>
4:34 pm - Tuesday October 16, 0981

ህወሓት የአንድ ፀሐፊን ብዕር ከባታልዮ ጦር በላይ ይፈራል ፍርሃቱ ልክ የለውም (ሃብታሙ አያሌው)

ተመስገን ብርቱ ጋዜጠኛ ነበር ያገኘውን እውነት በድፍረት ለህዝብ ጆሮ የሚያደርስ ከሚያምንበት ነገር ወደ ኃላ የማይል ነው! በመጀመሪያ እስሩ የመለስን መሞት ብሉምበርግ የኢትዬጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤትን መሠረት በማድረግ ይፋ ያረጋል፤ ሽግግር ም/ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ መረጃውን ከህልፈቱ ጥቂት ሰዓታት በኃላ አስታማሚው የነበሩ ወደ ኢትዬጵያ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተሰጥቶ በጉዞ ዝግጅት ላይ ብረሰልስ አውሮፕላን በበረራ ዝግጅት ላይ ከነበሩ የዓይን እማኞችና አስታማሚዎች የህልፈቱን መረጃ አግኝቶ ለዓለም ይፋ ሲያደርግ ይህንን የሽግግር ም/ቤቱን በምንጭነት በመግለጽ bloomerg News በሰፊው ይፋ አደረገ ፤ ተመስገንም ይህንን ዜና ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣው ላይ ሽፋን ሰጥቶ ዘግቦ ስለነበረ ሕዋቶች በስብሃትና በረከት አማካይነት አቶ መለስ በጤንነት እንዳለና በወቅቱ ከነበረው የኢትዬጵያ ዓመት በዓል በፊት አገር ቤት እንደሚመለስ ነበር ለህዝብ የዋሹት ነገር ግን ኃሰት ወሬ ዘግበኃል በማለት ወደ እስር እንዲገባ ተደረገ ፤ በኃላም በተለየ እንደገና በዚህ ሁኔታ ለእስር በቃ ፤

ተሜ ደጋግሞ “ህወሓት የአንድ ፀሐፊን ብዕር ከባታልዮ ጦር በላይ ይፈራል ፍርሃቱ ልክ የለውም ” ይለኝ ነበር። የዛ ፍርሐት ልክ ይህው ለሶስት አመታት በእስር እንዲማቅቅ ምክንያት ሆነው። በመሰረቱ ከልቤ እንደማምንበት እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አባባል “ህገ አራዊታቸው” እንኳን በተፃፈው መንገድ ቢሰራ ተሜ ሐምሌ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ/ም ከእስር መፈታት ነበረበት። ምክንያቱም የመለስን ሞት ተከትሎ ለአንድ ሳምንት ታስሮ ነበር ። የተፈረደበት በዚያው ክስ ስለሆነ ያ ሊደመር ይገባ ነበር። ነገር ግን አልሆነም ተሜ አመክሮ ተከልክሎም እንደገና ቦነስ እየታሰረ ነው። እነ  እንቶኒ የሚናኙባት ኢትዮጵያ ለተሜ የምትፋጅ እሳት ሆነች። ህወሓትን ለመክሰስ ሺህ ምክንያት አለኝ የምለው ለዚህ ነው። የሚሟገቱለት ጠየቆቹም ምክንያት እንዳላቸውም በደምብ ይገባኛል። እንኳን ለግዕዝ በቀረበው ትግሬኛ በኮሪያኛ ሲናገሩም እረዳቸዋለዎ።

Filed in: Amharic