>

የኦሮሞ ንቅናቄ  (ወረራ) በመቶ ዓመት ውስጥ የአማራና የሌሎች ነገዶችን ስምና ባህል ለውጧል! (ታደለ ጥበቡ)

ኦሮሞ ንቅናቄ  (ወረራ) በመቶ ዓመት ውስጥ የአማራና የሌሎች ነገዶችን ስምና ባህል ለውጧል!
ታደለ ጥበቡ
 
* ጥንታዊ የአማራ ክፍላገሮች ስያሜ…..
*ትውልድ በወፍ ዘራሽ ፈላስፎች እንዳይደናገር በመረጃ አስደግፈን መራራውን ሃቅ እንጽፋለን።የምጽፈው ውነታውን ነው ትክክል አይደለም የሚል ፊደል የቆጠረና በምክንታያዊነት የሚያምን ሊሞግተን ይችላል።
*ጥንታዊ የአማራ ክፍላገሮች ስያሜ የተቀየሩት በ2 መንገድ ነው በወረራና ምክንያታዊነትን ተከትሎ በሕዝብ ፈቃድ።
*በወረራ ከኦሮሞ ንቅናቄ በፊት ነባር ስም የነበራቸው እና ኦሮሞዎች ወደ መሀል አገር በዝለና ከገቡ በኋላ ስማቸው ተውጦ የቀሩ አካባቢዎች አሉ።የኦሮሞ ንቅናቄ የጀመረው በ1520 ዓ.ም.ከባሊ ነው።የገናሌን ወንዝ ተሻግረው።ንቅናቄው ለመቶ አመት እስከ 1620 ዓ.ም.ቆይቷል።በመቶ ዓመት ውስጥ የአማራና የሌሎች ነገዶች ባህል ተውጧል፤ቅርስ ወድሟል፤የአካባቢ ስሞች ተቀይረዋል።
*በ1508 ዓ.ም.ወደ ኢትዮጵያ የተላከው
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ  በኢትዮጵያ ያደረገውን የ6 ዓመት ቆይታ (ከ1513-1519 ዓ.ም.) “The prester John of the Indies” በሚል ርእስ ጽፎታል።አልቫሬዝ በዚህ የጉዞ ዘገባው ውስጥ ካነሣቸው ነገሮች አንዱ ከኦሮሞ ወረራ በፊት  የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገሮችን  የሚያሳይ ካርታ አዘጋጅቷል።ከዚህአኳያ፣፦ጎጃም፣በጌምድር፣ደምብያ፣በለሳ፣ጣና፣ሸዋ፣መንዝ፣ቡግና፣ዋግ፣ዶባ፣አገው፣አንጎት፣አምሐራ፣ቢዛሞ፣ጋፋት፣ዳሞት፣ጉራጌ፣ሃዲያ፣ባሊ፣ወጅ፣ፈጠጋር፣ዳዋሮ፣ይፋት፣ወለቃ፣አዳል…እያለ ይዘረዝራል።ከተጠቀሱት መካከልዶባ፣አንጎት፣ቢዛሞ፣ጋፋት፣ዳሞት፣ባሊ፣ወጅ፣ፈጠጋር፣ዳዋሮ፣ይፋት፣ወለቃ እና አዳል ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ስማቸው ተቀይሯል እንደ ጋፋት እና ዳሞት ያሉ ሕዝቦች በኦሮሞ ጭራሹን ጠፍተው ቀርተዋል።
የቀድሞ ስያሜ     የአሁን ስያሜ
==========       ========
1.ባሊ                  ባሌ
2.እናርያ             ኢሉአባቦራ
4.ገንዝ               ጅባት እና ሜጫ (ምዕራብ ሸዋ)
5.ግራርያ            ሰላሌ (ሰሜን ሸዋ)
6.እንደጥና          እንጦጦ፣ጉለሌ እና የካ
7.ኦ(ወ)ይጃ        የረርና ከረዩ (ምሥራቅ ሸዋ)
8.ገሙ                ጅማ
9.ቢዛሞ             ቄለም (ምዕራብ ወለጋ)
10.ዳሞት           ሌቃ (ምሥራቅ ወለጋ)
11.ፈጠጋር          አርሲ
12.ደዋሮ            ጭሮ (ምዕራብ ሐረርጌ)
13.ሽምብራ ኩሬ     ሞጆ
14.ደብረ ዘይት        ቢሾፍቱ
15.ናዝሬት               አዳማ
16.በረራ               አዲስ አበባ
17.ሴዋ                ሽዋ
18.ደብረ ኤባ        ደብረ ብርሃን
19.ኤፌሶን              አጣዬ
20.ምድረ ገኝ         ከሚሴ
21.ቤተ ሳባ            ወረሂመኖ
22.ቤተ-ጊዮርጊስ    ወረኢሉ
23.ወለቃ                ቦረና
24.ጭቃ በረት          ባቲ
25.ቢራሮ                ቃሉ/ኮምቦልቻ
26.ላኮመልዛ           ወሎ (ቤተ አማራ)
27.አንጎት                ራያ
28.ገነቴ                  የጁ
29.በጌምድር          ጎንደር
30.ሰማራ                ደብረ ታቦር
31.ግዮን                ጎጃም
32.መንቆረር            ደብረ ማርቆስ
33.ወጀት                ፍኖተ-ሰላም
34.ኤዶም              ሰከላ
*ከላይ ከጠቀስናቸው መካከል ለምሳሌ ደብረ ኤባ፣መንቆረርና ሌሎችም በነገሥታቶችና በሕዝቡ የተቀየሩ ስያሜዎች ናቸው።የተቀሩት ከኦሮሞዎች ወረራ ወዲህ የተለወጡ ናቸው።
*ዳሞት ወለጋን፥ ምዕራብ ሸዋን ይዞ ከዓባይ በስተደቡብ፤በምዕራብ እስከ ዴዴሳ፤በደቡብ እስከ ወላይታ የተንጠለጠለ ግዛት ነበረ።
*እናርያ ፦ የዛሬው ኢሉአባቦራ  የጊቤ ወንዝ ከሚመነጭበት ቦታ ላይ የሚገኘው ግዛት እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ “ጊቤ እናሪያ”ይባል ነበር።በአሁኑ ጊዜ ሊሙ እናርያ የሚባል አካባቢ አለ።በኋላ ዘመን የከፋ ንጉሣዊ ግዛት ከሆነው ሥፍራ በስተደቡብ የነበረው ግዛት እናሪያ ነው።የዳሞቱ ንጉሥ ሞተለሚ በይኩኖ አምላክ ድል ሲሆን የሸሸው ወደ እናሪያ ነበር።(Taddesse Tamarat,church and state፣177,No.11)
*ቤተ-ጊዮርጊስ ፦የወረኢሉ ጥንታዊ ስሟ ነበረ።ከኦሮሞዎች ወረራ በኋላ ግን ወረኢሉ ተባለች።ወረኢሉ የዐማራ ነገዶችዋና ነገሥታቶች ዋና   ስትራቴጂካዊ ቦታ ነበረች።ዛሬ  ወረኢሉ “ድርማ”ከሚባል ቦታ ላይ የዐፄ ገላውዴዎስ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽ ይገኛል።በቤተ-ጊዮርጊስ የሚታወቁ ሚያት፣ወሰት እና አሰለል የሚባሉ ጥንታዊ ስሞች አሉ።ወደ አምሐራ ለመግባት 5 ጥብቅ በሮች ነበሩ።የመጀመሪያ በወለቃ በኩል፣ሁለተኛው በእህያ ፈጅ በኩል፣ሦስተኛው በመንዝ በኩል ፣አራተኛው በግደም ውስጥ ባለው በሚያት በኩል (በወረኢሉ አጠገብ)፣አምስተኛው ደግሞ በወሰት በኩል (ማለትም በመካነ ሥላሴ አጠገብ በአሰለል መሻገሪያ) ነበሩ።(The conquest of Abyssinia፣46,note)
*ወለቃ፦ማለት የጥንቱ የአምሐራ ምድር ዋና ቦታ ነበር።የንጉሥ ሰይፈ አርእድ መቀመጫ ከተማውም ነበረች። ወለቃ በአሁኑ ጊዜ በደቡብ ወሎ ቦረና የሚባለውን አካባቢ የሚያካልል ሰፊ ግዛት ነበር።ወለቃ የሚለው ስም መጀመሪያ በመዝገብ ላይ የተገኘው በ15ኛው መክዘ በተጻፈው የአባ  ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገድል ላይ ነው።ስሙን ወደ ቦረና ሲቀይር ጥንታዊ ስሙን ለዓባይ ገባር ለሆነው ወንዝ አውርሶታል።በተለይም በመካከለኛው ዘመን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት ተሠርተውበት ነበር።ኢትዮጵያን “ብሔረ ኢትዮጵያ”እያሉ የሚጠሯት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የነበረበት ደብረ ነጎድጓድ የተሰኘው ትምህርትቤትም የነበረው በወለቃ ነው።ከሸዋ ጋር በዠማ ወንዝ ከጎጃም ጋር በዓባይ ወንዝ የሚዋሰነው ወለቃ ለጎጃም፣ለጎንደርና ላኮመልዛ መገናኛ ነበረ።በ17ኛው መክዘ ጨቃታ የሚባሉ ኦሮሞዎች አካባቢውን ሲይዙት ወለቃ የሚለው ስሙ ቀርቶ ቦረና ተባለ።
(ዳንኤል ክብረት,ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፣596-597,Encyclopedia Aethiopica vlo.iv,p.1081-1082)
*አንጎት፦አንጎት በቤተ አምሐራና በላስታ መካከል የነበረ ጥንታዊ ግዛት ነው።ሐይቅ አንዳንዴ በአንጎት ሌላ ጊዜ በአምሐራ ትካለል ነበር።.አንጎት በዛሬው ሰሜን ወሎ የሚገኘው ራያ ነው።አንጎትን ያጠፋት  ሐርሙፋ  ቀጭኖ የተባለ ኦሮሞ ነበር።
Filed in: Amharic