የሸገር የሕዝብ መናፈሻ አደባባይ ምረቃ ክንውን ወቅት ፤ ሰምቼና አይቼ የታዘብኳቸውን የቋንቋ አጠቃቀም በተመለከተ
ታጠቅ መ ዙርጋ
ሰምቼና አይቼ ለስላሳ ትችት ወይም አስተያየት መስንዘር በፈለኳቸው ቀጥሎ ባሉት ነጥቦች ላይ እንደ እኔ ተሰምቷችው በጽሁፍ ወይም በድምጽ የተቹ ወይም አስተያየታቸውን ያካፈሉ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ ። በሰሙትና ባዩትን ሁኔታ ቅር ተሰኝተው የተሰማቸውን በድምጽም ሆነ በጽሁፍ ገልጸው አደባባይ የሚያወጡበት መንገድ ጠፍቷቸው ወይም አቅም አንሷቸው በዝምታ ያለፉ ብዙ ሺዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም እገምታለሁ። ምናልባትም በዚያን ትዕይንት ቦታ የቋንቋ አጠቃቀም ግድፎች እንደነበሩ ያስተዋልኩ ብቸኛ ሰው ልሆንም እችላለሁ ። በመሆኑም ሰምቼና አይቼ ቅር በተሰኘሁባቸው ‘በሀገሬ! እና በሕዝቤ! ጉዳዮች ላይ ፣ ከሀገሬ! እና ከሕዝቤ! ጋር በተዛመዱ እርእሶች፣ ነጥቦች ፣ ኩነቶች ፣ ክስተቶች ወዘተርፈ አስተያየት ለመስጠት፣ ለመተቸት፣ለመሄስ ፣ለመከራከር ወዘተ..የማንንም ፥ ፈለግ አልከተልም፣ ፤ፈቃድ/አፕሩቫል እና እውቅና አልጠይ ቅም።
እንግሊዝኛ ከብሄራዊ ቋንቋችን ለምን ይቀድማል? የ(Park) ቃል የሚተካ የአማርኛ ቃል የለንምን ? The (republic guard የሚተኩ የአማርኛ ቃላት የሉንምን? ሪፐብሊዊ መንግሥት አለን? ሪፐብሊክ ከተባልንስ በምን መስፈርት)?
ሀ) እንግሊዝኛ ከብሄራዊ ቋንቋችን ለምን ይቀድማል? በየትኛውም አገር የሌላ አገረ ዜጎች በታጋበዙበት ፥ መንግሥታዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ግብረሰናያዊ፣ ማህበራዊ/ባህላዊ ወዘተርፈ ሰብሰባዎችና በዓሎች ሲደረጉ በመጀመርያ በአስተናጋጁ አገር ብሄራዊ ቋንቋ በመቀጠል ተጋባዦች በሚስሙት ቋንቋ እንደሚገለጽ በሁሉም አገራዊ ኅልወና ባላቸው አገሮች ሁሉ የተለመድ ሥርዓት ነው ። ከላይ በተጠቀስው ዕለት የትርኢቱ ሥነ-ስርዓት ትመራ የነበረቹ ሹሚት፤ በርግጥም አማርኛን በማስስቀደም፣ እንግሊኛን በማስከተል ነው በዓሉን ያስጀመረቹ። ከዚያ በኋላ እስከ በዓሉን ማብቄ በእንግሊኛ ነው የመራቹ።
ለ) የ(Park) ቃል የሚተካ የአማርኛ ቃል የለንምን? ተጽፎ ያነበብኩ ‘Sheger park’ በሚል በእንግሊዝኛ ጽሁፍ ብቻ ነው ። ለምን አማርኛን አላስቀደሙም?
ለምን ሸገር የሕዝብ መናፈሻ አደባባይ ወይም ሸገር የሕዝብ መዝናኛ አደባባይ ተብሎ በቅንፍ {SHEGR PUBLIC PARK} አይባልም ወይም ፦
-ሸገር የሕዝብ መናፈሻ አደባባይ ተብሎ ዝቅብሎ
-SHEGER PUBLIC PARK ኣይባልም ?
ለብሄራዊ ቋንቋ ግድየለሸነት ወይም ካለመቀርቆር ካልሆነ በስተቀር ፤ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የአማርኛ ሊሂቃን ስላሉን በርካታ አማራጮች ማቅረብ ይቻላል። ‘ባለቤቱ የናቀው አሞሌ ባለ ዕዳ ………’ ካልሆነ በቀር ። ኬኒያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር (professor Ali Muzeri) ሶስቱ የአፍሪካውያን ውርሶች (The African Triple Heritages) በማለት ከቅርጸ ድምጽ ጋር ባጠናቅሩት የአፍሪካውያን ታሪክ – ‘before the British started the Latin alphabet, Ethiopia had church literature’ አሉ ። የባዕድ ቋንቋ ከብሄራዊ ቋንቋችን ማስቀደም የምንቃጣው ለምን ይሆን ?
ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ ባይነኝ። ራሱን በቻለ እርእስ ጥሩ ጥናት ተደርጎበት መመልስ የሚያስፈልገው ጥያቄ ቢሆንም፣ ለግዜው የሚታየኝን ጨረፍ ጨረፍ ላድርግ ።
- የአገዛዙ ሥርዓትና የአገዛዙ ሹማምንት ለብሄራዊ ቋንቋችን ክብርና ዋጋ አለመስጠት
- ኢትዮጵያውያን ለብሄራዊ ቋንቋችን ኅልውና ያለን ንቃተ-ኅሊናና ግንዛቤ የተለያየ በመሆኑ ፤ ብሄራዊ ቋንቋችን በበዘፈቀደ/በግድ የለሽነት የሚጠቀሙ ስላሉ
- አብዛኛው የመማርያ መሳርያዎችና ቁሳቁሶች በንግሊዝኛ የተዘጋጁ ስለሆኑና አብዛኛውን የትምህርት ዘመኛችን በእንግሊዝኛ ቃላት ስለምንጠቅም ሳናውቀውና ግብታዊ (sub-consciously and spontaneously) እንግሊኛን ለመቀላቀል ስለምንገደድ
- ከላይ እንደጦቆምኩት ገዢዮቹ ለብሄራዊ ቋንቋ የማይጨነቁ ከሆኑ፣ የገዢ መደብ ልፍስፍስ ምሁራን ከየትኛውም ብሄር ብሄረሰብ ቢሆኑም ፤ አለቆቻቸውን ለማስደሰት ለብሄራዊ ቋንቋ አይጨነቁም /ዋጋ አይሰጡም ወዘተርፈ ።
ሐ) The (republican guard) የሚተኩ የአማርኛ ቃላት የሉንም? ሪፐብሊዊ መንግሥት አለን ? ሪፐብሊክ ነን ከተባልንስ በምን መስፈርት ነው)?
እዚህ ጋ በቅድሜያ የሪፐብሊክ/Republic – የእንግሊዝኛ ትርጉም እጀግ በጣም አሳጥሬ ላስጨብጥ ።
I .Country with a system of government in which the elected representatives of the people are supreme, with an elected head (the president) as, eg in the US,France,India…… <2> any society in which the members have equal rights and privileges ……[Oxford Advanced Learner`s Dictionary Of Current English,1974]
- A republic is a country where power is heled by the people or the representatives that they elect. Republics have presidents who are elected, rather kings or queens (Google chrome)
3 .Republic, a) ‘form of government in which a state is ruled by representatives of the citizen body. ……………..Citizens do not govern the state themselves but through representatives ……. b) the term republic may also be applied to any form of government in which head of state is not a hereditary monarch’ (Andr`e Munro).
የነዚህ የአማርኛ ትርጉም እጀግ በጣም በማሳጠር ፦
- በተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ፍጹም የበላይነት የሚገዛ/የሚተዳደር መግሥታዊ ሥርዓት እና የተመረጠ ቁንጮ/ፕሬዝዳንት ያለው አገር ። እንደ አሜሪካ፣ፍራንስ፣ ህንድ ወዘተ..
- ለማኅበረሰቡን አባላት እኩል መብቶችና ጥቅሞች የሚሰጥ ማኅበረሰብ ያለበት አገር
- በሕዝብ በተመረጡ ተወካዮች እና በሕዝብ በተመረጠ ፕሬዝዳንት የሚተዳደር አገር
- በዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ ሳይሆን ፤በዜጎች ተወካዮች የምትተዳደር አገር/ ብሄር
- ሪፐብሊክ ማለት ፦ እርዕሰ ብሄሩ ወይም ፕሬዝዳንቱ ከዘውዳዊ አገዛዝ ውርስ ላልሆነ የትኛውም መንግሥታዊ ቅርጽ ላለው አገር ፤ መዋል ወይም ማገልገል ይችል ይሆናል ። ልብ በሉ ይችላል አላለም ፤ ምናልባት ነው ያለው ።
- ታዲያ በየትኛው መስፈርት ነው ገዢዮቻችን ሪፐብሊካዊ ነን የሚሉን? ከላይ ከአንድ እስከ አራት (1-4) ባሉት ትርጉሞች መሰረት ረፐብሊክ ማለት ሕዝባዊ ወይም ሕዝባዊ መንግሥት ማለት ነው ። ከላይ በተራ ቁጥር አምስት (5) የተቀመጠውን ትርጉም ስለምናሟላ ይሆን የመንግሥት ሥርዓታችን ሪፐብሊክ/ሕባዊ ነው የሚሉን? የውሸት/ ሲዶ ወይም ምኞታዊ/ ዩቶፒያ ሪፐብሊክ ! ለምን ያልሆነውን ነን ይሉናል?
- ሪፐብሊካን ጋርድ ፦ መርሃግብሩን ስትመራ የነበረቹ ሹሚት የጦር ሃይሎች ትዕይንት እንዲያሳዩ ስትጋብዝ ‘ዘሪ-ፐብሊካን ጋርድ’ እያለች ታስተዋውቅ ነበር።
- ሪፐብሊክ ነን ካሉን በቅድሜያ በብሄራዊ ቋንቋችን ፣ የሕዝብ ዘቦች ወይም ሕዝባዊ ዘቦዝች ብላ በመቀጠል በእንግሊዝኛ (the Republican guard ) ብላ መጥራት መግለጽ አልነበረባትምን?
የዚህ ጽሁፍ መልዕክት ሲጠቃለል ፦
- በማንኛውም ፖለቲካዊ ፣ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ ፣ ግብረሰናአዊ፣ ንግዳዊ ወዘተ.. ስብሰባ መድረኮች የባዕድ ቋንቋን ማስቀደም ብሄራዊ ቋንቋችንን የመናቅና የማሳነስ ባህሪ አለው ። በመሆኑም የባዕድ ቋንቋ ከብሄራዊ ቋንቋችን ላለማስቀደም ትልቅ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ።በመጀመርያ በብሄራዊ ቋንቋችን በመቀጠልም ተጋባዦችን በሚሰሙት ቋንቋ ማስተናገድ በሌሎችም ሃገራትም የተለመደ ነው ።
- የመናፈሻዎች፣ የመንገዶች፣ የጎዳናዎች፣የንግድ ቤቶች ፣የትምህችት ቤቶች ፣የሃይማኖት ድርጅቶች ፣የተለያዩ አገራዊ ተቋምት ወዘተርፈ ስሞች ፣ በመጀምረያ ተርታ በብሄራዊ ቋንቋችን ፤ በዓለም አቀፋዊ ቋንቋ (ለምሳሌ በእንግሊኛ) መጻፍ ግድ በሚሉ አካባቢዮች በሁለተኛ ተርታ መጻፍ/ማስቀመጥ ።
- የዘመኑ ገዢዮቻችን ለብሄራዊ ቋንቋችን ቅንና ቀናኢ ከሆኑ ይህንን በተመለከት ለማኅብረሰቡና ለየተቋማቱ አስተምሮትና ግንዛቢ መስጠት
- ብሄራዊ ቋንቋችንን የሚያስተምሩ መምህራን፣ የቋንቋ ምሁራንና ሊሂቃን ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያስገደዱኝ ዓይነት ግድፎች ተክታትለው እርማት መስጠት
- ለኢትዮጵያዊነት እሴቶች የምንቆረቆር፣ የምንታገልና ቀናኢ የሆን ሁሉ ለብሄራዊ ቋንቋችን ኅልውና ዘብ መቆም አለብን