>

የህይወት ጉዞ [አርአያ ተስፋማሪያም]

Niguse Gebire with his wife Yetmwork JakamaKeloንጉሴ ገብሬ ከ30 አመት በላይ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ያገለገለ ባለውለታ ነው። በደርግ ዘመን ተጨዋቾች በሄዱበት አገር ሲኮበልሉ ሁለት ተጨዋቾች ብቻ ይመለሱ ነበር፤ ንጉሴ ገብሬና ሙልዓለም እጅጉ ናቸው። በርካቶች በአንዴ ሲጠፉ የሚቀርብላቸውን የእንጥፋ ጥያቄ አይቀበሉም ነበር። ይህ አቋማሸው ለአገራቸው ያላቸውን ጥልቅ ፍቅርና ክብር ከማመላከቱ ባሻገር በአንድ ወቅት እንዲህ ተብሎ ተቀልዶ ነበር፤ “ንጉሴ አውሮፕላን ቢያጣ እንኳን በእግሩ አቆራርጦ ይመለሳል” ተብሏል።..ከጥቂት አመት በፊት በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን ውድድር በእንግድነት የተጋበዘው ንጉሴ ገብሬ በቀድሞ ጓደኞቹ “እዚሁ ቅር” ተብሎ ሲጠየቅ ..በጭራሽ ብሎ ነው የተመለሰው። እነዮሀንስ ሰሀሌ ኮብልለው አሜሪካ ሳይገቡ በፊት ንጉሴ እድሉ ነበረው፤ ግን አላደረገውም። የንጉሴ ውለታ ግን ተገፍቷል። በኳሱ የማይታወቁ ከክለብ እስከ ታዳጊና ብ/ቡድን እንዲያሰለጥኑ ሲደረግ፣ ያውም ከፍተኛ ደመወዝ እየዛቁ ያለውጤት፣..ንጉሴ ግን አስታዋሽ አጥቷል። ..የንጉሴ ባለቤት የትመወርቅ ናት። የስመጥሩ አርበኛ የጄ/ል ጃጋማኬሎ ልጅ ናት – የትመወርቅ። በጣሊያን አገር የምትገኘው የትመወርቅ በኩላሊት ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች። ኩላሊት ለማስቀየር ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልጋል። ንጉሴም ሆነ የትመወርቅ ይህን ለመሸፈን አቅም የላቸውም። ..እህታችንን በሚከተለው አካውንት ማግኘት ይቻላል፤  #YetmworkJagemaKello ፎቶ:- አፍላው ዘመን ንጉሴና የትመወርቅ

Filed in: Amharic