>
6:46 pm - Thursday February 2, 2023

ከተመስገንነቱ ፈቀቅ ያላለው ተመስገን ደሳለኝ! [ታሪኩ ደሳለኝ]

በ20/8/08ዓም ሐሙስ እለት በእስር ቤት ተገኝቼ ከተሜን ጋር እየተጫወትን በመሀል ተሜ “ዛሬ ሆስፒታል ትሄዳለህ ብለውኛል” አለኝ። አላመንኩኝም የህመሙ ደረጃ ምን ያሃል እንደደረሰ ተሜን የጠየቁት ሁሉ ያቁታል። ከአንድ አመት ከአምስት ወር በኃላ ወንድሜ ሊታከም ነው። እንዴት ደስ ይላል። በቃ አሁን በአሉ በአል ሆነ። ከ 2 ቀን በኃላ ተመልሼ ስመጣ ለውጡን አያለሁ። እነዚህን እያስብኩ የሰሞኑን የተሜን የእስር ቤት አክርሞት ሳልጠይቀው መቆየቴ  እየገረመኝ። “እሺ የውስጡ ጉዳይ እንዴት ነው?” አልኩት ተሜ ፈግግ አለ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኑ ፈገግታ ወይ ተሜ አልኩኝ ለራሴ። ሆስፒታል ስለሚሄድ ተሰነበብተን ሰወጣ የሰሞኑ ጉዳይ እያሰብኩ ነው።

Journalist Temesgen Desalegn- By Tariku Desalegnነገሩ ይህ ነው። ከ13 ቀናት በፊት 3 እስረኞች ተመስገን ወደ አለበት ከፍል መጡ። ለነዚህ አዲስ እስረኞች ነበር እስረኞች ቦታ ሊሰጧቸው ሲሰናዱ በፊት እስረኛን አስገብተው ብቻ የሚወጡት ወታደሮች አሁን አዲሶቹን እስረኞች አስገብተው አልወጡም። ሦስቱን እስረኞች ይዘው ተመስገን ወደ ሚተኛበት ፍራሽ በመሄድ ተሜ አጠገቡ የሚተኙትን ነባር 3 እስረኞች ከቦታቸው አባረው በምትካቸወው በተመስገን ዙሪያ አዲሶቹ ታሳሪዎች እንዲተኙ አድርገው ወጡ። እንዲህ አይነት ድርጊት ተደርጎ ስለማያውቅ ለስረኞቹ ሁሉ በሁኔታው ግራ ገብቷቸው ተመስገንና የከበቡትን እንግዳች ላይ አፈጠጡ። ተመስገን ለአዲሶቹ እስረኛ ከነበረው ምግብ እራት እንዲበሉ ገበዛቸው። እንቢ አሉ። ቆሎ ሰጣቸው። የግዳቸውን ቆንጠረው ቀመሱ።

በንጋተው እስረኟች ለቆጠራ ሲወጣ እነዚህ እስረኞች ወደ ቆጠራው ቦታ ሳይሆን ቀጥታ ወደ ዝዋይ እስር ቤት አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ቤሮ አመሩ። ይህም ሁለተኛው የእንግዳ እስረኟች ድርጊት ነው። እነዚህ እስረኟች አልተቆጠሩም እንደውም ከምሳ በኃላ ተመለሰው ገቡ። የዛን እለት ማታ በድንገት ከምሽቱ 5 ሰዓት ሲል ያለ ወትሮ የእስር ቤቱ በር ከፈተው የገቡት ወታደሮች “ፍተሻ አለ” በማለት ቀጥታ ተመስገን የተኛበት ቦታ በመምጣት የተመስገንን እቃ ብቻ ከአዲሶቹ እሰረኞች ጋር በመሆን እቃዎቸን በረበሩ አገለበጡ በመጨረሻ ሳሙናን ሶፍት ሳይቀረ ወስደውበት ሄዱ። እንግዲህ ይህም ሌላው እንግዳ ነገር ነው።

እነዚህ እስረኟች ወደ ተመስገን የአስር ክፍልና የመተኛ ቦታ ከመጡ በኃላ ማንም እስረኛ ከተመስገን ጋር እንዳይሆን ተደርጓል። በተለያየ ግዜ አዲሶቹ እስረኟች ተመስገን ለፅብ እንዲገበዝ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው። እንዲሁም ተመስገን እኛን ለማናገር ሆነ በተለየ መክኒያት ከእስር ክፍሉ በወጣ ግዜ እነዚህ እስረኞቹ የተመስገንን እቃዎች የፈትሻሉ። ያለውን ሆኔታውን ለኮማንደር አሰፋ ያሳውቃሉ።

አዲሶቹ እስረኟች ከሁት ወር በፊት እስከ የካቲት 2008ዓም ድረስ በመንግስት ደሞዝ የሚከፈላቸው ሁለቱ የሻንበልነት ማአረግ ያለቸው ወታደሮች ነበሩ አንዱ ደግሞ የቤሔራዊ ደንት አበል ነበረ። ዛሬ እስረኛ ሆነው የመጠት ተጠሪነታቸው ለእስር ቤቱ አዛዥ የሆኑት አነዚህ ሰዎች ነገ ከነገ ወዲያ በተመስገን ላይ ምን እንደሚያደርጎ መገመት አስቸጋሪ አይሆንም።

ይህ እስር ቤት ተመስገን ከገበበት ግዜ ጀምሮ አለኝ የሚለውን የሀይልና የማሰቀያ የጉልበት መንገዶች ሁሉ እየተጠቀመ እዚህ ደርሷል።
ተመስገን የእስር ቤቱ የቅጣት ቤትና የጭለማ ክፍል የዘውትር ደንበኛቸው አድረገውታል። በፈለጉም ግዜ አሁን ማንም አይጠይቀውም አሁን ቤተሰብ ብቻ አሁን ደግሞ ወዳጅ ብቻ ይጠይቀው እያሉ ተስለቀዋል። ህመምህንም አትታከመም አታነብም ከእስረኛ ጋር አተወራም በማለት ከስረኛች ሁሉ በተለየ በስቃይና በእንግልት ውስጥ እንዲቀመጥ አድርገውታል። “ሀሳቡን በነፃነት በመጠቀሙና በመፃፉ ብቻ” የታሰረው ተመስገን ይህ ሁሉ ሲሆን ከተመስገንነቱ ፈቅቅ እንኳን አለማለቱ እኛን ያበረታናል።

እሁድ 23/08/08ዓም

ከሁት ቀናት በኃላ የትንሳኤ ዕለት ተሜ ጋር ለመሄድ ከቤት ስወጣ የአዲስ አበባ ዝናብ ተቀበኝ። ዛሬ ዝናብ ቢመታኝም አልበሰብስም። ዛሬ ብርዱ የከፋ ቢሆንም አይበርደኝም። ምክኒያቱም ሀሙስ ዕለት ሆስፒታል ትሄዳለህ የተበለው ተሜ ሻል ብሎት የማይበት ቀን ስለሆነ። ቃሊቲ መነሀሪያ ስደርስ በአል ስለሆነ ወደ ዝዋይ የሚሄድ መኪና የለም። ወደ ግራ ባይ ቀኙን በመለከት ዝዋይ የሚል መኪና አጠሁ። ሻሸመኒ አዋሳ ወደ ሚል መኪና ሄድኩኝ “እስከ ዝዋይ ልግባ” አልኩት “በአዋሳ ሂሳብ ከከፈልክ” አለኝ ክፍያው ከእጠፍ በላይ ቢሆንም አማራጭ የለኝም ገባው ቦታ የለም ጉማ ላይ ተቀመጪ ሄድኩኝ።

ዝዋይ እስር ቤት ስደርስ የቀደመኝ ሰው አልነበረም። እናታችን የሰራችውን የበአል ዶሮ ወጥ አስፈትሺ ተሚን የማገኝበት ቦታ ሄድኩኝ።
ተሜ ሲመጣ አየሁት እስከርቭ አድርጉል ካኪ ሸሚዝና ግራጫ ሱሪ ለብሷል ከተቀመጥኩበት ተነሳው አረማመዱን አስተዋልኩ ረጋ ብሎ ነው የሚራመደው። ስላምታ ተለዋውጠን ከጨረስን በኃላ። በችኳላ “ሆስፒታ ወሰዱክ ወይ?” አልኩት “ባቱ ሆስፒታል ወሰዱኛ” አለኝ ባቱ ሆስፒታል የዝዋይ ከተማ ትልቁ የመንግስት ሆስፒታል ነው። ፈገግታዬ ጨመረ “ምን አለሁ” አልከት “አራት ሆነን ነው የሄድነው 3 እራጅ ተነስተው እኔ ጋ ሲደርስ የእራጁ ማንሻ ተበላሸ አሉኝ” አለኝ “ምን ማለት ነው” አኩት “እኔ ልነሳ ስል ተበላሽ” አለኝ ሳቀ መሳቁ ግራ አገብቶኝ “ምንድነው” አልኩት “ዶክተሩ ከመጣህ አይቀር ደምና ሽንት ተመርመር ማለቱ ገርሞኝ ነው” አለኝ ወደው አይስቁ የሚባለው ለካ እንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ነው እኔም ሳኩኝ። “በሚቀጥለው ሳምንት ትሄዳለህ ብለዋል” አለኝ “አዲሶቹ እስረኟችስ” አልኩት “አሉ አለሁ” አለኝ። በደንብ ተመለከትኩት ከሞራሉ ማማው ላይ ወረድ አለለም በነበረበት ነው። እኔ ግን ለሊት የዘነበብኝ ዘናብ አሁን አበሰበሰኝ የበረደኝ ብረድ ሲንቀጠቅጠኝ እየታወቀኝ ነው። እንግዲህ የሚቀጥለውን ሳምንት የራጅ ማንሻ ማሽኑ እንደማይበላሽ ተስፋ አደርገለሁ። አዲሶቹም እስረኟች ምን ያደርጉ ይሆን እያልኩ በስጋት እጠብቃለሁ።
ለሀገሬ ስል ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው ያልከውን እያሰብኩ ወንድሜ ከነ ብርታትህ ያቆይህ እላለሁ።

Filed in: Amharic