>
3:04 am - Monday July 4, 2022

በኬንያ ስደተኛው መሃል ሰርገው በመግባት የሚሰልሉ የወያኔ ሰላዮች አዲስ አበባ ከትመዋል::

ምኒሊክ ሳልሳዊ

ሰሞኑን የዲያስፖራ ሳምንት በሚል የወያኔ በዓል ላይ ለመገኘት ወደ አስር የሚጠጉ የወያኔ ሰላዮች ከኬንያ ናይሮቢ በዳያስፖራ ስም ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል።እነዚህ በስለላ ስራ ተሰማርተው ለረጂም አመታት በናይሮቢ መንግስትን ሲያገለግሉ የነበሩት ግለሰቦች በተባበሩት መንግስታት ስደተኛ ኤጀንሲ(ዩኤነኤችሲአር)ተመዝግበው የቆዩና የስደተኛ ወረቀት ያላቸው ናቸው። ሲሉ ኬንያ የሚገኙ በወያኔ ግፍ ተማረው የተሰደዱ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በውስጥ መስመር ለምኒሊክ ሳልሳዊ ያደረሱት መረጃ ይጠቁማል::

በኬንያ የሚገኙ ንጹሃን ስደተኞች እንደተናገሩት ግለሰቦቹ ወደ ሀገር ቤት ከመመለሳቸው በፊት በናይሮቢ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሰዎቹ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ጋር ያላቸው ግንኙነት ያሳስባቸው እንደ ነበረ በተለያዩ ተቋማት ፍርሀታቸውን ሲገልጹ የቆዩ መሆናቸው ተዘግበዋል። እነዚህ ሰላዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አካባቢ አገልግሎት በማድረግ የሚታወቁ ሲሆኑ ቤተክርስትያኒቷን እንደ ሽፋን በመጠቀም የተለያዩ የስለላ ስራዎችን ሲሰሩ እንደቆዩ ታውቋል።ኬኒያ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሲሆን ከነዚህ መሀል ሀምሳ የሚሆኑት ጋዜጠኞችና የሰብ አዊ መብት ተሟጋቾች መሆናቸው ይታወቃል።

ንጹሃንኑ ስደተኞች ያላቸውን ተጨማሪ መረጃ በማጣቀስ እንደገለጹት ወያኔ የዲያስፖራ በዓል ብሎ በሚያከብረው ሳምንት ላይ ለመገኘት ወጪያቸውን ሸፍኖ ከኬንያ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ ከጎረበት አገሮች ወደ 5000 ተላላኪ ጆሮ ጠቢዎችን ዲያስፖራ ናቸው በሚል ሽፋን ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዙ ሲታወቅ መሬት እና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸውዋል:;በጎረቤት አገሮች በስደተኛ ስም ተመዝግበው የሚገኡ እነዚህ የወያኔ ተላላኪዎች ንጹሃኑን ዜጎች አሳልፈው በመስጠት ስራ ላይ የተሰማሩ የነበሩ እና ተመልሰው ወደነበሩበት የጎረቤት አገር ከመምጣታቸውም በፊት በጆሮ ጠቢነት እና መረጃ አቀባይነት ስልጠና እና መመሪያ እንደሚሰጣቸው ታውቋል::ዲያስፖራ ማለት በውጪ ሃገር የተማሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል ስያሜ መሆኑ ሲታወቅ በኬንያ እና በተለያዩ የጎረቤት ሃገሮች ወያኔ ጭኖ የወሰዳቸው ግለሰቦች ዲያስፖራውን የማይወክሉና የዲያስፖራን ስያሜ የማያሟሉ የወያኔ ተላላኪዎች እንደሆኑ ንጹሃኑ ስደተኞች ይናገራሉ::

Filed in: Amharic