>

እያንዳንዷ ጠብታ ወንዝ ትሰራለች!!![የዋሽንገተን ዲሲና አካባቢው የጋራ ግብረ ሀይል]

ለተግባራዊ እንቅስቃሴ በመነሳት ራሳችንን፣ አገራችን እና ወገናችንን እንታደገ!!

በግፍ ተገድለናል……… በግፍ ታስረናል…… በጭካኔ ተደብድበናል ….. በግፍ ተፈናቅለናል ……. በግፍ ተሰደናል …… ባጠቃላይ
ፍፁም ተዋርደናል፤ ፍፁም ተንቀናል

ባለፉት 23 አመታት እኛ ኢትዮጵያውያን በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በማንነታችንና በህልውናችን ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል የተቀነባበረ ዘመቻ ሲፈፀም የመቆየቱን ያህል ራሳችንና ሀገራችንን ከጥፋት ለማዳን የተደረገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ እነሆ ዛሬ ከምንገኝበት የውርደት ጠርዝ ለመድረስ በቅተናል ። በተቃራኒው ዛሬ ጠላቶቻችን በእኛና በሀገራችን ለማጥፋት ከተያያዘው ዘመቻ ጎን ለጎን በሀገር ሀብትና ንብረት ላይ ከሚያደርጉት ዘረፋ በተጨማሪ ከእኛ ከግፍ ቀማሾቹ በተለይም በስደት ከምንገኘው ኢትዮጵያውያን ኪስ በተለያዩ መንገዶች በገፍ በሚያገኙት ገንዘብ እየከበሩና የአፈና ስርአታቸውን እድሜ ለማስረዘም እየተጠቀሙበት ለመሆኑ ከማናችንም የተሰወረ አይደለም። ይህ ማለት ደግሞ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለግፈኛው የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ አንዱ የፋይናንስ ምንጭ ሆነን መቆየታችን መገንዘብ ግድ ይለናል።

በተለይ በተለያዩ መንገዶች የወያኔን የውጭ ምንዛሪ ችግር በመቅረፍና የባለሟሎቹን ከረጢት ስንሞላ ከመክረማችን ባለፈ በወያኔ የዘረኝነት ቀንበር ስር በግፍ ከሚማቅቀውና በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ተስኖት በተአምር ውሎ ከሚያድረው ወገናችን አፍ ተነጥቆ የመጣን እንጀራ እና የጤፍ ዱቄት በመግ ዛት የግፈኞቹን ኪስ ስንሞላ መቆየታችን ዛሬ ለደረስንበት የውርደት ደረጃ አስተዋፅዎ ስናደርግ ለመክረማችን አንዱ ማሳያ ነው። በአጭሩ በስደት የምንገኝ እኛ ኢትዮጵያውያን ወያኔ ላደረሰብን ግፍና ውርደት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጉልበት እንደሆንነው መገንዘብና መረዳት ዛሬ የሁላችንም አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑን እያንዳዳችን ማመንና መቀበል ፤ ተቀብለንም ይህን ግፈኛና ዘረኛ ስርአት ከነባለሟሎቹ በቃ ችሁ ልንላቸው ይገባል።

ይህን በግድያ፤ በአፈናና በዘረፋ ቅጥ ያጣ የወያኔ ስርአት እንዲሁም በወንጀል የተጨማለቁ ባለሟሎቹን በቃችሁ!! ለማለት ትንሽና አንዳች የሚናቅ ነገር እንደሌለ ሁላችንም ማወቅና መረዳት ይኖርብናል። “እያንዳንዷ ጠብታ ወንዝ እንደምትሰራ ሁሉ” ስለዚህ በመጀመሪያ ከተራበው ፤ ከተጠማውና ከታረዘው ወገናችን ጉሮሮ እየተነጠቀ የሚቀርብልንን እንጀራ እና የጤፍ ዱቄት ባለመግዛትና በኪሳራ ከገበያ በማስወጣት ህብረታችንና አንድነታችን እንኳን ካዝናቸውን ግፈኛ ስርአታቸውውንም ጠራርጎ ማስወገድ እንደሚችል ለጠላትም ለወዳጅም የምናሳይበት ወቅቱ ላይ ነንና ሁላችንም እንነሳ!!

“ለተግባራዊ ሥራ በጋራ እንነሳ!!!!”
የዋሽንገተን ዲሲና አካባቢው የጋራ ግብረ ሀይል
dctaskforce.eth@gmail.com
571-327-8492

Filed in: Amharic