በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ላይ ሁለተኛው ዙር የውሃ ማጠራቀም አቅድና ያስነሳው ውዝግብ፣
እውን የውሃ ሙሊት በሚካሄድበት ጊዜ ግብጽ በውሃ ጥም ትቃጠል ይሆን ?
ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)
ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በታላቁ የአባይ ወንዘ ግድብ ዙሪያ ፣ በተለይም በግድቡ ላይ ስለሚጠራቀመው የውሃ መጠንና ስለሚሰጠው አገልግሎት በተመለከተ ለበርካታ አመታት ሲወያዩ እንደነበረ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ በሶስቱ ሀገራት መሃከል ሲደረግ የነበረው ውይይት እጅጉን አስቸጋሪ ነበር፡፡ አስቸጋሪነቱም የሚነጨው ደግሞ ከግብጽ አልጠግብ ባይነት፣ እኔ ብቻ ተጠቃሚ ልሁን የሚለው የትምክህት ባህሪዋ፣ለምእተ አመታት የአባይን ወንዝ ትሩፋት በብቸኝነት(የአንበሳውን ድርሻ ) ይዤ ልቀጥል በማለቷ ይመስለኛል፡፡ በሰፊው ስናየው ወይም ስንመረምረው ግብጽ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በቅኝ 1959 በቅኝ ገዢ እንግሊዝ በተረቀቀው የአባይን ወንዝ በብቸኝነት ለመጠቀም በሚስችለው ውል ላይ ተጣብቃ በመቀጠሏ ነው፡፡ ( ይህ የ1959 ውል የአባይን ወንዝ ለሱዳንና ግብጽ ብቻ እንዲጠቀሙ የሚፈቅድ ውል ነበር፡፡ ለሌሎች የአባይ ተፋሰስ ሀገራት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአባይ ወንዝ ላይ የመጠቀም መብታቸውን የገፈፈ ነበር፡፡
በርግጥ ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት የ1959ኙ (እ.ኤ.አ.) ስምምነት ላይ አልተካፈሉም ወይም ስምምነቱን አልፈረሙም ነበር፡፡ ከዚህም እልፍ በማለት እ.ኤ.አ. በ1959 የተፈረመውን ውል ኢትዮጵያ በግዜው ተቃውማ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ እንደ ጎርጎሪሲያኑ አቆጣጠር 2015 ሱዳን ካርቱም ላይ ሶስቱ ሀገራት መሪዎች ከፈረሙት የመርህ መግለጫ, for the Declaration of Principle (DoP) በቀር ሌላ ስምምነት የለም፡፡
በነገራችን ላይ በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ላይ በየደረጃው ውሃ ከመሙላት አኳያ ሶስቱም ሀገራት በዋና ዋና ጉዳዮች እንደተስማሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የመጨረሻው ስምምነት ላይ ገና አልደረሱም፡፡ እንደ ዜና አውታሮች ዘገባ መሰረታዊ ችግሩ ከሆነ የግብጽ ጥያቄ ሱሪ በአንገት (bottleneck ) የመሆኑ ጉዳይ ሲሆን የሱዳን ተለዋዋጭ አቋምም ቢሆን ለኢትዮጵያ ራስ ምታት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ለአብነት ያህል ሱዳን ከምታነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መሃከል የላይኛው የናይል(አባይ) ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት በውሃ ላይ ልማት ሲሰሩ አሰገዳች ውሎችን እንዲፈርሙ ፍላጎቷ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ውሃን በአግባቡ ለመጠቀም የሚደረጉ ውሎች ሁሉንም የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ማሳተፍ አለበት የሚል አቋም አላት፡፡ ከታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ጋር የማይገናኙ የውሃ ልማቶች ማለት ነው፡፡
በቅርብ ግዜ ውስጥ የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣኖች በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫዎች ከእውነት ጋር የሚጋጩ ነበሩ፡፡ ለአብነት ያህል የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩት ታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ የሱዳን ዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡ የሱዳን ውሃና መስኖ ሚንስትር በበኩላቸው ኢትዮጵያንና ግድቡን እየገነባ የሚገኘውንና እና የጣሊያኑን አለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ድርጅት ሳሊኒን (the dam Contractor Salini Impregil ) ለመክሰስ ፍላጎት እንዳላቸው የሚያመላክት ድንፋታ በአደባባይ ተናግረውም ነበር፡፡
በእውነቱ ለመናገር እነኚህ የሱዳን ባለስልጣናት ታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ የሱዳን ህዝብ በሀይለኛ ጎርፍ እንዳይጠቃ ስለሚሰጠው ፋይዳ፣ እንዲሁም ወደ ሱዳን የሚፈሰው የአባይ ወንዝ ውሃ መጠን እንዳይቀንስ በማመጣጠን የሱዳን ህዝብ ለመስኖ እና ለመጠጥ ውሃ እንዳይቸገር ጥቅሙ የትዬየሌሌ መሆኑን ለመናገር መንፈሳዊ ወኔ ከድቷቸው ማየት ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራልም፡፡ እንደ ዶክተር አለም ገብርኤል የመሳሰሉ የውሃ ምህንድስና ጠበብት በተለያዩ ጥናታዊ ወረቀቶቻቸው ላይ እንዳስቀመጡት ከሆነ ግብጽ ለብዙ ክፍለዘመናት ካጋጠማት የሀይለኛ ጎርፍ አደጋ ከተደጓት ዋነኛውና ብቸኛው ፕሮጄክት የታላቁ አባይ ወንዝ ግድብ በግንባር ቀደም የሚጠቀስ ነው፡፡
640 ሜትር ከፍታ የውሃ ሙሌት ለመድረስ 7 አመታት ሊፈጅ ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ላይ የመጀመሪያውን የውሃ ሙሊት ያደረገችው እንደ ጎርጎሮሲያኑ
አቆጣጠር ሀምሌ 21 2020 እንደነገር የሚታወስ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የታላቁ አባይ ወንዝ የውሃ ግድብ በጠቅላላው ወደ 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትርስ (4.9 billion cubic meters (BCM) of storage )የውሃ መጠን ማጠራቀም እንደሚችል የሚያሳዩ የውሃ መሃንዲሶች ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጀመሪያው የውሃ ሙሊት ሂደት ወደ ከ90 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ በቀን፣1042 ኪዩቢክ ሜትርሰ ፐርሰከንድ ማመንጨት ይችላል፡፡
over 90 million cubic meter (MCM) per day, or over 1,042 cubic meters per second (cms) ወይም እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሀምሌ አጋማሽ 2020 ላይ የተጠቀሰውን የውሃ መጠን አመንጭቷል፡፡ ይህ መረጃ የተገኘው ከኢትዮጵያ መስኖና ውሃ ሀይል ሚንስትር ሲሆን ኢትዮጵያ በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ውስጥ በምትሞላበት የሐምሌ ዝናብ ወቅት ሱዳን ግዛት ውስጥ የሚገኘው ‹‹ at El Diem station ›› ላይ የሚገኘው የውሃ ልኬት እንደሚያሳየው በደረቅ (በበጋ) ወቅት ከሚከማቸውየውሃ መጠን አራት እጥፍ እንደሚበልጥ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ከዚህ መራር እውነትበተቃራኒው የሱዳን ውሃና መስኖ ሚንስትር የሆኑት ሚሰትር ,( Yasser Abbas,)ታላቁ አባይ ወንዝ ግድብ የውሃ ሙሊት በሚከናወንበት የሐምሌ ወር የዝናብ ወቅት ወደ ካርቱምና ሌላ አካባቢ የሚፈሰው የአባይ ወንዝ ውሃ መጠን ሊቀንስ ይቻለዋል ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡
በእውነቱ ለመናገር የአባይ ወንዝ ፍሰት ከበጋው ወቅት ጋር ሲወዳደር አራት እጥፍ የውሃ ፍሰት መጠን ባለበት በዚህ ክረምት ግዜ የውሃ እጥረት ሊከሰት ይችላል የሚለው የሱዳኑ ባለስልጣን አስተያየት ውሃ የሚቋጥር አይደለም፡፡በነገራችን ላይ በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ውስጥ የውሃ ሙሊት ሱዳንን እንዳማይጎዳት የሚያሳዩሌሎች ምክንቶችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከታላቁ የአባይ ግድብ በታች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሁለት ግድቦች ይገኛሉ፡፡ የግድቦቹ መጠሪያም ሮሳሪስ እና ሴናር( Rosaries and Sennar) ይባላሉ፡፡ እነኚህ ግድቦችየአባይ ወንዝ ውሃ ወደ ካርቱም ሱዳን ከመድረሱ በፊት የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ ሁለቱ በሱዳን ግዛት ውሰጥ የሚገኙት ግድቦች ወደ ካርቱም ሱዳን የሚፈሰውን የአባይ ውሃ መጠን የሚቀንሰው ከሆነ ሱዳን ራሷንመመርመር ማጥናት አለባት፡፡ ወደ ታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ የውሃ ሙሊት ላይ የሚሰጠው አስተያየትከእውነት የራቀ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ተስፋ አንቆርጥም፡፡ መራሩን እውነትም ከመጋፈጥ ገሸሽ አንልም፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው ኢትዮጵያ በታላቁ አባይ ግድብ ውሰጥ ሁለተኛውን የውሃ ሙሊት ለማከናወንመንፈሳዊ ወኔ ታጥቃ ተነስታለች፡፡ እንደ የኢትዮጵያ ከፍተኛ መንግስት ባለስልጣናትና የሚመለከታቸውየውሃ ምህንድስና ጠበብት አቅድ ከሆነ ኢትዮጵያ ተጨማሪ 13.5ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትርስ ተጨማሪ የውሃ በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድብ ውስጥ ታጠራቅማለች፡፡ እንዲሁም የግድቡን ከፍታ ወደ 595 ሜትር ለማሳደግ እንደታቀደ ይገመታል፡፡
በነገራችን ላይ አንዳንድ የጥናት ድርጅቶች በጥናታቸው ላይ እንደተነበዩት ከሆነ በያዝነው 2021( እ.ኤ.አ.) የዝናብ መጠኑ በቂ ነው( እርጥበት አዘል አየር እውን ይሆናል) ስለሆነም ግብጽም ሆነች ሱዳን ከታላቁ የአባ ወንዝ ግድብ ውሃ ሙሌት አኳያ የሚሰጡት አስተያየት ሚዛኑ የተሰበረ ነው፡፡ ታላቁን የአስዋንየውሃ ግድብ ከብዙ አመታት በፊት ገንብታ ለዘመናት የሚተቅማትን ውሃ ያጠራቀመችው ሱዳን በውሃጥም ልቃጠል ነው ማለቷ ስላቅ ነው፡፡ እንደ ዶክተር የመሳሰሉ የውሃ ምህንድስና ጠበብት በጥናታቸው
እንደደረሱበት ከሆነ ከሰኔ ወር ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወራት ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ በታላቁ የአባይ ወንዝ ግድቧ ላይ የተከለቻቸውን ተርባይኖቿን ለማንቀሳቀስ ሙከራ በምታደርግበት ግዜ ወደ ግብጽና ሱዳን ምድርከ27 እስከ 45 ቢሊዮን ሜትርኩብ የውሃ መጠን ይፈሳል፡፡ በነገራችን ላይ ድንገት ከፍተኛ ድርቅ ወይም ደረቅ የአየር ንብረት ቢከሰት የኢትዮጵያ መንግስት በወንድማማችነትና እህትነት መንፈስ መሰረት ሁለተኛውን ውሃ ሙሊት ጉዳይ ለማጥናት አቅድ ይዞ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስለሆነም ግብጽም ሱዳን በታላቁ አባይ ወንዝ ግድብ ውስጥ የውሃ ሙሊት መካሄዱ ወደ ግዛታችን የሚፈሰውን የአባይ ወንዝየውሃ መጠን ሊቀንስ ይችላል የሚለው መከራከሪያቸው ምክንያታዊ አይመስልም፡፡ እነርሱ ዋነኛ ምክንያት የቀድሞ የበላይነታቸውን ( በተለይም ግብጽ ) ለማስጠበቅ ስለሚፈልጉ ነው አበክረው በታላቁ የአባይ ውሃ ግድብ ውስጥ በቶሎ ፣በግዜው፣ የውሃ ሙሌት እንዳይካሄድ መጠነ ሰፊሴራዎችን የሚገነጉኑት፡፡
እንደ መደምደሚያ
ኢትዮጵያ በጥንታዊው ታላቅ ስልጣኔዋ ዘመን የአባይን ውሃ ሙሉ ለሙሉ መዝጋት በምትችልበት ዘመን እንኳ ውሃ ልከልክል ብላ አታውቅም ፡፡ ኢትዮጵያ በሠራዊት ኃይል ጭምር ከግብጽ እጅጉን የበለጠች በነበረችበት ጊዜ ‹‹አባይን ገድቤ የግብጽን ጉሮሮ ልዝጋ›› እንዳላለች ታሪክ ምስክር ነው፡፡
አለቃ ደስታ ተክለወልድ ዘ-ብሔረ ወግዳ ገበታዋርያ በተባለውና በ1928 ዓ.ም. በታተመው መጣፋቸው ገጽ 41 ላይ ይህንኑ የሚያስረግጥ ግጥም እንዳላቸው ማስታወስ ጠቃሚ ነው ፡፡ እንዲህ ይላል፡-
…ያባቶቻችንን ፈረስና ጓዝባህርም አላገደው እንኳን ፈሳሽ ወንዝበሰሜን አፍሪቃ ያጤ ዳዊት ጫማሱዳንና ኖባን ሲረግጥ እንደ አውድማየግብጽን ጉሮሮ አባይን መዝጋት
በጣታቸው ነበር እንደቀለበት፡፡
ይህ ከጥንት ጀምሮ ያለው የኢትዮጵያ አቋም ዛሬም ቢሆን የተከበረ ነው፡፡ አገራችን ‹‹አባይን ገድቤ የግብጽን ጉሮሮ እዘጋለሁ›› የሚል ሃሳብ ጥንትም አልነበራትም፣ ዛሬም የላትም ፡፡ ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጪያ የሚሆን ኃይል እየሰጠ የሚያልፍ ግድብ ነው እየሰራች ያለችው ፡፡ ይህንንም የታችኛው የተፋሰሱን አገራት አሳምና ፣ መላውን ህዝቧን አነቃንቃ ፣ በሙሉ ቁርጠኝነት ነው የገባችበት ፡፡
በዚህም ለግብጽ የሚሄደው የውሃ መጠን ትርጉም ባለው ሁኔታ ሳይቀንስ ኃይል አመንጭቶ የሚሄድ ፣ የግብጽን መሰረታዊ ጥቅም የማይነካ፣ ግብፆችን ጉልህ ሥጋት ውስጥ የማይጥል ፕሮጀክት ነው ፡፡ የግብፅ አንዳንድ አጉራዘለል ፖለቲከኞችና አክቲቪስት ተብዬዎች ግን ይህን መሬት ላይ ያለ ሀቅ ሊያምኑ አልቻሉም ፤ አይችሉምም…….