“ኢትዮጵያ በዓባይ ውሃ ልታስከፍለን አቅዳለች”
ግብጻዊ ልሂቃን
– የካይሮን ትርታ ያዛባው፣ ውሃ ከነዳጅና ወርቅ መሰለፍ
እስሌይማን አባይ
ግብፅ ሱዳናን ኢትዮጵያ በውሃ ዋጋ እና ሽያጭ ላይ ያደረጉት ስምምነት ባይኖርም ቱርክ በኤፍራጥስና ትግሪስ ወንዞች በሚያልፈው ሰላም-ፕሮጀክት ለእስራኤል እና ለባህረ-ሰላጤው ውሃ ኤክስፖርት ለማድረግ ስራ መጀመሯን ያወሳል፤ አል ሞኒተር በትንታኔው።
በአሜሪካ ወልስትሪት ገበያ ከሚታወቁት ወርቅ ነዳጅ … በተጨማሪ ውሃም ዋጋ ተቆርጦለት መካተቱ የግብፅ ልሂቃን መባተት አብዝተዋል። በግድቡ ድርድር ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት የማትፈርመው ውሃው በገንዘብ ልትሸጥልን አስባ ነው እያሉ ናቸው። አልሞኒተር ግብፃዊ ምሁራንና ባለስልጣናትን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግሯል። ሞኒተር እንዳስነበበውም የግብፅ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛው አህመድ ሙሳ ጥር ላይ በሳዳ-ኤል-ባላድ ቴሌቪዥን እንደተናገረው “ኢትዮጵያ የጥቁር ዓባይን ውሃ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ትፈልጋለች። ግብፅን በማስከፈል ውሃውን ኤክስፖርት ማድረግ ትፈልጋለች”
ሱዳናዊው ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያና የቀድሞ የካርቱም የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባል አሕመድ አል ፋታ “ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ዕቅዷን የሚያደናቅፍ ስምምነት ላለመፈረም ነው በርካታ አስገዳጅ ውሎችን ውድቅ የምታደርገው” ብለዋል “የኢትዮጵያ ዕቅድ” ይላሉ ፋታ “የኢትዮጵያ ዕቅድ ተጨባጭ ፖሊሲ በመቅረፅና ዋጋ በመተመን ውሃ ለግብፅና ለሱዳን ለመሸጥ ነው”
የቀድሞ የግብፅ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞና ኦማር ለአል-ሞኒተር እንደተናገሩት “ለአባይ ውሃ ዋጋ የመተመንና የመሸጥ ነገር አሁን እንዳዲስ የታሰበ ባለመሆኑ አሁንም ላይ እንደገና ሊቀርብ ይችላል”
ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን ከመገንባቷ በፊት ለእስራኤል ውሃ ለመሸጥ ሀሳብ ማቅረቧን ተናግራለች ፡፡ ግብፅ ይህንን ሐሳብ በመቃወም የናይል ውሃ የሚሸጥ ሸቀጥ ሳይሆን የሕይወት መብት ስለመሆኑ የአፍሪካ ሀገሮችን የማግባባት ስራ አከናውናለች። እናም ትብብር እና መግባባት ብቸኛው የልማት መንገድ ነው” ብለዋል ኦማር ፡፡
አክለውም ኢትዮጵያ አሁን ላይም በግብፅና በሱዳን እንዲሁም በዜጎቻቸው ሕይወት እና ብሄራዊ ደህንነት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከግምት ባላስገባ መንገድ የአባይ ውሃን የመቆጣጠር፣ የመሸጥና ዋጋ የመተመን ፍላጎት አላት፤ ይህ ደግሞ ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው” ብለዋል።
በአል-አህራም የፖለቲካ እና ስትራቴጂካዊ ጥናት ማዕከል የናይል ተፋሰስ ጥናቶች ኃላፊ የሆኑት ሀኒ ራስላን በአሜሪካን አክሲዮን ገበያ ለመጀመሪያ ጊዜ ውሃ እንደ ነዳጅና ወርቅ ዋጋ ተተምኖለት የአክሲዮን ዝርዝር መካተቱ የዓባይ ውሃን ለሽያጭ የማቅረብ ሐሳብ እንዲያንሰራራ የሚያደርግ አደገኛ ጠቋሚ ነው ብለው ያምናሉ።
“ኢትዮጵያ የግድቧን ሙሊት ያለስምምነት መፈፀሟን ከቀጠለችበት ሌሎች ሶስት የታቀዱ ግድቦች ገንብታ የናይል ውሃውን ወደ መሸጥና ዋጋ መተመን ትሸጋገራለች። በዚህ ጊዜም ከግብፅና ሱዳን ለሚቀርቡ የጉዳት ቅሬታዎች fait accompli በሚለው መከራከሪያዋ ላልተማከርኩባቸው ፕሮጀክቶች ጉዳት ተጠያቂ አይደለሁም በማለት ወጥራ ትሟገተናለች” ነው ያሉት።
የቀድሞው የግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ሞሃመድ ናስር አላም ከ 1970 ዎቹ ወዲህ የውሃ ኮታ ለእርሻ ስራ ድርሻ መውጣት ከጀመረ ወዲህ የውሃ ሽያጭና ግዥ መታየት ጀምረዋል። በአክሲዮን ገበያው ላይ ውኃን ለንግድ ማዋል አዲስ ሁነት ቢሆንም በአገሮች መካከል በሚደረጉ ስምምነቶች ላይ ሊጠቃለል የማይችልና ጉዳዩን መቆጣጠር ለዓለም አቀፍ ሕግጋት ነው። ከናይል ተፋሰስ አገራት ውሃን የመሸጥና ዋጋ የመተመን ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢቀርቡም ግብፅ በግልፅ ተቃውማለች፤ ምክንያቱም ለብሄራዊ ደህንነቷ አደገኛው ስጋት ስለሆነ”
የቀድሞው የመስኖና ውሃ ሀብት ሚኒስትር አማካሪ ዲያ ኤል ዲን አህመድ ሁሴን ኤል-ኮሲ “ግብፅ የአባይ ውሃን የመሸጥ እና ዋጋ የማውጣት ሀሳብ ጎጂ ስለሆነ መቀበል አትችልም ብለዋል።
የውሃ ኤክስፖርት ዋጋ
ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ኤክስፖርት ላይ ዋጋው የሚተመነው በሻጭና ገዢዎቹ መካከል ነው። የዋጋው ሁኔታ በ desalination ውሃን ማጣራት ከሚጠይቀው ወጪ ጋርም ይገናዘባል። ቱርክ ለእስራኤል ለመሸጥ የተነጋገረችበት ዋጋ በሜትር ኪዩብ $ 75 ሳንቲም መሆኑን በርካታ ጥናቶች አስቀምጠውታል። ለመጠጥ ደረጃ ተብሎ የሚላክ ውሃ ዋጋ ከሌላው የውሃ አቅርቦት የተለያየ ደረጃ ነው የሚሆነው።
ግብፅና ሱዳን ከኢትዮጵያ የሚያገኙት ዓመታዊ የውሃ መጠን ቱርክ ባስቀመጠችው ተመን መሠረት በዓመት $ 40 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የሚያስከፍል ይሆናል።
በዲሴምበር 2021 አሜሪካ ላይ በቀረበ የውሃ ተመን መሠረት ደግሞ አንድ አክር ጫማ ውሃ $ 496 ዋጋ አውጥቷል። አንድ ሜትር ኩብ 0.8 acre-foot ገደማ ነው። በዚህ ስሌት ግብፅና ሱዳን ከጥቁር ዓባይ በያመቱ 50 ቢሊዮን ሜትር ኩብ አገኙ ብንል 40 ቢሊዮን acre foot ይሆናል፤ አሃዙን በ በ 496 ዶላር ስናባዛው የማይታመን የቢሊዮን ዶላሮች አሃዝ ያስነብበናል።