>

ዶ/ር አብይ የያዙት ክህነታዊ አመራር ወይስ መንግስታዊ አመራር???" (ዶ/ር ተድላ ገ/ዮሀንስ)

ዶ/ር አብይ የያዙት ክህነታዊ አመራር ወይስ መንግስታዊ አመራር???”

ዶ/ር ተድላ ገ/ዮሀንስ – በሀሪሰን ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ፕሮፌሰር
(በ  እንዳለ ከተፎ)
እኚህ የፍልስፍና ምሁር እውነታውን ዓለም የሚያዩት እቢሯቸው ቁጭ ብለው በፍልስፍና መንፅር ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በክፉም በደጉም ለውጥ እየተካሄደ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። በለውጥ ማግሥት ደግሞ መልካም ነገሮችም ባለፈው ክፉ ሥርዓት የተተከሉ መጥፎ ክስተቶችም ይኖራሉ እያየን ነው።
 ጥሩ ፍሬ ብቻ ሊሆን አይችልም ። በደርግና በወያኔ ዘመን እንዳየነው የአንድ ወገን አመለካከትን ለማስረፅ ሌሎችን ሁሉ በሀይል ለማፈን ተችሎ ይሆናል። ያ ዓይነቱ አካሄድም እንዳልሠራ ከደርግ 17 ዓመት እና ከወያኔ 27 ዓመት ክፉ የአፈናና የፈላጭ ቆራጭ ሥርዓቶች አይተናል። በነዚህ ሁለት ክፉ ሥርዓቶች የነበረው የግፍ አገዛዝ ነው ህዝባችን ግፉ ከሚቋቋመው በላይ ሲሆን በቃኝ ብሎ ተነስቶ ይህንን አሁን የተገኘውን እንፃራዊ ለውጥ ሊያመጣ የቻለው። እናም ለውጥ መጥቷል። ጥያቄው ይህንን ለውጥ እንዴት እናስቀጥለው ነው። እንደቀድሞዎቹ አገዛዞች በክርንና በቡጢ ወይስ በመቻቻልና በመማማር? መንግሥት ኮሽ ባለ ቁጥር እየተደናገጠ ወደ ሀይል እርምጃ የሚሯሯጥ ከሆነ ወደ እምባጉነነት የመለወጥ አደጋ ሊኖር ስለሚችል የሚመረጥ አይደለም። ስለሆነም ብልህ ልጅ የስጡትን እየበላ ለተጭማሪ ያለቅሳል እንደሚባለው እስካሁን የተገኘውን የለውጥ አየር ሁላችንም መንከባከብ አለብን። ሥራውን ለመንግሥት ብቻ ትተን ህፀፅ መጠቆም ብቻ ሳይሆን እኔ በግል ለለውጡ ምን አስተዋጽኦ ማድረግ እችላለሁ ብሎ ማስብ ያስፈልጋል።
 ልክ ነው የመንግሥትን ድክመቶች መጠቆም ባግባቡና ጠቃሚ በሆነ መንገድ ተገቢ ነው፤ ባንፃሩ በትንሹም በትልቁም መንግሥትን ለማብጠልጠል መቻኮል ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። እርግጥ የህግ የበላይነት መከበር አለበት። ለዚያም ቢሆን በየመንደሮቻችን ለግል ጥቅም የሚሽሎከሎኩ ህግ ተላላፊዎችን ከመንግሥት ጎን ሆነን ካልተከላከልን መንግሥት ብቻውን የሚያደርገው ነገር በቂ ላይሆን ይችላል። ደርግ ለመጥፎ ነገር ተጠቀመበት እንጂ ህዝቡን የእብዮት ጠባቂ ብሎ እስከ ቀበሌና ገበሬ ማህበር ድረስ ወርዶ በማስታጠቅ አድራጅቶት ነበር። ግን እንዳለመታደል ሆኖ ህዝቡን እርስ በርሱ አጫርሶታል።
እንደዚህ ህዝቡን በማሳሪያ ሳይሆን በመልካም ሀሳብ ዙሪያ በማደራጀት ባካባቢው ከሚገኘው የህግ አስከባሪ ሀይሎች ጋር በመተባበር የራሱን ሰላም ራሱ የሚያስጠብቅበት ሥርዓት ቢዘረጋ መልካም ይሆናል እላለሁ። እድርን  በመሳሰሉ በተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት ህዝቡን አደራጅቶ መጠነኛ መንግሥታዊ ድጋፍ በማድረግ ደህነታቹውን ራሳቸው የሚያስከብሩበትን ህግና ሥርዓት መፍጠር ከባድ ይሆናል ብዬ አላስብም።
Filed in: Amharic