>

የኦሮሞ ገዳ፡ የቀማኞች ዲሞክራሲ (መስፍን አረጋ)

የኦሮሞ ገዳ፡ የቀማኞች ዲሞክራሲ

‹‹አራተኛው ሉባ ቢፎሌ ይባላል፡፡ ደዋሮን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ፈጠጋርን መውጋት የጀመረው እሱ ነው፡፡ ምርኮኞችን እያጋዘ አገልጋዮች በማድረግ ገርባ አላቸው፡፡››

አባ ባሕርይ፣ ዜናሁ ለጋላ፣ ክፍል 8

 

 

ነጻነት ሰይፍ ነው ባለ ሁለት ስለት
አንገት እየቀላ የሚቆርጥ ሰንሰለት፣
ሰንሰለቱን ሲቆርጥ አንገት እንዳይቀላ
ሊያዝ ይገባዋል በዘዴ በመላ፡፡

ገበናው ሲሸፈን ሲታይ በቁሙ
ከሰው ቢፈረጅም በሥጋ በደሙ፣
በደም የሚደሰት የሚረካ ጥሙ
እንስሳ ከሆነ የባሕሪ ወንድሙ፣
የነጻነቱ ልክ የመብቱ ደረጃ
መብለጥ የለበትም ከሚሰጥ ለጥጃ፡፡

መስፍን አረጋ

 

መንደርደርያ


ይህ ‹የኦሮሞ ገዳ፣ የቀማኞች ዲሞክራሲ›› የሚል ርዕስ የሰጠሁት ጦማር ከሦስት ወራት በፊት (June 11, 2019 ) ኢትዮጵያ ነገ (ethiopianege.com) በተሰኘ ድርጃዳ (website) ላይ በተመሳሳይ ርዕስ ካወጣሁት ጦማር በትንሹ የተሻሻለ ሲሆን፣ ‹‹የኦሮሞ ሥርዓትና ዲሞክራሲ ምንና ምን ናቸው?›› በሚል ርዕስ አቶ አቻምየለህ ታምሩ (ethioreference.com) በቅርቡ ከጦመረው ጦማር ጋር ይዛመዳል፡፡

አቶ አቻምየለህ የኦሮሞ ገዳ ዲሞክራሲ አይደለም ሲል፣ እኔ ደግሞ አቻምየለህን በመቃረን የኦሮሞ ገዳ ዲሞክራሲ ነው እላለሁ፡፡ ዲሞክራሲነቱ ግን እውነተኛ ዲሞክራሲ ሳይሆን የቀማኞች ዲሞክራሲ ነው፡፡ ምክኒያቶቸን ልተንትን፡፡

የቀማኞች ዲሞክራሲ

ቀማኞች ሲቀማኙ እጅና ጓንት ናቸው፡፡ ዓይናቸውን የሚጥሉት በቅምኝቱ ቱርፋቶች ላይ እንጅ በቅምኝቱ ላይ ስላልሆነ፣ ቅምኝቱን ለማሳካት ማድረግ /የሚገባቸውን/ ሁሉ በሙሉ ስምምነትና ትብብር ያደርጋሉ፡፡ የቅምኝቱን አመራሮች የሚመርጡት ደግሞ የቅምኝቱን ቱርፋቶች አመርቂ ለማድረግ ሌት ተቀን ይተጋሉ ብለው ሙሉ በሙሉ የሚያምኑባቸውን ግለሰቦች ብቻና ብቻ ነው፡፡ ማናቸውም የቅምኝቱ አመራር አባል ደግሞ የቅምኝት ሚናውን በሚገባ ካልተወጣ /የሚጎዳው/ እሱ ራሱ በመሆኑ፣ ቦታውን ከሱ ለተሻለ ግለሰብ ለመልቀቅ ደስተኛ ነው፡፡ ማናቸውም የቅምኝቱ ዐባል ደግሞ ቅምኝቱን አመርቂ ለማድረግ ይበጃሉ የሚላቸውን ሐሳቦች የመግለጽ ሙሉ ነጻነት ብቻ ሳይሆን፣ እንዲገልጽም በእጅጉ ይበረታታል፡፡

ቅምኝቱ ከተከናወነ በኋላ ግን አብዛኞቹ የቅምኝቱ አባሎች በቅምኝቱ ቱርፋቶች ክፍፍል ቅር ይሰኙና በቅምኝቱ ወቅት የነበረው ፍቅር ወደ መናቆር ይለወጣል፡፡ በክፍፍሉ እጅግ የተጎዱት በክፍፍሉ እጅግ በተጠቀሙት ላይ መሣርያ እስከማንሳት ይደርሳሉ፡፡ ተጠቃሚወቹ ደግሞ ጥቅማቸውን የሚያስከብር ድርጅት አቋቁመው በዘረፉት ልክየለሽ ሐብትና ንብረት አማካኝነት የበላይነት ይይዙና በሐብታሞች፣ ለሐብታሞች፣ የሐብታሞች የሆነ ስርዓት ይመሠርታሉ፡፡ የዚህ ስርዓት ዋና ተግባር ደግሞ ለግል ሐብት ከሚገባው በላይ አጽንኦት በመስጠት የዋኖቹን ቀማኞች የቅምኝት ቱርፋቶች መጠበቅና ማስጠበቅ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ስርዓቱ በይበልጥ የሚያተኩረው በቅምኝቱ ክፍፍል እጅግም ያልተጠቀሙት የቅምኝቱ አባሎች እድላቸውን እየረገሙ ከፍፍሉን አሜን ብለው እንዲቀበሉ የሚያስገድዱ ሕጎችን በመሐገግና ሕግ አስከባሪውን ኃይል በማጠናከር ነው፡፡ አስገዳጆቹ ሕጎችና ደንቦች እየሰፉና እየጠነከሩ ሲሄዱ፣ በቅምኝቱ ወቅት የሰፈነው ነጻነት እየጠበበና እየተዳከመ ይሄድና በጊዜ ሂደት ወደ ሙሉ አምባገንነት ይለወጣል፡፡

የሆነ ዓላማን ለማሳካት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ በጊዜያዊነት የሚያገለግል፣ ዓላማው ከተሳካ በኋላ ወደ ሙሉ አምባገነንነት የሚለወጥ ዲሞክራሲ የቀማኞች ዲሞክራሲ ይባላል፡፡ የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ የኦሮሞ ገዳ የሚባለው ሥርዓት ኦነጋውያን እንደሚሉት እውነተኛ ዲሞክራሲ ሳይሆን፣ ባሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለተከናወነው መጠነ ሰፊ ቅምኝት እንዲያገለግል ብቻ በጊዜያዊነት ከተሠረተ በኋላ ቅምኝቱ /ሲገታ/ ወዲያውኑ የከሰመ የቀማኞች ዲሞክራሲ እንደነበር ማስገንዘብ ነው፡፡

የኦሮሞ ገዳ

ኦሮሞ ከመነሻው ፈልሶ፣ በጦቢያ ላይ ተስፋፍቶ፣ ግብርና ተምሮ በቋሚነት ከመስፈሩ በፊት አርብቶ አደር የነበረ በመሆኑ፣ ከኗኗሩ ምንነት የመነጨ ነጻነት የሚመስል መረን ለቀቅነት ወይም ልልነት ነበረው፡፡ ዘላን የተባለበትም ምክኒያት ባሻው ጊዜ ወዳሻው ቦታ ስለሚዘል ነው፡፡ የከብት ጭራ የሚከተል አርብቶ አደር፣ በሬ እንደሚጠምድ አርሶ አደር ጥብቅ ሊሆን አይችልም፣ መሆንም የለበትም፡፡ አርብቶ አደራዊ ኑሮ የሚኖሩ ወይም ደግሞ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይኖሩ የነበሩ ብሔረሰቦች አኗኗራቸው በተወሰነ ደረጃ ልቅ መሆኑን ለመረዳት ያፋሮችን፣ የኢሳወችን፣ የሱማሌወችን፣ የከረዩወችን፣ የቦረናወችን ልቅ አኗኗር ከደገኛው ጦቢያዊ ጥብቅ አኗኗር ጋር ማነጻጸር ይበቃል፡፡

ሙሐመድ ሐሰንን የመሳሰሉ የኦሮሞ ልሂቆች ግን የኦሮሞን ከዘላንነት የመነጨ መረን ለቀቅነት ከዲሞክራሲ ጋር ሥራየ ብለው ያምታቱታል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የኦሮሞ ብሔረሰብ ከሌላው ጦቢያዊ በተለየ መልክ ዲሞክራቲክ ነበር በማለት በብዙ ረገዶች (በስነቃሎች፣ በጽሑፍነክ ትውፊቶች ወዘተ.) የሚሰማቸውን ባዶነት ለመሙላት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ደግሞ ኦሮምኛ የማያውቀው አስመሮም ለገሰ በኦነጋዊ ባልደረቦቹ የተተረጎመለትን የገዳ ትርክት ተሳስቶ (ወይም ሆን ብሎ) ወደ ዲሞክራሲ ትርክት በመቀየር የጻፋቸው ጽሑፎች ያንበሳውን ሚና ተጫውተዋል፡፡

የገዳ ስርዓት የኦሮሞ መስፋፋትና መንሰራፋትን ለማሰለጥ (make efficient) ብቻና ብቻ የተሰረተ የቀማኞች ዲሞክራሲ ነበር፡፡ በሌላ አባባል የገዳ ስርዓት በዲሞክራሲ የሚያምን ሕዝብ የሰረተው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሆን፣ በቀማኛነት ለመስፋፋት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ መስፋፋቱ እስከቀጠለ ድረስ እንዲያገለግል የተሰረተ የተስፋፊ ቀማኞች ዲሞክራሲ ነበር፡፡ የገዳ ስርዓት የተሰረተው 1522 ዓ.ም ገደማ (ማለትም በ 1515 የተጀመረውን የግራኝ ወረራ ተከትሎ) እንደነበር ራሱ ሙሐመድ ሐሰን ‹‹ኦሮሞና የጦቢያ ክርስቲያናዊ ንጉሥጌ›› (Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia) በተሰኘው በራሱ መጽሐፍ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ ትክክል ነው፡፡ የገዳ ስርዓት ከኦሮሞ መስፋፋት በፊትም ሆነ በኋላ አልነበረም፡፡ ስለዚህም የገዳ ስርዓት የኦሮሞን ሕዝብ ዲሞክራሲያዊነት የሚያመለክት ልዩ ክስተት ሳይሆን ቀማኞች ቅምኝታቸውን ለማቀላጠፍ የሰረቱት የቀማኞች ዲሞክራሲ ነው፡፡

የቀማኛ ዲሞክራሲ አመራሮች የሚመረጡት የቅምኝቱን ቱርፋቶች አመርቂ ለማድረግ በተቻላቸው መጠን የሚተጉ መሆናቸው ሙሉ በሙሉ ሲታመንባቸው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም አቶ አቻምየለህ በትክክል እንዳስቀመጠው ለገዳ ስርዓት አመራርነት የሚታጩት ቅምኝቱን በተመለከተ ምንም ዓይነት ቅሬታ፣ ማቅማማት ወይም ማመንታት ይኖራቸዋል ተብለው ሊጠረጠሩ የማይችሉት በሺ የሚቆጠሩ እውነተኛ ኦሮሞወች (ቦረናወች) እንጅ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የሞጋሳና የጉዲፈቻ ውጤት የሆኑት ገርባወች አይደሉም ማለት ነው፡፡ አባ ባሕርይ በመጽሐፋቸው መግቢያ ላይ እንደገለጹት፣ የኦሮሞ መስፋፋት የተከናወነው ሰውን ለመግደል እንበለ እንቅልፍ ቀን ከሌት በሚተጋ፣ የሆዱ አውሬ (ኮሶው) እንደ እንስሳ በቋንጃው ላይ በሚፍለከለክ፣ የእንስሳነት ባሕርይ በተጠናወተው አረመኔ ሠራዊት ነው፡፡ ተገዶ ገርባ የሆነ ግለሰብ ደግሞ የገዛ ወገኖቹን ለመጨፍጨፍ እስከዚህ ድረስ አይተጋም፡፡

በቱርክ ነፍጠኞች የተመራው የግራኝ አህመድ ወረራ፣ አማራ የሚባለውን ጀግንነቱ የተመሠከረለትን ታላቅ ሕዝብ ተቋማት ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በማፈራረስ እጅጉን አዳከመው፡፡ የሱማሌን ጅራፍ ይሸሹ የነበሩት የኦሮሞ አርብቶ አድሮች ደግሞ ግራኝ የፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ባባ ገዳወቻቸው መሪነት ድንገተኛ አደጋ እየጣሉ፣ በሐይማኖቱ ቀናኢ የነበረውን አማራ ስምንተኛው ሺ ደረሰ እስከሚያስብሉት ድረስ ሴት፣ ወንድ፣ ሕፃን፣ አዛውንት ሳይሉ በሰይጣናዊ ጭካኔ ጨፈጨፉት፡፡ የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር ነውና፣ የነዚህ አንድም ቀን ፊት ለፊት ተዋግተው የማያውቁ ቱርቂወች ብትር ከግራኝ ብትር የከፋበት አማራ፣ ከግራኝ ቁስል እስከሚያገግም ድረስ ምርጫ ስላልነበረው እጅግ ሰፊና ለም ከነበረው ርስቱ እየተፈናቀለ ከኦሮሞ አደጋ ጣዮች ራሱን በቀላሉ ለመከላከል ወደሚችልባቸው ተራሮች በመሸሽ ዝንጀሮቴኔ ኑሮ ለመኖር ተገደደ፡፡

አደጋ ጣዮቹም አማራውን እግር በግር እየተከተሉ፣ ያማራውን ምድር በየጎሳቸው በመከፋፈል ወረምንትስ፣ ወረቅብጥርስ እያሉ ሰየሙት፡፡ የአማራ አገር ፈጠጋር (አሩሲ)፣ የአማራ አገር እናርያ (ወለጋ)፣ የሀድያ አገር ዳዋሮ (ጨርጨር)፣ የጃንጀሮ አገር ገሙ (ኢሉባቦር)፣ የአገው አገር አንጎት (ራያ)፣ ያማራ አገሮች መካነ ሠላም (ቃሉ)፣ ሠገነት (ወረሂመኖ)፣ ዋሰል (ወረኢሉ)፣ ቤተሳባ (ወረባቦ)፣ ገነቴ (የጁ)፣ ምድረገኝ (ከሚሴ)፣ ላኮመልዛ (ወሎ)፣ ግራርያ (ሰላሌ)፣ ገንዝ (ጅባትና ሜጫ)፣ ወጂ (ወንጂ)፣ ሸምብራ ቁሬ (ዱከም)፣ በራራ (ፊንፊኔ) እየተባሉ እርምንና (ኢክርስትና) ተነሱ፡፡

አማሮች ነፍጥንና አነፋፈጥን ከፖርቱጋሎች ተምረው ግራኝን አሸንፈው ካገገሙ በኋላ ፊታቸውን ወደ ኦሮሞ ተስፋፊወች አዞሩ፡፡ አደጋ መጣል እንጅ መዋጋት የማይችለው የኦሮሞ ተስፋፊ ባራት ማዕዘናዊ የውጊያ ጥበብ (ፊታውራሪ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ደጃዝማች) በተካኑት አማሮች ፊት መቆም አቃተው፡፡ የነፍጥ ድምጽ ሲሰማ ኦቦው ካቦ ሸማኔ ፈጠነ፡፡ የቱርክ ነፍጠኞች በከፈቱለት ሰፊ በር ያለ ምንም ፊት ለፊት ውጊያ ሰተት ብሎ የገባው የኦሮሞ ተስፋፊ፣ ነፍጥና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃሎች አምርሮ ጠላቸው፡፡ ሰይጣኑ፣ ጭራቁ በነፍጠኛ ተመሰለ፡፡ ራቡ፣ ጥማቱ፣ ማይምነቱ፣ አረመኔነቱ በነፍጠኞች ተሳበበ፡፡

አማሮች ግራኝን ድል ነስተው የኦሮሞን ቅምኝት ሲገቱት፣ ቅምኝቱን ለማቀላጠፍ ሲባል ብቻ የተሰረተው የገዳ የቀማኛ ዲሞክራሲ ግልጋሎቱን ስለጨረሰ ወዲያውኑ አከተመ፡፡ የገዳ የቀማኛ ዲሞክራሲ ባቀላጠፈው መስፋፋት ይበልጥ የተጠቀሙት ጉምቱ ቀማኞች አባ ጅፋር፣ አባ ምንትስ የሚባሉ አምባገነኖች ሆኑ፡፡ በቅምኝቱ እጅግም ያልተጠቀመው ተራ ኦሮሞ ባምባገነኖቹ ላይ ሲያምጽባቸው ደግሞ ባማራ አሳበቡ፡፡ ፀራማራ ትርክት በሰፊው ተተረከተ፡፡

በኦሮሞ ተስፋፊወች እጅጉን የተበደለው አማራ በደሉን ስላስቆመ ብቻ በዳይ ተደረገ፡፡ አማራ ከመስፋፋት ባይገታን ኖሮ፣ አማራ ወደኋላ ባይመልሰን ኖሮ፣ አማራ እንዲህ ወይም እንዲያ ባያደርገን ኖሮ እያሉ ማላዘን ብቸኛ መጽናኛ ሆነ፡፡ ያማራ ጥላቻ ተለኮሰ፡፡ አማራን ካለጠፋነው ያጠፋናል የሚለውን የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ሐሳብ የጦቢያ ፖሊሲያቸው የማዕዘን ዲንጋይ ያደረጉት ምዕራባውያን ደግሞ ነብታሚ ሙሐመድ ሐሰንን በመሳሰሉ የኦሮሞ ‹‹ምሁሮች›› አማካኝነት በእሳቱ ላይ ቤንዚን ጨመሩበት፡፡

የሙሐመድ ሐሰን ምሁርነት ሙሉ በሙሉ የተገነባው ኦሮሞን ቤተኛ ሐበሻን መጤ በሚለው ባዱ ትርክቱ ነው፡፡ ይህን ትርክት ግን ብዙም ሐተታ ሳያስፈልግ አጥቂን በቀላሉ ለመከላከል በሚቻልባቸው በኦሮሞ ወቅያኖስ ውስጥ በሚገኙት ዝቋላንና ዝዋይን በመሳሰሉት ደሴቶች የሚኖሩት ጥንታዊ አልኦሮሞወች ከየት መጡ? በሚል አንድ ጥያቄ ብቻ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ይቻል ነበር፡፡

የነ ሙሐመድ ሐሰን ውሸት በእንጭጩ ሳይጋለጥ ቀርቶ ይህን ያህል ገዝፎ፣ ይህን ያህል ሕዝብ ለማሳሳት በመብቃቱ ዋናወቹ ተወቃሾች የጦቢያ የታሪክ ምሁራን የሚባሉት ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ምሁራን በምእራባውያን ታሪክ በመራቀቅ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩ፣ እነ ሙሐመድ ሐሰን በሰፊው የጦቢያ የታሪክ መስክ ላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ እንደ ልባቸው ፏለሉበት፡፡

ዋሾና ውሸቱ አይናቁም፡፡ ተጋጣሚው የቀረ ቡድን በፎርፌ ያሸንፋል፡፡ እነ ሙሐመድ ሐሰን ደግሞ የእስካሁን ግጥሚያወቻቸውን ሁሉንም ያሸነፉት በፎርፌ ነው፡፡ ካሁን በኋላ ግን ፎርፌው መቆም አለበት፡፡ መቆም ያለበት ደግሞ ጋጠወጦቹ የኦሮሞ ጎጠኞች ከፈሪነት በሚቆጥሩት፣ አህያ የበቅሎ አባት በሚባልበት ካህንኛ (politically correct) ዘይቤ ሳይሆን፣ አህያ አህያ በሚባልበት መዕምንኛ (politically incorrect) ዘይቤ ነው፡፡ ጥያቄው የህልውና ጥያቄ ስለሆነ፣ እንትን ብንል እንትና ይቀየማል የሚባልበት አይደለም፡፡ ሐቅ የሚያንቀው ጓጉሮ ይሙት፡፡

እየየም ሲደላ ስለሆነ፣ በሞት ሽረት ትግል ላይ ትህትናና ጨዋነት ይቅሩና ሰብአዊነትና ዲሞክራሲም ቅንጦት ናቸው፡፡ ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲ ከኔ ወዲያ ላሳር የሚለው ያሜሪቃ መንግሥት በሁለተኛው ያለም ጦርነት ወቅት የገዛ ራሱን ዜጎች (እንጥፍጣፊ የጃፓን ደም ስላላቸው ብቻ) ከወንጀለኛ ቆጥሮ ሕፃን፣ ሴት፣ ወጣት፣ አዛውንት ሳይል ንብረታቸውን ነጥቆ፣ የዜግነት መብታቸውን ገፍፎ ሰብጉረኖ (concentration camp) ውስጥ ማጎሩን መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡

አጼ ምኒልክን ወራሪ የሚሉ፣ ወራሪው አጼ ምኒልክ ሳይሆኑ በሉባወች የሚመራው የገዳ አረመኔ ሠራዊት እንደሆነ በግልጽ ሊነገራቸው ይገባል፡፡ ፊንፊኔ ኬኛ ሲሉ የቆጡን አወርድ ብለው የብብታቸውን እንዳይጥሉ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ቆንጨራ ሲያነሱ ደግሞ አፈሙዝ ማዞር የግድ ነው፡፡

አጼ ምኒልክ ያደረጉት በገዳ ሠራዊት ማንነቱን የተነጠቀውን ገርባ ወደ ቀድሞ ማንነቱ መመለስ ነበር፡፡ አጼ ምኒልክ የሚወቀሱ ከሆነ፣ ሊወቀሱ የሚገባቸው ምልሰቱን ምሉዕ ባለማድረጋቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡ በግዴታ የተጫነ የተስፋፊ ቋንቋ ከተጫነበት ምድር ላይ ሙሉ በሙሉ የግድ መክሰም፣ በዚህ ቋንቋ የተሰየሙ ቦታወችና ስሞች ደግሞ ወደ ቀድሞ ስያሜወቻቸው ሙሉ በሙሉ የግድ መለወጥ ነበረባቸው፡፡ ኦነጋውያን ፊንፊኔ ኬኛ፣ ከሚሴ የኛ እያሉ የሚጨማለቁት አጼ ምኒልክ ምልሰቱን ምሉዕ ባለማድረጋቸው ነው፡፡ በቀለ ገርባን የመሰለ የኦሮሞ ስም በግዴታ የተለጠፈበት ገርባ፣ ገርባ መሆኑን ሳያውቅ ከእውነተኞቹ አሮሞወች በላይ ጽንፈኛ የሚሆነውም በዚህ ምክኒያት ነው፡፡ ለማ መገርሳ፣ ሕዝቀኤል ጋቢሳ፣ ጸጋየ አራርሳ፣ ዮሐንስ ለታ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ቂጢሳ የማነት ምልሰት ምሉዕ አለመሆን ውጤቶች ናቸው፡፡

ለምሳሌ ያህል ‹ያማራ ሕዝብ ከየት ወደ የት›› በሚለው መጽሐፉ ያማራ ብሔርተኛ መስሎ የቀረበውና፣ ‹‹ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር›› በሚለው መጽሐፉ ላይ ደግሞ 180 ጉላፕ (degree) በመገልበጥ የለየለት ፀራማራ ሁኖ የቀረበውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እንውሰድ፡፡ መቶ ሰማንያ ጉላፕ የመገለባበጡ ምክኒያት የስልጣን አራራው ሲሆን፣ የፀራማራነቱ ምክኒያት ደግሞ ከለማበት የተጋባበት መሆኑ ነው፡፡

አባ ባሕርይ እንደገለጹት (ምዕራፍ 12) ሸዋን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ጎጃምን መውጋት የጀመረው ሮበሌ የሚባለው ወሮበላነቱ ወደር ያልነበረው ሰባተኛው ሉባ ነው፡፡ ስለዚህም ያቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ሸዌወች ከሆኑ የሮበሌ ገርባወች እንደነበሩ በሙሉ እርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ስለዚህም አጼ ምኒሊክ የሸዋ ገርባወችን በእውነተኛ ስሞቻቸው እንዲሰየሙ አስገድደዋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ቂጢሳና ሌሎቹም የኦሮሞ ስሞች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባልተለጠፉበት ነበር፡፡ እሱም ደግሞ አሮሞ ነኝ በማለት የጊዜውን የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት ምክኒያት ባላገኘ ነበር፡፡ አጼ ምኒልክን ደግሞ አምርሮ ከመወቀስ ይልቅ ቢያንስ ቢያንስ እሱና አባቱ በራሳቸው ቋንቋ አንዳርጋቸውና ጽጌ ተብለው እንዲሰየሙ ነጻነት ስላጎነጸፏቸው አብዝቶ ባመሰገናቸው ነበር፡፡

ኦነጋውያን ክልላችን ነው በሚሉት ልቦለዳዊ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ቦታወች ዱከም፣ ቢሸፍቱ፣ አዳማ፣ ውንጂ እያለ ሲጠሩ፣ ያማራ መሠረት በሆነው በምድረ አምሓራ (ወሎ) ውስጥ የሚገኙትን ቦታወች የጁ፣ ራያ፣ ቃሉ፣ ወረኢሉ፣ ወረባቦ እያሉ መጥራት ያማራን ሕዝብ ሆደሰፊነት፣ ትልቅነትና ጨዋነት ቢመሰክርም በሌላ አንጻር ግን እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡ ጨዋ መሆን የሚያስፈልገው ጨዋነትን ለሚያውቅ ብቻ ነው፡፡ ኦነጋውያን ደግሞ ጨዋነት አልተፈጠረባቸውም፣ አያውቁትም፡፡

ኦነጋዊው ዐብይ አህመድ የሚያበሻቅጠውን ደብረጽዮንን እያሽሞነሞነ፣ የሚያከብረውን አምባቸውን የረሸነው ጨዋነቱን ከፍራት ስለቆጠረው ብቻ ነው፡፡ ዲባቶ አምባቸው (ውሃ ውስጥ የሚያልበው ቱርቂ መሆኑ በግልጽ የሚታወቅበትን) ዐብይ አህመድን፣ ያለ ምንም ይሉኝታ ልክ ልኩን እየነገረ ገደቡን እንዳያልፍ ቢያስጠነቅቀውና የጠቅል (ጀነራል) አሳምነውን ቅድመ ዝግጅት በግልጽና በይፋ ደግፎ ቢሆን ኖሮ፣ ራሱንና ባልደረቦቹን ከርሽና አድኖ፣ ያማራን ሕዝብ ደግሞ ያረመኔው የኦነግ ሠራዊት ፍሪዳ ባላደረገው ነበር፡፡

ኦነግ ስለ ልቦለዳዊው አኖሌ ሲያላዝን በእውነተኛው አርባጉጉ ሊወነጀል ይገባል፡፡ አንደኛው ወገን ምዕተ ዓመታት ወደ ኋላ ሂዶ ተስፋየ ገብረአብ እና በረከት ስምኦን የተባሉ አማራጠል እኩይ ቧልተኞች (evil comedians) የጻፉለትን ልቦለዳዊ ስቅጠት (fictional trajedy) ቀን ከሌት እያነበነበ፣ ለኻጩን እያዝረበረበ ሲነፋረቅ፣ ሁለተኛው ወገን ግን ባንደኛው ወገን አሁን ትናንትና የተፈጸሙትን በምስል የተደገፉ አረመኔያዊ ጭፍጨፋወች ከናካቴው መርሳቱ ይቅር የማይባል ኀጢያት ነው፡፡ ለልቦለዳዊው አኖሌ የቆመው ሐውልት ፈርሶ፣ በፍርስራሹ ላይ ፈጠጋርን (አሩሲን) መሉ በሙሉ ያጠፋት ያራተኛው ሉባ የቢፎሌ ሰለባ የሆኑት ያማራ ሰማዕታት ሐውልት መገንባት ይኖርበታል፡፡

ለማጠቃለል ያህል የኦሮሞ ሕዝብ ገዳ የሚባል አፍሪቃ በቀል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰረተ ዲሞክራሲያዊነትን የተላበሰ ዲሞክራቲክ ሕዝብ ነው የሚባለው ትርክት ምንም መሠረት የሌለው የቱሪናፎች ባዶ ቱልቱላ ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጅ ዲሞክራሲያዊ ሕዝብ የለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የገዳ ዲሞክራሲ ምንጭ ቀማኛነት ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ባህል ቢሆን ኖሮ ራሱ ኦነግ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ነበር፡፡ እነ አቦማ ዋቆ የመሳሰሉትን መሪወቹን የበላው የኦነግ ስግብግብ ጅብ ግን አመራሮቹን መቸም ቢሆን በገዳ ዘዴ መርጦ አያውቅም፡፡

ኦነግ እንደ ገዳ ዘመን አገሬውን እየነቀለና እየፈነቀለ በቀማኛነት ሊስፋፋና ሊንሰራፋ እስካልቻለ ድረስ ዲሞክራቲክ ሊሆን አይችልም፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዓይንና ናጫ የነበሩት የኦሮሞ ጎጠኞች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰምና ሙጫ የሆኑት ደግሞ የዘመናችን ግራኝ የነበረው ወያኔ ጦቢያዊነትን ክፉኛ አዳክሞ የመስፋፋት በር ስለከፈተላቸው መስፋፋቱን የሚያቀላጥፍ የቀማኛ ዲሞክራሲ ለመመሥረት ሲሉ ብቻ ነው፡፡

ግራኝ ሙሐመድ አማራውን እጅጉን በማዳከም ላስራ ስድስተኛው ክፍለዘመን አባገዳወች የቅምኝት በር ወለል አድርጎ እንደከፈተ፣ የደደቢቱ ወያኔም አማራውን ግራኝ አስተኔ በማዳከም ለኦነጋውያን የቅምኝት በር በረገደ፡፡ ስለዚህም የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) ወሳኝ ትግል መሆን ያለበት፣ ኦነጋዊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነ የመጣው የሣር እባቡ ዐብይ አህመድ ወያኔ የበረገደውን በር ጭራሹን ነቃቅሎ፣ ጉበኑንና መቃኖቹን አወላልቆ ሳያንቦራቅቀው በፊት ለመጠርቀም ነው፡፡

መስፍን አረጋ mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic