>
10:38 am - Tuesday May 17, 2022

ትህነግ በ6 ተቧድናለች! ልዩነታቸው እንዴት እየጨቆንን እንቆይ ከሚለው አያልፍም እንጅ! (ኣስገደ ገብረስላሴ)

” በመቀለ ከተማ ካሁን በፊት ያልነበረ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የደህንነት ፣ ኢንሳ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስብሰባው ኣካባቢ እያንጃበቡ ከባድ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ ።ተራ የስለላ ወይ ደህንት ሃይሎች ፣ፈደራል ፓለስ የትግራይ ልዩ ሀይል በሙሉ መቀለ ከተማ ነው ያለው ። የመከላከያ ሀይልም ከወትሮው የተለዬ ኣለ ።”

በኣጠቀላይ በስብሰባው ተጠምዶና ተጨንቆ ያለው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በብዙ ቡድኖች ተከካፋፍለው ከርመው በኣሁኑ ጊዜ በጥቅማቸው ተሳስረው ወደ ሶስት ጠንካራ ቡድናኖች እና ሶስት ደካማ ቡዱኖች ወርደዋል።

1) በኣባይ ወልዱ ኣዲስ ኣለም ባሌማ በየነ መኩሩ ፣ኣለም ገብረዋህድ ፣ኣባይ ጸሀዬ ፣አለም ገብረወህድ ሓገስ ጤና ጥበቃ ፣ኪሮስ ቢተው ፣ እና ሌሎች እንደሮቦት በሪሞት የሚነዱ ሆነው ትልቅ ቡዱን ነበሩ ። ኣሁን ግን ኣባይወልዱ፣ ኣባይ ጸሀዬ፣ ኣዜብ መስፍን ፣ሀጎስ እና ጥቂት ሰዎች የመለስ ርዓይ ነክሰው ሲቀሩ

2) ይህ ቡዱን የኣርከበ እቁባይ በመጠኑ ለነደብረጽዮን እና ጌታቸው ኣሰፋ የሚደግፍ ሰልጣናችን ለሀቀኛ እና ቡቁ የሙሁራን ትውልድ እናስረክብ ፣ እስከኣሁን በስመሙሁር በማእከላይ ኮሚቴና ሌላ የስልጣን ቦታ ሰጥተናቸው
የነበርን ሌቦችና ለሆዳቸው ኣዳሪዎች በይ ነው ይህ ቡድን በብዛቱ ጥቂት ነው ።

3 ) ሰብሀት ነጋ የያዘው ቡዱን ህወሓትን እናድን ነባር ተጋዮችና ኣማራር፣ ኣባልት እንሰብስብ ይላል። እንደኣርከበ በዱንም ወደነደብረጽየን እና ጌታቸው አሰፋ ያዘነብላል ።

4 ) እነ ብርሀነ ገብረክርስቶስ ያሉባቸው ጥቂት ሰዎች ደግሞ የህዝብ መእበል ወላፈን እንዳያኣቃጥላቸው ማኸል ሰፋሪ ሆነዋል ።

5) ኣዲስ ተምረዋል የሚባሉ ወጣት ማእከላይ ከሚቴ ደግሞ በማኸል ሆነው በበላት እና ባካበታት ትንሽ ገንዝ ሳይበሏት በስጋት እያዋጀቁ ኣጎላጉል የቆሙ ናቸው ።

ኣለም ገብረዋህድ ኪሮስ ቢተው ፣ ኣዲስ ባሌማ በየነ መኩሩ የያዙ በርከት ያሉ የሂስ ድላ ካረፈባቸው በኃላ ለሌላው ቡድን ፈርተው ወደ እነ ደብረጽዮን እና ጌታቸው ኣሰፋ እንደወገኑ ከህወሓት ስብሰባ መረጃው ኣፈትልኳል ።

6) ከላይ እንደጠቀስኩት ደብረጽዮንነ ጌታቸው ኣሰፋ እነኪሮስ ቢተው ኣስከትሎ ለኣባይ ወልዱና ጓደቹ በከባድ ሂስ ከሰራ ውጭ እያደረገ ያለ ትልቅ ቡዱን ነው ።
ጀነራል ሳሞራ የኑስም በውጭ ሆኖ ለኣባይ ወልዱ እና ኣዜብ ፣ኣባይ ጸሀዬ እንደሚደግፍ የወጡ መረጃዎችን ይጠቁማሉ

በመቀለ ከተማ ካሁን በፊት ያልነበረ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የደህንነት ፣ ኢንሳ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስብሰባው ኣካባቢ እያንጃበቡ ከባድ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ ።ተራ የስለላ ወይ ድህንት ሃይሎች ፣ፈደራል ፓለስ የትግራይ ልዩ ሀይል በሙሉ መቀለ ከተማ ነው ያለው ።
የመከላከያ ሀይልም ከወትሮው የተለዬ ኣለ ።

Filed in: Amharic