችን ራስዋ ባለቤት ሆና የምታስተዳድረው (sovereign ownership) የባህር በር እና መተላለፍያ (ኮሪዶር) የማግኘት መብት ሊኖረን እንደሚገባ ኢዜማ ያምናል፡ ፡ ከአካባብያችን እና ከሃገራችን ልዩ ሁኔታ አንጻር ሲታይ ደግሞ ይህን መብት የማሰከበር ጉዳይ የኢኮኖሚ እድገት ብቻ ሳይሆን የሃገር ደህንነት እና የሃገር ህልውና ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይህን በሠላማዊ፣ ህጋዊና እና ዲፕሎማሲያዊ መስመር ብቻ ተግባራዊ ለማድረግ ይሰራል፡፡
4.2.4. ኢዜማ ሀገራችን ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶችን በተለይ ደግሞ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብት እንዳላት ያምናል፤ ይህንንም ከአገሮች ጋር በስምምነት ለመፈፀም እና የትብብር እንጂ የግጭት መንስዔ እንዳይሆኑ አበክሮ ይስራል፡፡
4.2.5. ከጎረቤት ሃገራት ጋር የሚደረግ ግንኙነት የሚመራው ከሌሎች ሃገሮች ጋር በሚደረጉ መሰረታዊ መርሆዎች ሲሆን፣ከዚህ በተጨማሪ ግን የጎረቤት ሃገሮች በራሳቸውም ይሁን የሌሎች ሃይሎች መሳሪያ በመሆን በሃገራችን ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ አሳዳሪ መሆን ስለሚችሉ በሚገባ የታሰበበት በጥናትና ምርምር ላይ የተደገፈ በጥንቃቄ የሚያዝ ፖሊሲ ይቀረጻል፣
4.2.6. ከጎረቤት ሃገሮች ጋር የሚኖር ግንኙነት የየሃገራቱን ማንነትና ምንነት በሚገባ ያጠና፣ በቀላሉ ለጋራ ጥቅም መቆም የሚችሉትን፣ ለጋራ ጥቅም በጋራ ለመስራት የተለያዩ ችግሮች ያለባቸውን ሃገራት በመለየት ለእያንዳዳቸው የሚሆን ስትራተጂ የነደፈ ፖሊስ ተግባራዊ ይደርጋል፤
4.2.7. በአካባቢው መልካም ጉርብትናን በመፍጠርና በማቀራረብ በሁሉም ሃገራት የነበሩ የፖለቲካ ስርአቶች የፈጠሩትን የቁርሾ፣ የመጠራጠር ስሜት በማጥፋት፣ ለመልካም ጉርብትናው ዋስትና መሆን የሚችሉ የፖለቲካ የማህበራዊና የኢኮኖሚ እሴቶች የሚጋሩ በነዚህ እሴቶች ዙሪያ ሃገሮቻቸውንና ህዝቦቻቸውን በሁሉም መንገድ የሚያስተሳሰሩ፣ ከጋራ ኢኮኖሚ ግንባታ እስከ ጋር መከላካያ ለማቆም የሚዘልቅ የጋራ ጥቅም ማስከበሪያ ስትራተጂ ነድፎ እሰከ መንቀሳቀስ የሚወስድ ሩቅ አላሚ ፖሊሲ እንዲቀረጽና በስራ ላይ እንዲውል ይደርጋል፣ ኢዜማ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተለምዶ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተብሎ የሚጠራው፣ ከኢትዮጵያ ውጭ በሌላው አለም ተበትኖ የሚኖረው በአንድ ወቅት ምንጩ ኢትዮጵያ የሆነው ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ትውለደ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠራው ነው። ከሃገሩ የወጣበት ምክንያት የፈለገው ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌላም ይሁን፣ በፈለገው የተለያዩ ማህበረሰቦች፣ ቋንቋን ሃይማኖትን የሙያ ዘርፍ፤ ወዘተ ለይቶ በተከፋፋፈለ ሁኔታ በወጭ ሃገራት እየተሰባሰብ ወይም ተበትኖ ይኑር፣ በአንድ ወቅት ምንጩ ኢትዮጵያ እስከሆነ ድረስ የአገራችንን ችግር ለማቃለልና ወደ ተሻላ ሁኔታ ላይ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማድረግ ትልቅ ሀይል ነው ብሎ ኢዜማ ያምናል።
የፖለቲካ ፍልስፍናውን ማህበራዊ ፍትህ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊ ፓርቲ፤ የፓርቲውን ፕሮግራም በሚገባ ለማስፈጸም ዝግጁ የሆነ ፓርቲ በአገር ውስጥ ከተፈጠረ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ትልቅ ድጋፍ ሊሰጥ የሚችሉ በመሆናቸው ተገቢው ትኩረት ሊሰጣቸው እና ግልፅ ፖሊሲ ሊወጣላቸው እንደሚገባ ያምናል። ኢዜማ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከት ግልፅ ፖሊሲ ሊኖረው የግድ የሚያደርገው በውጭ ያሉት
አባላቱና ደጋፊዎቹ የሚመኙትን፤ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊና የበለጸገች ሃገር ለማድረግ በብዙ ዘርፎች ወሳኝ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ሰለሚያውቅ ነው።
ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአብዛኛው እንደሚታሰበው ተንደላቀው እና በምቾት የሚኖሩ አድርጎ መሳል ሰህተት ነው፡፡ እጅግ ብዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአስከፊ ሁኔታ በሰው አገር እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ አብዛኞቹ የሚኖሩት ዴሞክራሲ በዳበረባቸው ሃገሮች ነው። በነዚህ ሃገሮች በመኖር ብቻ ሰብአዊ መብት፣ የሚድያና የግለሰቦች ነጻነት፣ የህግ የበላይነትና የፍትህ ሚዛናዊነትን ለመረዳት፣ በዚህ መንገድ በሰለጠነ ሁኔታ፣ የተረጋጋና የበለጸገ ሃገር ፈጥረው በሚኖሩ ሕዝቦች እንዲቀኑ ተደርጓል። “ምነው ኢትዮጵያም እንዲህ የሞላላት ሃገር ብትሆን” ብሎ የማይቀና ትውልደ ኢትዮጵያዊ አይኖርም። ይህ ማለት የተሳትፎው ጉዳይ ቢለያያም በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሃገራችን ነጻነት፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ የሰፈነበት ሃገር እንድትሆን እስካሁን ያደረጉት ትግልና የከፈሉት መስዋእትነት ወደፊትም የሚኖራቸው አስተዋጸኦ ቀላል አይሆንም። ሰለዚህ በሚኖሩበት አገራት ያካበቱትን ልምድ፣ እውቀትና ሀብት ከአገራቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ፣ ድጋፋችን ለሚሹ በችግር ላይ ላሉትም ተስፋ የሚሰጥና የሚደግፍ፤ ሁሉን አቀፍ የሆነ ምቹ የፖለቲካ፣ የኤኮኖሚ እና ማህበራዊ ተሳትፎ ሊያደርጉ የሚችሉበት ፖሊሲ ኢዜማ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ፖሊሲው በሁሉም ደረጃ ግብዓት እንዲያገኝ ጥልቅ ውይይት ይደረግበታል፡፡
Filed in: Amharic