>
2:09 am - Tuesday May 24, 2022

ኦነጋውያኑ እነ አሕመዲን ጀበል በሃይማኖቱ ስም እንደገና የከፈቱት  ጸረ አማራ ዘመቻ!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ኦነጋውያኑ እነ አሕመዲን ጀበል በሃይማኖቱ ስም እንደገና የከፈቱት  ጸረ አማራ ዘመቻ! 

አቻምየለህ ታምሩ
ሞጣ በሁለቱም ወገን የተጎዱት ወንድማማቾቹ አማሮች ናቸው። በአጥፊዎቹ የተጎዱትም ቢሆኑ ክርስቲያኖች ጭምር  ያሰሯቸው መስጂዶጅና ሙስሊሞቹም ያሰሯቸው ቤተ ክርስቲያኖቹ ናቸው። በዚህ በወንድማማቾቹ ላይ  በድረሰው ጉዳት ግን ወንድማማቾቹን ለማጣላት ከጣራው በላይ የሚሰማ ጩኸት የሚያስጮሁት ትናንትና ከወለጋ፣ ከጅማ፣ ከኢሉባቦር፣ ወዘተ ሙስሊም አማራዎች በግፍ ያሰደዱት፣ ንብረታቸውን የቀሙት፣ የገደሉትና ሰፋሪዎች ብለው ቤታቸውን ያፈረሱት  ጸረ አማራዎቹ እነ አሕመዲን ጀበል ናቸው።
ባለፈው አመት ከወለጋና ከኢሉባቦር «በ1977 የድርቅ ወቅት ከወሎ መጥታችሁ የሰፈራችሁ አማሮች ናችሁ» ተብለው  ሃብታቸው ተዘርፎ፣ ቤት ንብረታቸው ተቀምቶ፣ በሕይዎታቸውና በአካላቸው ላይ ጉዳት ደርሶ የተባረሩ ሙስሊም አማሮች  ዛሬም ድረስ ቆቦ በመጠለያ ውስጥ ከነሕጻናት ልጆቻቸው ጋር  ፍዳቸውን እያዩ ይገኛሉ። በሞጣ ከደረሰው የንብረት ጉዳት በላይ  አማራ ናችሁ ተብለው ከከወለጋና ኢሊባቦር  በተባረሩ ሙስሉም አማሮች ሕይወትና  ንብረት ላይ  የአሕመዲን ጀበል ተከታዮች ጉዳት ደርሷል። ይህ ሲሆን ግን የኦነግ የፕሮፓጋንዳ ጸሐፊዎቹ እነ አሕመዲን ጀበል አንዳች ነገር ትንፍሽ አላሉም።
የአማራ ጥላቻን መመሪያቸው ያደረጉት ኦነጋውያኑ እነ አሕመዲን ጀበል ሞጣ ላይ የተከሰተውን የአማሮች ጉዳት  ሰርግና ምናሽ እያደረጉት ያለው አማራን የሚያጠቁበትና መንጋቸውን በጸረ አማራነት የሚቀሰቅሱበት እድል ስለተፈጠረላቸውን እንጂ ለሙስሊም አማሮች ተቆርቁረው አይደለም። እነ አሕመዲን ጀበል  ለሙሊስም አማሮች ቢቆረቆሩ ኖሮ ሞጣ ከወደመው የሙስሊሞች ንብረት ስንት እጥፍ የሚሆን ንብረታቸው ለወደመባቸውና ለተዘረፈባቸው ከወለጋና ከኢሉባቦር  ለተባረሩ ሙስሉም አማሮች ሲቆረቆሩ እናገኛቸው ነበር።
አሕመዲን ጀበል ስለደረታቸው የጥላቻ ድርሰቶች ነውረኛነትና የፈጠራ ልበወለድነት ወደፊት በሰፊው እመለስበታለሁ። ጅብ ባልዋለበት ቆርበት አንጥፉልኝ የሚለው የሰራውን የማናውቅ መስሎት ነው። የቀረሸውን እያንዳንዷን  የኦነግ ፕሮፓጋንዳ አፈር ድሜ የምናስግጥበት ቀን ሩቅ አይደለም።
የሞጣ አማሮች በሃይማኖት ሊለያዩዋችሁ የተሰለፉትን ኦነጋውያኑን  እነ አሕመዲን ጀበልን የምታስገቡበት ቀዳዳ አትክፈቱ። ጥፋተኞችን ለፍርድ አቅርቡ።  የወደመውን ቤተ እምነታችሁን እንደ ጥንቱ ልማዳችሁ በጋራ አሰሩት። የተቃጠለውን የጋራ መገልገያችሁን  በጋራ ወደ ነበረበት መልሱ።  ለዚህ መላው አማራና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከጎናችሁ ነው። በናንተ በአማሮች መካከል የሃይማኖት ወንድሞች መስለው የሚሰብኳችሁ እነ አሕመድን ጀበል አማሮች ስለሆናችሁ ብቻ ከጅማ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቦር ሰፋሪዎች ናችሁ ብለው የሚያባርሯችሁ፣ ጠላት አድርገው በዱልዱም የሚያርዷችሁና ሀብት ንብረታችሁን የሚቀሟችሁ ኦነጋውያን እንጂ መንፈሳዊ ሰዎች አለመሆናቸውን ከወለጋና ለኢሉባቦር አማራ በመሆናቸው ብቻ ዛሬ የሃይማኖት ወንድሞች መስለው በሚቀርቧችሁ የአሕመዲን ጀበል ተከያዮች ከተገደሉትና ከተፈናቀሉት ወገኖቻችሁ ተማሩ።
ከታች የታተሙት ሁለት ቪዲዮዎች በነ አሕመዲን ጀበል ከወለጋና ከኢሉባቦር  ሰፋሪ ናችሁ ተብለው  ቤታቸው የተቃጠለ፣ ቤተሰቦቻቸው በግፍ ታርደው የተባረሩትን የሙስሊም አማሮች የሰቆቃ ታሪክ የሚያሳይ ነው። እነዚህ በነ አሕመዲን ጀበል ቅስቀሳ ሰፋሪ ናችሁ ተብለው ከወለጋና ኢሉባቦር የተፈናቀሉ ሙስሊም አማሮች ዛሬም ድረስ ቆቦ ውስጥ  በዳስ ተከልለው  የመከራ ሕይዎታቸውን እየገፉ ይገኛሉ። እነ አሕመዲን ጀበል ግን ስላፈናቀሏቸው ስለነዚህ ሙስሊም አማሮች ጉዳት አንዳች ትንፍሽ አይሉም። ከነዚህ ያነሰ ጉዳት ለደረሰባቸው የሞጣ አማሮች ግን አማራውን በሃይማኖት ከፋፍለን ለማጣላት ይጠቅመናል ብለው ስላሰቡ አዛኝ ቅቤ አንጓች መስለው ቀርበዋል። ድንቄም አዛኝ!
Filed in: Amharic