>
10:36 pm - Friday October 22, 2021

ፎቶና ታሪኩ (1) [መስፍን ማሞ ተሰማ]

በወያኔ ዘመን በህወሃት ቀንበር ያሳለፍነው ህይወት የጠጣነው አረር እንዴት እንደሆነ እንዴት እንደነበር ጠበቃ ከማቆም እማኝ ከመደርደር ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር።

*የተከበርክ አንባቢ ሆይ! ቀጣዮቹን ፎቶዎች በፅሞና እና በማስተዋል ተመልከታቸው፤ መልዕክቶቹንም ረጋ ብለህ ወደ ነፍስህም ቀርበህ አንብብ። ምናልባት ለመፍትሄውም ሆነ ለችግሩ አንተ ትቀርብ ይሆናልና።

በጎንደር ከተማ የሚታየው ዘግናኝ የቁልቁለት ‘እድገት’። በህወሃት በይፋ ጠላትነት ተፈርጆ የቁም ስቅሉን እያየ በሚገኘው የአማራ ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ በመካሄድ ላይ ያለው የኢኮኖሚ ተዐቅቦ ያስከተለው መከራና ድህነት እጅግ ዘግናኝ ሲሆን በቅርቡ በወጣ ጥናታዊ ዘገባም የአማራ ህፃናት ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ (በርግጠኝነትም በሌሎች ክልሎች በዚህ ስፋትና መልክ ያልተከሰተ) ያለ ዕድሜያቸው እየቀነጨሩ በመሆኑ ክልሉ ሰፊ የሆነውን የነገውን የሥራና የአስተዳደር ተረካቢ የሆነውን ወጣት ሀይል የማጣት እድሉ ከፍተኛ እንደሆን ተጠቁሟል። ጎንደርና ባህር ዳር ሲጨልም መቀሌና አክሱም በብርሃን ሙሉውን ለማንበብ

Filed in: Amharic