>
2:21 am - Monday July 4, 2022

የ«የምስራቅ አፍሪካ የፖሊሲ ምርምር ተቋም» ምክትል ዳይሬክተር  ነገር... !!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የ«የምስራቅ አፍሪካ የፖሊሲ ምርምር ተቋም» ምክትል ዳይሬክተር  ነገር… !!!
አቻምየለህ ታምሩ
ከታች በታተመው «የምስራቅ አፍሪካ የፖሊሲ ምርምር ተቋም» ምክትል ዳይሬክተሩ «ትንተና» መሰረት «የበዓድ አምልኮ» ማለት ከሌላ ቦታ የመጣ አምልኮ ማለት ነው። ምክትል ዳይሬክተሩ ለ«በዓድ አምልኮ» ይህን ትርጉም የሰጠው ክርስትናና እስልምናን ከውጭ ከመጡ በማድረግ ኢሬቻን ብቻ አገር በቀል ሃይማኖታዊ ሥርዓት አድርጎ  ለመመጻደቅ ነው።
የ«ፖሊሲ ምርምር ተቋም» ዳይሬክተሩ ሲባል የሰማውን ወይም አፉ ያመጣለትን ከሚናገር  እንደ ተመራማሪ  «የበዓድ አምልኮ» ስለሚለው ሃይማኖታዊ jargon  ለመጻፍ ሲነሳ ቢያንስ ቅዱስ መጽሐፍን ወይም ቅዱስ  ቁርዓንን ለመመርመር ጥረት ቢያደርግ ኖሮ  እንዴት አይነት ሰው «የፖሊሲ ምርምር ተቋም» ምክትል ዳይሬክተር መሆን እንደሌለበት በአብነት የምናቀርበው ሰው አይሆንም ነበር።
«በዓድ አምልኮ» ማለት ከሌላ ቦታ  ወይም ከሌላ አገር  የመጣ ማለት አይደለም። «በዓድ አምልኮ» የሚለው ቅዱስ መጽሐፋዊ ፍቺ  መጽሐፉ «ኢታምልኩ ባእደ አምላከ ዘእንበሌዬ» እንዲል ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ የሚመለከን ሥርዓት የሚገልጽ ነው።
በነገራችን ላይ «የፖሊሲ ምርምር ተቋም» ምክትል ዳይሬክተሩ  «በዓድ አምልኮ» የሚለውን ቃል  «ከሌላ ቦታ የመጣ አምልኮ» በሚል  በተረጎመው  እንኳ ብንቀበለው ኢሬቻም ከሌላ ቦታ የመጣ የበዓድ አምልኮ ነው። በዛፍ፣ በተራራና በወንዝ በማምለክ፣ ባሕላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሥርዓትን መፈጸም በነሶምሶንና በነዳዊት ታሪክ ውስጥ አለ። «የፖሊሲ ምርምር ተቋም» ምክትል ዳይሬክተሩ ኢሬቻን ከሌላ ቦታ ያልመጣ በኦሮሞ የተጀመረ  ባሕል ወይም ሃይማኖታዊ ሥርዓት አድርጎ ለማቅረብ  የሚሞክረው በሶምሶምና ዳዊት ዘመን የነበረውንና  ከሌላ ቦታ የመጣውን አምልኮ ነው።
Filed in: Amharic