>

ስም ባህልና ታሪክን መቀየር የዘር ማጥፋቱ አካል ነው!

ስም ባህልና ታሪክን መቀየር የዘር ማጥፋቱ አካል ነው!

 

እውን ዐማራ የጀመረው የህልውና ትግል የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው አይነት ያልታቀደ፣ ያልተመከረበት፣ የአፈጻጸምና የመነሻ ችግር ያለበት ነውን? ወይስ ዐማራ እንደሌሎች ጥገኛ ካልሆነ ማሸነፍ አይችልምን? ዐማራ በግብታዊነትና በአጭር ጊዜ ውጤት ላይ የተንጠለጠለ ትግል ጀምሮ ከሆነ ያለጥርጥር ለጠላቶቹ እድሜ መርዘም የራሱን አስተዋጽኦ ይጨምራል። በተቃራኒው የዐማራን ጉዳትና የሚታየውን የዘር ጭፍጨፋ ብቻ ሳይሆን በረዥም ጊዜና በስልታዊ መንገድ ዐማራን ለማጥፋት የተነደፈውን እቅድ የተረዳና የነቃ ለሞትም ሆነ ለሚቀበለው መስዋእትነት የቆረጠ ትውልድ ይዞና የማሸነፍን ፣ ስርዓት የመለዎጥንና ህልውናን የማስከበርን ዓላማ ያነገበ የማይመለስ ትግል ነው የተጀምረው።

በዐማራ የህልውና ትግል የገጠሙ ተግዳሮቶች በአብዛኛው ካለመደራጀት የመነጩ ናቸው ቢባልም በዋናነት ግን ጸረ ዐማራ የሆኑ ቡድኖች የሚከተሉትን ስልት አንድ በአንድ ካለመረዳት የመጡ ናቸው። ዐማራ አቅመ ቢስና ሌሎችን ለማንገስ የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ ለሌሎች ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያ እንዲሆን የሚሰሩ የእናት ጡት ነካሾች በርካታ ናቸው። የዐማራን ታሪክና ባህልን በማጥፋት ከሚኖርበት ከየትኛውም ቦታ በማሳደድ በማሰርና በመግደል የተገለጠ ክንውን እየተመለከቱ በፈቃደኝነት ለዚህ ሂደት ግብ መምታት ተባባሪ ከዐማራ ማህጸን የወጡ ፍጡራንን ማየት አስገራሚ ነው። ኦሮሙማም ሆነ ትህነጋዊው የቀድሞው ስርዓት ዐማራን ለማጥፋት የሄዱበት ርቀት እጅግ ያስገርማል ። አሁን በአዲስ አበባና አካባቢዋ ዐማራን ለማጽዳት እየተደረገ ያለው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በወልቃይትና ራያ ሲደረግ ከነበረው የአካሄድ ልዩነት እንኳ ሳይቀይር እየተከናወነ ይገኛል። በአዲስ አበባ የሚገኙ ነባር ስሞች ፣ ህንጻዎች መንገዶችና ዐማራ በብዛት የሚኖርባቸው ስፍራዎች ሁሉ ተቀይረዋል። ይህ ለአብዛኛው ሰው ምንም አይመስለውም ፤ የዘር ማጥፋቱ ሂደት አንደኛው መንግድ መሆኑና ትህነግ ለሃያሰባት ዓመታት የሰራመት ዘዴ ነው። እስኪ ከስር በወልቃይትና በስሩ ባሉ ወረዳዎች የነበሩ የከተማና የቀበሌ ስሞችን እንዴት እንደተቀየሩ እንመልከት። መረጃው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ‘’ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት በውልቃይት ጠገዴና ጠለምት የምርምር ውጤት ‘’ ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ ነው።

ከሰሞኑ ብዙዎቻችን እንደሰማነው ፋኖ ከትህነግ ትእዛዝ ውጪ ምንም ማድረግ አይችልም የሚልና ለዚህም ማስረጃ ብሎ ማንም የፋኖ መሪ ወልቃይት ወይም ራያ የዐማራ ነው ብሎ አይናገርም የሚል የህወሃት ወታደር ድምጽ በማህበራዊ ሚዲያ ሲንሸራሸር ስሰማ ዐማራን ምን ያክል ቢንቁት ነው? የሚል ስሜት ተሰማኝና ስለ ጅምላ መቃብሮች ስላደረጉት ተቆጥሮ የማያልቅ ግፍ ገና ብዙ መዘርዘር እንዳለበት አመንሁ። ዐማራ በልጆቹ ነጻነቱን ህልውናውንና ክብሩን ያስመልሳል። የምትሰራዋ ፖለቲካ ሁሉ በጊዜው እየጠራችና የጠላቶቻችንንም ማንነት እየገለጽን እንቀጥላለን።ከልጆቹና ከማንነቱ እንጂ ከመቀሌ ወይም ከአዲስ አበባ የሚመጭ የዐማራ ነጻነት የለም።

ድል ለዐማራ ህዝብ!

አዲስ ተስፋ

@AmharaSurv78790

 

 

Filed in: Amharic