>

የወደብ ከተማዋ ምፅዋ   (ክፍል-2) ዳን ኤል እንግዳ

የወደብ  ከተማዋ ምፅዋ

       ክፍል-2
ዳን ኤል እንግዳ
በእለቱ አብዮታዊው ሰራዊት ከማረካቸው ምርኮኞች መካከል መሐሪ ዮሐንስ የሚባል የሻዕቢያ ተዋጊ ይገኝበት ነበር ። ይህ ተዋጊ በሰጠው ቃል መሰረት በጦሩ ውስጥ የሀይሊ አዛዥ እንደነበረ ተናግሯል፡፡
ከርሱ በተገኘው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ዘመቻው በከፍተኛ ደረጃ የታቀደ ሲሆን አፈጻጸሙን በበላይነት የሚከታተሉትም ኢሳያስ አፈወርቂ እና ስብሐት ኤፍሬም ነበሩ፡፡
መሐሪ እሱ የሚያውቀውን ያክል በሰጠው መረጃ መሰረት ሻዕቢያ ለውጊያ ያሰለፈው ሀይል፦
1. አምስት እግረኛ ብርጌድ
2. ሁለት ሜካናይዝድ ብርጌድ
3. አንድ ኮማንዶ ብርጌድ ነበሩ፡፡
#በከባድ መሳሪያ በኩል
1. በርካታ T-55 ታንኮች
2. ሶስት መድፈኛ ሻለቃ
3. አራት የአየር መቃወሚያ ሻለቆች ተሳታፊ ነበሩ፡፡
#ዘመቻው“ፈንቅል” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን ዓላማውም የምጽዋን ወደብ መቆጣጠር እና
የአስመራ-ምጽዋን መንገድ ከነአካቴው መቁረጥ ነው፡፡
የሻዕቢያ ሀይል የተሰማራው ከአፋቤት ከተማ ነበር፡፡ ስምሪቱ ሲጀመርም (ጥር 30/1982 በግምት ከስድት ሰዓት በኃላ) ኢሳያስ አፈወርቂና ስብሐት ኤፍሬም ንግግር አድርገውም እንደነበር አክሎበታል፡፡
ከዚያም ለግዳጁ በሶስት አቅጣጫ (በሰለሞና፣ሸዒብ እና ውቅሮ ግንባሮች) ተንቀሳቀሱ፡፡
እኩለ ሌሊት ላይ ሰለሞና አቅራቢያ ደርሰው ከላይ የተገለጸውን ድንገተኛ ጥቃት ከፈቱ፡፡
በድንገተኛው ጥቃት የተደናገጠውን ጦርም በከፍተኛ ሃይል ማጥቃት መቀጠላቸውን ጥቃቱ ድንገተኛ ከመሆኑ የተነሳ መቋቋም ያቃተው አብዮታዊ ሰራዊት በየፊናው መበተኑን ከመረጃው ማወቅ ተቻለ። ያንንም ተከትሎ ሻዕቢያ ድል ቀንቶት ጋህተላይን በእጁ አስገብቶ ቀጣዩን ጥቃት ከፈተ።
የኮሩ ወታደራዊ አዛዦችና የፖለቲካ ሰዎች ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ምጽዋ ባለው የ6ኛው ክፍለ ጦር
መሰብሰቢያ አዳራሽ በጄኔራል ጥላሁን ክፍሌ ሰብሳቢነት ተሰበሰቡ፡፡
የሻዕቢያን ግብና ዓላማ ምን ሊሆን እንደሚችል ተነበዩ፡፡
አንዳንዶቹ “ሻዕቢያ ውጊያውን የከፈተው ለጊዜው ሽብር ለመልቀቅ ነው” የሚል ግምት ሰነዘሩ፡፡
ከፊሎቹ ደግሞ “ሻዕቢያ ምጽዋን ለመቆጣጠር ያለመ ይመስላል” በማለት ግምታቸውን አስቀመጡ፡፡
በዚህ ዙሪያ ክርክር ተደረገ፡፡
የኋላ ኋላም “ሻዕቢያ ምጽዋን ለመቆጣጠር ያልማል” በሚለው ሃሳብ ተስማሙ፡፡ ይሁንና በአዛዦቹ መካከል በነበረው አለመጣጣም ሳቢያ የሚረባ የውጊያ እቅድ ሳይነድፉ  ስብሰባው ተበተነ።
ከጥር 30 ቀን 1982 እስከ የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ምጽዋን ለመያዝ ሻዕብያ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ሌት ከቀን ተዋግቶ ታሪክ የማይረሳው ፤ መሥዋዕትነት በከፈለው  አብዮታዊ ሠራዊት ግዳጅ ውስጥ ምንጊዜም ቢሆን የማይረሱ ጥቂት ሰዎች አሉ ።
የተወሰኑት “በወገናቸው ላይ ክህደት ፈጽመው ለሻዕቢያ ያደሩና የሠራዊቱን የውጊያ ዕቅድና አሰላለፍ ምሥጢር ያጋለጡ” ተብለው በወቅቱ መንግሥት የተኮነኑ ሲሆን ፣ ሌሎቹ ደግሞ “ለጠላት እጄን ከምሰጥ ሞቴ ይሻለኛል” ብለው ራሳቸውን በራሳቸው የሰዉ “ዳግማዊ ቴዎድሮሶች” ናቸው ፡፡
በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ምጽዋ በሻዕቢያ ሲያዝ ለ30 ዐመታት የተካሄደው ረጅምና መራራ “የእገነጠላለሁ፤ አላስገነጥልም” ጦርነት ማብቃቱ ገሃድ ነበር፡፡ በተገኘው የሻዕቢያ ድል በመንግሥት መከላከያ ሠራዊት ላይ ከባድ የአካልና የህይወት ዋጋ የመከፈሉን ያህል፣ የአዛዦችንና የመላ አገሪቱን ህዝብ ስሜት በእጅጉ የጐዳ ክስተት ነበር፡፡
ድል ሲገኝ “የታሪኩ ቀዳሚ ተዋናይ እኔ ነኝ” ብሎ መፎከር የተለመደውን ያህል እንዲህ አይነት ውድቀት ሲያጋጥም ደግሞ ዕርስ በርስ መነታረኩና እራስን ከሃላፊነት ነፃ ለማውጣት ጣት መጠቋቆሙ የተለመደ ነው፡፡ ለዚህም ነው በምጽዋ ግንባር የነበረው “መክት ዕዝ” ወይም 606ኛ ኮር ዋና አዛዥ በነበሩት ብ/ጄኔራል ጥላሁን ክፍሌ ስም የጠለሸው፡፡
ብ/ጄኔራል ጥላሁን ክፍሌ “የተማረክሁት ከአቅም በላይ የሆነ የጠላት ኃይል ገጥሞኝ እንጂ ወድጄና ፈቅጄ ለሻዕቢያ እጄን አልሰጠሁም” በማለት ቢያስተባብሉም በቀድሞ ጓደኞቻቸውና በአለቆቻቸው በኩል የተሰጣቸው ሥም ግን እጅግ የተለየ ነው፡፡ የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት ዋና አዛዥ የነበሩት ሜ/ጄኔራል ውብሸት ደሴ በቁጥር አሠ 2.1/ነ 142/102/82 የካቲት 11 ቀን1982 ዓ.ም ለጦር ኃይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ለሌ/ጄኔራል አዲስ ተድላ በጻፉት ረጅም ደብዳቤ ውስጥ ስለተማረኩት ጄኔራሎች እንዲህ የሚል ሪፖርት አቅርበዋል፡-
“…በጠላት ከሚናፈሰው የሬዲዮ ወሬ ሰሞኑን እንደተከታተልነው ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ሠራዊት ታሪክ አሳፋሪና ከፍተኛ የታሪክ ተወቃሽነት ክስተት ተከስቶአል፡፡ ይኸውም መንግሥትና ፓርቲያችን ከፍተኛ እምነትና ኃላፊነት ጥሎባቸው ለጄኔራል መኮንንነት ያበቃቸው ብ/ጄኔራል ጥላሁን ክፍሌና ብ/ጄኔራል ዓሊ ሐጂ አብዱላህ ከጠላት ወገን ሆነው ለጀግናው አብዮታዊ ሠራዊታችን የእጅ ስጥ ትዕዛዝ መልእክት እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡
“እነዚህ ሁለት ጄኔራል መኮንኖች ከቀይ ባሕር አውራጃ ውጊያ ቀደም ብለው ከጠላት ጋር የቅርብ ግንኙነት ሳያደርጉ እንዳልቀረና ጥላሁን ክፍሌ ቀይ ባሕር የሰፈረውን የወገን ጦር የሰው ኃይልና የጦር መሳሪያ አቀማመጥ ለጠላት ሳይሰጥ አልቀረም፤ እንዲሁም የ3ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር አዛዥ የነበረው ከሃዲው ብ/ጄኔራል ዓሊ ሐጂ የክፍለ ጦሩን ጠቅላላ ምስጢር ለጠላት አሰልፎ ሳይሰጥ አልቀረም የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሮብኛል፡፡
“የ6ኛ ነበልባል ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄኔራል ተሾመ ተሰማ እስከ የካቲት 9/1982 ዓ.ም 0800 ሰዓት ድረስ ከእኔ ጋር የሬዲዮ ግንኙነት እንደነበረውና ባስተላለፈልኝ መልእክት ጠላት አይሎ የምፅዋ ከተማን መቆጣጠሩንና ሁሉም ነገር ከአቅም በላይ እንደሆነባቸው ነግረውኛል፡፡ እርሳቸውም ቢሆኑ በአሁኑ ሰዓት ግንኙነት ስለተቋረጠ ይሙቱ ይኑሩ የታወቀ ነገር የለም…” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በወቅቱ የታሪኩ አካል የነበሩ የሰራዊቱ አባላት የሚያጋሩን የሚኖር ይመስለኛል በዚህ ዙሪያ?
ሁለቱ ሴረኛ ጀነራሎች ቅ
ይሄን የ18ኛ ተራራዉ አባል የገለፀዉን ሠሜሃዉ
የጥላሁን እና የአሊ ከሥመራ የመጡት ነገ በነሡ ላይ የሚወሠደዉን እርምጃ ሥለሚያዉቁ
ምርጫቸዉ ሻቢያ  ጋር መቀላቀል ነበር።
እኔ እንደገለፅኩልህ ወደ ምፅዋ የጥላት ወረዳ ሁለት ጀነራሎች ያቋረጡት ሐሳብ የሻጥሩ ሴራ በእነሡ ቅንብር መሆኑን ጠቋሚ ነዉ እንደመጡም በቀጥቴ በሠሊና አካባቢ ወደሚገኘዉ የጥላት ይዞበታ መግባታቸዉ በአርከት ያዩት ኮሎኔል በላይ አሥጨናቂ ከባህር ሐይል ግቢ  በዋና ተሻግረዉ ወባፀ በመምጥት ሲቃ በተናነቀዉ ድምፃቸዉ በቁጣ ጣወለት በር ላይ
ጀነራል ተሾመ በማለት ተጣሩ
ጀነራሉ አቤት በላይ እዬ
በማለት ምን ችግር አለ አሉ ጀ/ል ተሾመ
ኮ/ል በላይም እነዚህ እሥቱፒዶች ጥላሁኖና አሊ ሐጅ በዋዝ ጅፕ ሠንጥቀዉ ወደሻቢያ ቀጠና ገብ በመነፀርም ሥከታተል እጅ ሠጡ  ከአሁን በሖላ ምንም አይነት ትእዛዝ
መቀበል የለብንም በማለት ሲገልፁ በቦታዉ ነበርኩ።
Filed in: Amharic