>

የእቴጌ መነን አሥፋው ታሪክ ምን ይመሥላል? በአገዛዙ ላይ ምን አይነት ሚና ነበራቸው? (በፍቃዱ ጌታቸው)

የእቴጌ መነን አሥፋው ታሪክ ምን ይመሥላል? በአገዛዙ ላይ ምን አይነት ሚና ነበራቸው?

 

በፍቃዱ ጌታቸው
ግርማዊ  እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓም በወሎ ጠ/ግዛት  በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጏ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር  አስፋውና ከወ/ሮ ስሀን ሚከኤል ተወለዱ። እቴጌ መነን በልጅነት  ዘመናቸው በእናት በእባታው ቤት ሀህምሀር ተቀጥሮላቸው እማ ርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጏዳኝ ልዩ ልዩ የቤ ት ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ  ለመባል በቅተዋል፡፡
በ1892 ማለትም በተወለዱ በአሥረኛ  እመታቸው ለመጀመሪያ ባለቤታቸው በህግ ተዳሩ፡፡ ከእኝህ ባለቤታቸው ወ/ሮ  በላይነሽ ዓሊንና ጃንጥራር አስፋው ዓሊን ወለዱ፡፡ ከዚያም  ሁለተኛ ባለቤታቸውን በማግባት ጃንጥራር ገብረእግዚ አብሄር አመዴንና ወ/ሮ ደስታ እመዴን ወልደዋል፡፡ በ1903  ዓም ወደ  መጀመሪያ ራስ ልኡልሰገድ እጥናፍሰገድን አገቡ። በዚሁ  ዓመት ወደ መጨረሻም ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር ተጋቡ። የእቴጌ መነን እና  የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋብቻ ፓለቲካዊ ሢሆን የአጎታቸ ውን የልጅ ኢያሡንና የቀዳማዊ ኃይለሥላሤን ጠብ ለማስወገድ  ይቻላል በሚል መኳንንቱ ሁሉ በተለይም እነራስ ቢትወደድ ተስማ ናደው መክረው የፈፀሙት ነበር፡፡
እቴጌ መነን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ያፈሯቸው  ልጆች ስድስት ሲሆኑ ዝርዝራቸውም የሚከተለው ነው
ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሤ
ለዑል አልጋወራሽ እስፋወሠን ኃይለሥላሴ
ልዕልት ዘነበወርቅ ኃይለሥላሤ
ልዕልት ፀሃይ ኃይለሥላሤ
ልዑል መኮንን ኃይለሥላሤ
ልዑል ሣህለሥላሤ ኃይለሥላሤ
እቴጌ መነን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር በተጋቡ በሃያ ዓመታቸው  ማለትም 1923 ዓ፡ም፡ የእቴጌነት ዘውድ ጫኑ፡፡ በእድሜ ዘመና ቸው በግል ገንዘባቸው በኢትዮጵያና በእየሩሳሌም በርካታ ቤተክር ስቲያናትን አሳንፀዋል፡፡ በጉ አድራጎት ድርጅቶችን አቋቁመዋል፡፡  አንዳንዶችን ለመጥቀስ ያህል መጋቢት 16 ቀን 1910 ዓ፡ም፡ የሐመረ- ኖህ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስቲያንን አስርተው ታቦቷን በክብር  አስገብተዋል፡ በ1915 ኢየሩሳሌምና ግብፅን ጎብኝተዋል፡ በ1923  ዓ፡ም በመስከረም ወር እቴጌ መነን ተማሪ ቤትን አቋቋሙ፤  በ1925 ዓ፡ም፡ በፉሪ ቀበሌ የምትገኘውን የቅድስት ሐናን ቤተከር ስቲያን አሠሩ፤ በመስከረም ወር 1926 ዓ፡ም፡ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ው በዮርዳኖስ ያሰሩትን የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያንን እሣቸው  በተገኙበት አስመረቁ፤ በ1935 ዓ፡ም፡ ለገሀር የሚገኘውን የእጅ  ጥበብ ት/ቤት አቋቋሙ፤ በ1939 ዓ፡ም፡ የካቲት ወር ሠበታ ከተማ  የምትገኘውን የጌቴሴማኒን ቤተክርስቲያን በገንዘባቸው አሠሩ፤  በ1943 ዓ፡ም ወደግሽን ማርያም ቤተክርስቲያን የሚወጣውን የሰ ርጥ መንገድ አሠሩ፡፡ በዚሁ ዓመት በጠላት ዘመን ፈርሶ የነበረ ውን የቦሩ ሥላሴን ብር ወጪ አድርገው አሠሩ፡፡ ግርማዊት እቴጌ መነን ኢየሩ ላሌምን ለሁለተኛ ጊዜ ለመሳለምና በዮርዳኖስ ያሠሩትን ቢተክር ስቲያን ለመመረቅ አድካሚ ጉዞ አድርገዋል፡፡ ጉዟቸውም ከአዲስ አበባ ጅቡቲ በባቡር፤ ከጅቡቲ ግብፅ በመርከብ፤ ከግብፅ ወደኢየ ሩላሌም በባቡር ነበር፡ አቡነ ቄርሎስም አዲሱን ቤተክርስቲያን  ለማየትና ለመባረክ ከግርማዊት እቴጌ ጋር አብረው መጓዛቸው  ተዘግቦ ይገኛል፡፡
የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን እንደሚወር  ይፋ በሆነበት ጊዜ ግርማዊት እቴጌ መነን መስከረም 1 ፤ ቀን 1928  ዓ፡ም፡ የዘመን መለወጫ ዕለት ለዓለም ሁሉ ሴቶች የትግል ጥሪ  አድርገው ነበር፡፡ በንግግራቸውም “በዓለም ያላችሁ ሴቶች ሁሉ  በዓለም ላይ እውነተኛ ፍርድና ሰላም እንዲነግስ የመንግሥት ስዎ ች ሁሉ በሚሠሩት ሥራ በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲመሩ በምና ደርገው ፀሎት ተባባሪዎች እንድትሆኑ እንለምናለን” የሚል ነው።
እቴጌ መነን በ1928 ዓ፡ም፡ ግርማዊ ባለቤታቸው ጦር ሜዳ ሄደው  ከጠላት ጋራ ስላገራቸው ሢዋጉ በከተማው ያሉ ወይዛዝርትን እየ ሰበሰቡ ለቁስለኞች እና ለሠራዊቱ የሚሆን ስንቅ፣ ትጥቅና የህክም ና ቁሳቁስ እያዘጋጁ ይልኩ ነበር፡፡ የከተማውም ፀጥታ እንዲጠ በቅ ከከተማው የዘበኛ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር በትጋትና በብር ታት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በጦር ሜዳ ካሉት ለባለቤታቸው እና  በዚያው ከሚገኙ የመረጃ ሰዎች የጣሊያን አውሮፕላኖች በአዲስ  አበባ በሚኖረው በሰላማዊ ህዝብ ላይ የቦንብ ጥቃት ለማድረስና  ህፃን፣ ሽማግሌና ሴት ሳይለይ በአንድነት ለመደምስስ እየመጡ  እንደሆነ በስልክ በተላለፈ ጊዜ ግርማዊት እቴጌ መነን በአውቶ ቢል ሆነው በድፍረት በከተማው እየዞሩ በየመንገዱና በየገብያው  ያለው ህዝብ በአንድነት እጅብ ብሎ መቆሙን ትቶ እንዲበተንና እደ ጋውን ወደሚከላከልበት ቦታ አንዲደበቅ በማድረጋቸው ብዙ ህዝብ ሊድ ን ችልሏል፡፡
እቴጌ መነን በፓለቲካዊ አስተሳሰብ የተነሣ የእና ታቸው የወሮ ስህን ወገኖች በተለይም እያታቸው ንጉሥ ሚካ ኤልና አጉታቸው ልጅ ኢያሱ ከባለቤታቸው ከቀዳማዊ ኃይለሥላ ሴ ጋር በፈጠሩት ፓለቲካዊ ቅራኔ ሰበብ በተካሄደው የሰገሌ ጦር ነት ከግራ ከቀኝ ተሰልፈው የተዋጉ ወገኖቻቸው ያለቁባቸው ቢሆ ንም በየጊዜው ሁለቱንም ወገኖች እያስማሙ በአንድነት እንዲኖሩ  አስችላዋል፡፡ ይህንን የእቴጌ መነን አለፋውን ብርታት በማስታወስ  አርብ የካቲት 9 ቀን 1954 ዓ፡ም፡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋ ቸው በተቀበሩ በበነጋው ባለቤታቸው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቀጥሎ  ያለውን ንግግር አድርገው ነበር፡፡
“ሁላችሁም ከምታውቁት በላይ  እኛ አራሣችን በቅርቡ የምናቃት ልንገልጠው የሚገባን ክፉ ቀን የማይለውጣት፣ ሃይማኖተኛ፣ በደጉም ጊዜም ዓለማችን ላይ ተጣልተን ሰው አስታርቆን የማያውቅ፣ ሣራ አብርሃምን አንደምትታዘዘው እሷም የእኛን ሃሳባችንን ፈፅማ የእግዚእብሄር ዳኝነት እስኪለየን ድረስ ለህፃናትም ሆነ ለሽማግሌዎች ህዝብም የሚጠቀምበት ጉዳይ ከምትረዳንም በላይ ራስዋ ለማድረግ በምትጣጣረው  ባሰራችው ሁሉ ተመስክሮ የተቀመጠ ነው”
የአፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ በተባለውና በሌሎችም  መፅሃፍት እንደተረጋገጠው እቴጌ መነን አስፋው የአፄ ፋሲል ተወ ላጅ ናቸው፡፡ በዚሁ መፅሃፍ እንደተብራራው ከአፄ ፋሲል ጄምሮ  የዘር ሃረጋቸው ሲመዘዝ አያታቸው ንጉሥ ሚካኤል ስምንተኛ ትው ልድ ናቸው፡፡ እናታቸው ወ/ሮ ስሀን ዘጠነኛ እራሣቸው ግር ማዊት እቴጌ መነን አስፋው ደግሞ እስረኛ ትውልድ ናቸው፡፡  በአፄ ፋሲል በኩል እቴጌ መነን እስፋውና ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ  ዝምድና እላቸወ፡፡ዝምድናቸው ግን ጋብቻ የማይከለክል ሲሆን  አሥራ ሁለተኛ ትውልዳቸው ላይ የሚገጥም መሆኑን የታሪክ መፅ ሃፍት ያረጋግጣለ፡፡
ግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው የካቲት 9  ቀን 1954 ዓ፡ም፡ በተቀበሩበት ዕለት ከተሰሙት የሃዘን እንጉርጉሮ ዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡፡
የመኮንን እናት ምነው ምን ነካዎ፣
ብቸኛ ጓዶዎን ጥለው መሄድዎ፡፡
እረ ምን ይወራል ምን ትንፋሽ አላና፣
መነን ስታቋርጥ የሞትን ጉዳና፡፡
መኮንን ገሥግሦ ሥላሴ መግባቱ፣
ቤት ሊሠራ ኖሯል ለወላጅ እናቱ።
Filed in: Amharic