>
8:42 am - Tuesday July 5, 2022

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ለቀብር መቀሌ በሄዱበት ታሰሩ!!! (ኢሳት)

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ለቀብር መቀሌ በሄዱበት ታሰሩ!!!
ኢሳት
ወንበዴው ና በቀለኛው ህወሓት ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀመባቸውና ባዶ ስድስት (06) በሚባል ማሰቃየ እንደታሰሩ ታውቅዋል። ዶ/ር አረጋዊ ለጄነራል ሰዓረ መኮንንና ለሜጀር ጀነራል ገዛዒ አበራ ቀብር መቐለ እንደተገኙም ታውቅዋል። የጀነራል ሰዓረ መኮነን የቅርብ አማካሪ ነበሩ።
 ሹፌራቸውንም አስገድደው የተመረዘ መጠጥ በማጠጣታቸው በካባዱ ታሞ መቐለ ሆስፒታል ይገኛል። መኪናቸውንም የህወሓት ቅጥረኞች ጎማውን አውልቀው በመሰባበር ከፍተኛ ጉዳት እንዲርስበት አድርገዋል።
 የስብሃት ነጋ ህወሓት በጀነራል ሰዓረ መኮነን ና በጀነራል ገዛኢ አበራ ህልፈተ ሞት ትግራዎይ በመሆናቸው ነው የተገደሉት በማለት በህዝባችን ላይ ጦርነት ታውጆብሃል በማለት ሽብር እየፈጠሩ እንደሆነ ታውቅዋል።
 እነዚህ የሀገራችን ጀግኖች የተሰውት በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያዊነታቸው መሆኑ ቤተሰቦቻቸውም ይሁን የስራ ባለደርቦቻቸው ምስክረነታቸውን ሰጥተዋል።
ይባስ ብሎም የስብሃት ህወሓት “ከሃዲ ባንዳ” በማለት የስም ማጥፋትና ለማሸማቀቅ ይሰሩ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው እውነት ነበር። ይባስ ብሎም ቤተሰቦቻቸውን ለመበተን ወንበዴው ህወሓት ይሰራ እንደነበር ምስክሮች የቃል እምነታቸውን ሰጥተዋል።
 የዶር አብይ መንግስት ይህን የወንበዴው አፈና በአስቸኳይ በህግ ሊያስቆማቸው ና ወንጀል ፈፃሚዎች በህግ ሊጠይቅ ይገባል።
 ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው።
Filed in: Amharic