>

ትግራይ ውስጥ ያሉት ድብቅ እስርቤቶች መቼ ነው በፌደራል መንግስቱ የሚፈተሹት? (ቬሮኒካ መላኩ)

ትግራይ ውስጥ ያሉት ድብቅ እስርቤቶች መቼ ነው በፌደራል መንግስቱ የሚፈተሹት?
ቬሮኒካ መላኩ
ጠ/ሚ ዐቢይ ወደተለያዩ ሀገራት ሄደው ሲመለሱ እስረኞችን አስፈትተዋል። በቀደም ከሱዳን ሲመለሱም በተመሳሳይ ካስፈቷቸው እስረኞች ጋር እንደተመለሱ ተዘግቧል። ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነበር።
ዛሬ ወደ ትግራይ አቅንተዋል። ሕወሓት በተለይ ከ1982 ዓም ጀምሮ ከ2000 በላይ ዜጎችን ድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ አስሯል። በርካቶች የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው በድብቅ እስር ቤት እየማቀቁ መሆኑን በቅርብ የወጡ መረጃዎች ሳይቀር አመላክተዋል።
 ፀለምት የሚባል የዋሻ እስር ቤት በትግል ወቅት ጀምሮ ታጋይም ሆነ በደርግ የተያዙ ባለስልጣናት ከዚሁ እስር ቤት የእባብና የጊንጥ መጫወቻ ሆነው አልቀዋል። ይኸ እስር ቤት ዛሬም በትግራይ ድንበር  አካባቢ ያሉ ራያ አላማጣን ጨምሮ  ማጎረያ ሆኖ አሁን ድረስ ማሰቃያ ቦታ ሆኖ ቀጥሏል።
እንደማሳያ  በፎቶው የሚታዩት ሊቁ እንደስራቸው አግማሴ ናቸው። የእኚህ አባት አቤቱታ ጠ/ይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከደረሰ ቆይቷል።
ከሳውዲ፣ ከግብፅ፣ ከሱዳን እስረኞችን ያስፈቱት ጠ/ሚ ትግራይን እስረኞቹን ፍች ብሎ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን እንደ ስልጣናቸው እንድትፈታ ማስገደድ ነበረባቸው! እስካሁን በዚህ ጉዳይ ጠንካራ አቋም አልወሰዱም።   ጠ/ሚ ዐቢይ ትግራይ ውስጥ የሚገኙትን ከ2000 በላይ እስረኞች መቼ ነው የሚያስፈቷቸው?
Filed in: Amharic