>

መፅሃፍ:- “ነጠላ ተባራይ ንፍቅ ስነ-ስሌት” (ባህ ሩ ካሳሁን)

መፅሃፍ:- “ነጠላ ተባራይ ንፍቅ ስነ-ስሌት”

 

መፅሃፍ (Book in Amharic entitled “ነጠላ ተባራይ ጥርንቅ ስነ-ስሌት”)… (Single Variable Integral Calculus).

It is available on Amazon. (Interested individuals can search Amazon Website for “Calculus in Amharic”).

 

< ይህ መፅሃፍ እና ቀድሞ በ፳፻፱  (2017 CE) በርእስ “ነጠላ ተባራይ ንፍቅ ስነ-ስሌት” የታተመው ፅሁፍ ኣላማቸው በትምህርት ቤት ላሉ ተማሪዎች እና ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተማር ለሚጥሩ ሁሉ ጥናታቸውን ለመደገፍ/መደጎም እና  የስነ-ስሌት ፋይዳን እንዲረዱ ለማድረግ ነው።  ኣቀራረቡን ለማቅለል በተቻለ መጠን ተጥሯልና ምናልባት ጠባብ ወይም ውስን ሂሳባዊ ዳራ ያለቸው ኣንባቢዎችም ሆኑ ያለፈ የሂሳብ ጥናታቸውን ለዘነጉ ይረዳል ብለን እንገምታለን።  

     ባጭሩ “ጥርንቅ” (integral) የ”ንፍቅ” (differential) ተቃራኒ ነው። ስለዚህ፣ “ንፍቅ ስነ-ስሌት” (differential calculus) ተግባርን በንኡስ ክፍሎች ከፍሎ እና የክፍሉን “ለከት” (limit) ወስዶ “ቅፅበታዊ የለውጥ ቅልጥፍና” (instantaneous rate of change) እንዳገኘ፣ በሳይንስ እና ምህንድስና ኣግልግሎት እንደሰጠ ሁሉ፣ “ጥርንቅ ስነ-ስሌት” ቅፅበታዊ የለውጥ ቅልጥፍናዎቹን ሰባስቦ በ”መደመር” እና የድምሩን ለከት በመውሰድ የጠቅላላ ለውጡን ውጤት፣ ማለትም፣ ተግባሩን መልሶ በመስጠት ለሳይንስ እና ምህንድስና ታላቅ ኣስተዋፅኦ ይለግሳል። ልገሳውም፣ በኣልጀብራ፣ ስነ-ቅርፅ (Geometry) ወይም ስነ-ዘዌ (trigonometry) ፈፅሞ ሊገኙ ያማይችሉ፣ ከተገኙም ካስፈላጊ በላይ  እጅግ የሚያለፉ ፅንሰ-ሃሳቦችን በቀላሉ እና በፍጥነት ሂሳባዊ ቀመራቸውን ለማግኘት መርዳቱ ነው። 

    ጥርንቅ የንፍቅ ተቃራኒ ነውና ኣንዳንድ ጊዜ ኢ-ኑፋቄ ወይም ኢ-ድናን ይባላል።  በዚህ ቅራኔ በመመርኮዝ፣ ፅሁፉ በምርጥ እና ቀላል የተግባሮች ድናን (derivative) ጀምሮ፣ “ደናኑ ይህ ሊሆን የሚችል ተግባር ምንድን ነው?” ብሎ  በመጠየቅ “ጥርንቅ”ን ያሰተዋውቃል። በተጨማሪም፣ ኣዲስ ፅንሰ-ሃሳብን ለማቅረብ፣ ወደ ፅንስ-ሃሳቡ በሚመሩ ምሳሌዎች እና ጥልቅ ፍቻቸውን በመስጠት ይነሳል።  ፅሁፉ ከሁለት መቶ በላይ ምሳሌዎችን የያዘ ከሞሆኑም በላይ በያንዳንዱ ንኡስ ክፍል መጫረሻ በቂ መለማመጃዎችን ይሰጣል።  የምርጥ መለማመጃ መልሶች በፅሁፉ ኣባሪ ተካተዋል። 

 

Filed in: Amharic