>
4:38 am - Tuesday September 28, 2021

ከመሰቃያቸው ስፍራ የላኩት የጋዜጠኞቹ ኣናኒያ ሶሪ፣ኤሊያስ ገብሩና የፖለቲከኛው ዳንኤል ሺበሺ መልዕክት

ሠላም ያገር ሠዉ!! በዛሬዉ ዕለት ህዳር20-2009 ዓ.ም እነ ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ከታሰሩበት እስር ቤት በሶፍት ወረቀት ተጠቅልሎ የተላከ መልዕክት ነዉ፣ እባካችሁ ለማህበራዊ ድረ-ገጽ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊያንና ለሚመለከታቸዉ ሚዲያዎች በማድረግ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ!!

Anania Sorriየጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ መልዕክት ከእስር ቤት

‹‹ኢህአዴግ ታላቅ ስህተት ላይ ነዉ፡፡ጠላት በማብዛት ድል ያደረገ አንዳች የፖለቲካ ኃይል የለማና!! አሁንም ወጣቶችን በጅምላ በማሰር የሚገኝ መፍትሄ የለም!! የኤዲፐስ መንገድ የፈሩት ሥልጣን ያሳጣል፡፡ወንጀላችን ወጣት ሁነን መገኘታችን ብቻ ነዉ!!አበቃሁ!! ኦሮማይ-ኢህአዴግ!!››

Elias Gebru 15102006የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ መልዕክት ከእስር ቤት

‹‹ሰዉ ፈርቶ የተሻለ ህይወት ሲኖር አላየሁም፤የፍርሃት መንገድ ሁሉ መዳረሻዉ ባርነት ነዉ!!ፈርቶ ከመኖር በድፍረትና በኩራት መሞት የተሸለ ነዉ!!ኢትዮጵያ ለፈሪዎች ቦታ የላትም!!››

Daneil Shibehsi - AAየፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ መልዕክት ከእስር ቤት

‹‹ከዕድገት በህብረት ወደ ‹እስር በህብረት› መራመዳችን እንደ ሀገር እጅጉን አሳዛኝ ክስተት ሆኖ በታሪክ ይመዘገባል!!የማይቀረዉን ለማዘግየት መዉተርተር ትርፉ መላላጥ ነዉ፤የማይቀረዉ አብዮት እንደሆነ ይዘገይ ይሆናል እንጅ አይቀርም!!››

Filed in: Amharic