>

" አልጋው ቦዶ ሆነ! አልጋው ባዶ ሆነ! " (ቬሮኒካ መላኩ)

” አልጋው ቦዶ ሆነ! አልጋው ባዶ ሆነ! ” ይሄን ያለችው ከ 5 አመት በፊት አዜብ መስፍን ቦሌ ላይ የመለስ ዜናዊ አስከሬን አጠገብ ሳሞራ የኑስ አንገት ላይ በመጠምጠም ነበር ።
መለስ ዜናዊ በትክክል የሞተው ትናንት ነው። አልጋውም ባዶ የሆነው ከ 5 አመታት በፊት ሳይሆን ትናንት ነው። ህውሃት መለስን ሲጥ አድርጋ የመጨረሻውን ሚስማር ሬሳ ሳጥኑ ላይ ቀብቅባ አሰናብታለች ። ህውሃት መለስን እንደገና ትናንት እውነተኛውን ሞት እንድጋት አድርገዋለች።

ስላሴ ካቴድራል የተቀበረው የመለስ አጥንት ፈራርሶ ሳይጠናቀቅ ህውሃት ” የመለስ ራእይን ” አፈራረሰችው ።
መለስ ራእዬን ያሳኩልኛል በማለት ተክሏቸው ያለፈውን አዜብን ፣አባይ ወልዱንና በየነ መክሩ ህውሃት እንደ አሮጌ ዘንቢል አሽቀንጥራ ጥላለች ።
አሁን ” የመለስ ራእይ ” እያለ አምቡላ እንደ ሰረገበ አሮጌ ውሻ የሚያላዝነው ሆዳሙና ልሃጫሙ የአለምነው መኮንን ብአዴን ብቻ ነው።
ከአሁን በኋላ ህውሃት የቱንም ያክል ሹም ሽር ብታደርግ ድሮ የነበራትን የበላይነት ማስመለስ አትችልም። እሱ ተረት ሆኗል። አሁን የበላይነቱን ኦህዴድ ተረክቧል። ከዚህ በኋላ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ሁኔታ የማሽከርከር አቅም ያለው ኦህዴድ እንጅ ህውሃት አይደለም።
ለማ መገርሳ ህውሃት ኦሮሚያ ውስጥ ዘርግታው የነበረውን የማዢኖን ካብ ( Majino Line ) እንደ ካርድቦርድ ካብ እፈራርሶ ኦሮሚያን ከትግሬ የስለላ አይን አፅድቷል።

በህውሃት የአሁኑ የስልጣን ሽኩቻ አሸንፎ የወጣው ቡድን በፓርቲው ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አማራ ጠል የሆነው የስብሃት ነጋ ቡድን ነው። ይሄ ቡድን በአማራ ክልል ውስጥ ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ መዋቅር አለው። የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ ገነት ገ/እግዚአብሄር ትግሬ ነች። ባህር ዳር ከተማን ወክሎ የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆነው ግኡሽ የሚባል ትግሬ ነው። ጎንደር ውስጥ ከላይ እስከታች ባለው የስልጣን መዋቅር ተሰግስገው የሚያሽከረክሩት የእነስብሃት ኔትወርክ ትግሬዎች ናቸው።
አሁን አማራ ክልል ውስጥ ያሉት ብአዴን የሚባሉት እንክርዳዶች ህዝብ እንደት እንደሚመራ ፣ የተዘረጋ የጠላት ኔትወርክ እንደት መበጣጠስ እንደሚቻል ለመማር ወደ አሜሪካ ወይም አውሮፓ መሄድ ሳያስፈልጋቸው ወደ ኦሮሚያ ቢሄዱ ትልቅ እውቀት መቅሰም በቻሉ ነበር።
Filed in: Amharic