>
4:29 pm - Wednesday July 6, 2022

“የትግራይ ሕዝብ የሥርዓቱ ተጠቂ እንጂ ተጠቃሚ አይደለም!” (አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር)

*አባይ ወልዱን ከስልጣን ለማስወገድ፤ ከስብሀት ነጋ ጋር በመሆን ትልቁን ሚና የተጫወቱት፤ የአሁኗ ህወሀት  እጩ ሊቀመንበር፤ የፈትለወርቅ  ገብረእግዚአብሔር(ሞንጆሪኖ) ወንድም፤ የስብሀት ነጋ የወንድም ልጅ፤ በኢትዮጲያ 3ኛው ሀብታም የሚባሉት፤ አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ናቸው።

ከብዙ በጥቂቱ፤ . . . የራያ ቢራ ትልቁ ድርሻ የሳቸው ነው። ለአፍሪካ መንግሥታት ትላልቅ የሲቪል ሄሊኮፕተሮችን ይሸጣሉ። የህክምና መሳሪያዎችን ያቀርባሉ።“ዳዊት ጎልድ ማይንኒግ” እና “ሜዲካል ፋርማ” የተባሉ ኩባንያዎች አሏቸው፡፡የመጀመሪያውን የግል አየር መንገድ ባለቤትም ናቸው። ብድር ወስጄ አላውቅም ይላሉ። የሀብታቸው ምንጭ ‘አይታወቅም’።

እኚህ ሀብታም ሰው ታዲያ፤ . . . እንደ ‘ተቃዋሚው’ አረና ፓርቲ፤
* ‘የትግራይ ህዝብ የሚገባውን ጥቅም አላገኘም’ ብለው፤ የ’ቀድሞው’ ህወሀት ላይ የሰላ ትችት የሚያቀርቡ ናቸው።
* “የትግራይ ሕዝብ የሥርዓቱ ተጠቂ እንጂ ተጠቃሚ አይደለም!” ይላሉ።
* “ኤፈረት በባለቤትነት ከሚመራቸው ውጭ ትግራይ ውስጥ ምንም የተሠራ ነገር የለም” ብለው ይከሳሉ።
* አድዋ ሆስፒታል ምን ያህል እንደወረደ ደጋግመው በማሳያነት ያነሳሉ።
* “የትግራይ ህዝብ አሁንም ከሌሎቹ ክልሎች በከፋ ሁኔታ እየተበደለ ነው” ብለው ይላሉ።
* በጠመንጃ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ ህወሀትን እንዲታገሉ ይገፋፋሉ።

* ብቻ በአጠቃላይ፤ . . . የትግራይ ህዝብ የሚገባውን ጥቅም አላገኘም ብለው ያምናሉ።

ባለፈው፤ . . . 6ቱ የአረና ልጆች፤ በሚገርም ድፍረት ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት፤ ህወሀቶች ለብተና፤ ካስለመዱን ጥይት ይልቅ ድምጽ ማጉያን መጠቀማቸው ብዙዎቻችንን አስገርሞን ነበር። ብዙዎች ይህ የሆነው፤ ‘አረናም ከትግራይ ስለሆነ ነው’ አሉ። እኔ ግን በወቅቱ፤ ያ ብዙም አላሳመነኝም። ምክንያቱም፤ ህወሀት ለማንም የማይመለስ አውሬ እንደሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ።

ዛሬ ላይ ግን ነገሮች በደንብ የጠሩ ይመስላል። ዛሬ ያሳመነኝ፤ . . . በወቅቱ፤ ስልጣን ላይ የነበረው የአባይ ወልዱ ቡድን፤ ከማስፈራራት አልፎ ርምጃ ያልወሰደው፤ አረና፤ የነስብሀት ነጋ ቡድን ድጋፍ ስላለው፤ ፈርቶ ይመስለኛል።

በነገራችን ላይ፤ . . . ይሄ የልጆቹን ጥረት ለማኮሸሽ ሳይሆን፤ የታየኝን ሁኔታ ለመግለጽ ብቻ ነው። ድጋፉ እንዳለ እንኳን፣ (ድጋፉ ስልጣን ካልነበረው ቡድን ነውና)፤ መቐለ ላይ ህወሀትን ተቃውሞ ሰልፍ መውጣት ትልቅ ድፍረት የሚጠይቅ ጀግንነት ነው።

የኢትዮጲያችን ሁኔታ ግን፤ . . . መሽቶ በነጋ ቁጥር ይበልጥ እየተወሳሰበ ሄዷል። . . . ነገ ደግሞ ምን ይዞልን/ይዞብን ይመጣ ይሆን?

 

Filed in: Amharic