>
4:34 pm - Saturday October 16, 6088

እነ በቀለ ገርባ በችሎት ፊት የአንድ ሀገር ልጆች ነን ''አንድ ነን'' ሲሉ ተናገሩ (በዳንኤል ሺበሺ)

  • እነ በቀለ ገርባ በችሎት ፊት የአንድ ሀገር ልጆች ነን 
    (አንድ ነን) ሲሉ ተናገሩ
  • ችሎቱን በኦሮሚኛ ዘፈን ሲያደባልቁት ዳኞች ችሎቱን 
    ትተው ወጡ

በእነ አቶ #ጉርሜሣ አያኖ መዝገብ አቶ #በቀለ ገርባ’ን ጨምሮ የበርካቶችን የዛሬውን የችሎት ውሎ ተከታትያለሁ፡፡ ከጧት እስከ 10፡30 ፡፡ መዝገቡ ለዛሬ ያደረው መከላከያ ምስክሮችን ቃል ለማዳመጥ ነበር ፡፡ ምስክሮች ግን ዛሬም አልቀረቡም፡፡ የተሰጠው ምክንያት መጥሪያ አልወጣም የሚል ምክንያት በቀኝ ዳኛ ተነገራቸው፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ገና እያጣራን ነው ተብሎላቸዋል ፡፡ በርካታ ችሎቶችን ተከታትያለሁ ፡፡ ነገር ግን በችሎት አልቅሼ አላውቅም ፡፡ ይኼው ዛሬ እነ በቀለ’ን በደረሰባቸው ነገር አለቀሱኩኝ ፡፡ ስሜቴ ተጎዳ፤ ውስጤ ተረበቨ፡፡እንባዬ አመለጠኝ ፡፡
በቅድሚያ የመናገር ዕድል ያገኙ ሶስቱ ተናጋሪዎች <ይህ ፍ/ቤት እንዲረዳልን የምንፈልገው> በማለት ነበር ሀሳባቸውን የጀመሩት ፡፡

“እኛ አንድ ዘር ነን፡፡ እኛ የአንድ ሀገር ዜጎች ነን፡፡ ርግጠኛኞች ነን እኛን ዛሬ በእናንተ ፊት ያቆመን የግል ጥቅምና ብልጽግና ፍለጋ አይደለም፤ ጥቂት በጎ ነገር ቢሆንም ለምንወዳትና ለምናከብራት ሀገራችን እናበረክት ባልነው ነው፤ ሁላችንም የቤተሰብ ኃላፊዎች ነን፤ ሁላችንም ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪና ከዚያም በላይ የተማረን ነን፤ ኃላፊነት ይሰማናል፤ በአሁኑ ወቅት በእኛ ላይ እየተፈፀመ ያለው ነገር አይደለም በሕጉ ይቅርና ከተለመደው ተራ አሰራርም ውጭ ነው ወዘተ ” ማለት የተናገሩ ሲሆን ዳኞችም ዝም ብለው ያዳሚጧቸው ነበር ፡፡ እኔም በጣም ጥቂቱን ነው ቀንጭቤ ያቀረብኩት፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ልክ በፍ/ቤቱና በሃገራችን ፍትህ ሥርዓት ላይ እንዲማረሩ ያደረገው እነርሱ ያስመዘገቧቸው መከላከያ ምስክሮች (ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናትና በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ የሚገኙ ፍርደኞች) አቀራረብ ጋር በተያያዘ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱ እንዲቀርቡ ባለማድረጉ ነበር፡፡ ምስክሮቹ ያልቀረቡበት ምክንያት ተብሎ ከፍ/ቤቱ በኩል የተጠቀሰው “መጥሪያ ባለመውጣቱ ነው” የሚል ነው፡፡ ለምን? የሚል ጥያቄ የእኛም የዳኞችም ነው፡፡ መጥሪያው ለምን ወጪ እንዳልሆነ ወደ ፊት እናጣራለን የሚል ምላሽም ከዳኞች ተሰጥተዋል፡፡ ቀጠሉና ተከሳሾች ያስመዘገቧቸው መከ/ምስክሮች #አቀራረብን በተመለከተ ወደ ፊት ይወሰናል መባሉ እነ በቀለ ገርባ ክፉኛ ያስቆጣቸ፤ በፍ/ቤቱ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡ በአንድ ጉዳይ ተስፋ የቆረጠ ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል ማሰብ አያቅተንም ፡፡
ስለዚህ አሉ በተከሳሽ በኩል የተመዘገበው”ምስክር ማንም ይሁን ማን? በመጥሪያ ማቅረብ ነው እንጂ ይህ ችሎት ወደ ፊት መወሰኑ በፍጹም ሕገወጥ ነው፤ ስለዚህ ከዚህ በኀላ ይህንን ፍ/ቤት አምነን ፍትህ አንጠብቅም ፡፡ ከዚህ ችሎት ፍትሐዊ ዳኝነት አንጠብቅም” በማለት አንጀት የሚበላ ንግግር ተራ በተራ ካደረጉ በኀላ ነበር፥ ሁሉም ከቆሙበት ቁጭ አሉና በኦሮሚኛ ለስለስ ባለ ዜማ ግን ከፍ ባለ ድምፅ መዝፈን ጀመሩት ፡፡ ችሎት አስከባሪዎችም፣ አጃቢ ፖሊሶችም ሆነ ዳኞች እንዲያቆሙት ቢያስጠነቀቁትም “ስለማትሰሙን አንሰማችሁም” በማለት ቀጠሉበት፡፡ በመጨረሻም ዳኞች በቃ ቀጠሮ ለኀዳር 6፤ አሉና በድንገት ብድግ፡ብድግ አሉና ችሎቱን ለቀው ወጡ፡፡ ታዳሚ የነበረን በሀዘን፣ በድንጋጠም ተዋጥን፡፡ ሰዎች ነገሩ ከሯል፡፡

Filed in: Amharic