>
11:18 pm - Wednesday February 1, 2023

ከሻዕብያ ጥይት ተርፎ በሕወሓት ጥይት የተረሸነው መምህር ታምሩ በሪሁን (በአቻምየለህ ታምሩ)

በትግራይ ፖሊሶች ትናንትና በወልድያ ከተማ የተረሸነው መምህር ታምሩ በሪሁን ይባላል። የተወለደው ደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ ዘጠኝ ውስጥ ነው። ታምሩ ወያኔና ሻዕብያ ባድመን ሰበብ አድርገው ከኢትዮጵያ በዘረፉት ሃብት ክፍፍል ዙሪያ በተጣሉበትና የድሃ ልጅ ባስጨረሱበት ውጊያ የተካፈለና የቆሰለ ወጣትም ነበር።

ታምሩ የባድመ ውጊያው ካለቀ በኋላ «በቅነሳ» ሰበብ ከወያኔ ሰራዊት ቢባረርም ያቋረጠውን ትምህት እንደገና ቀጥሎ አስተማሪ በመሆን እስከለተ ሞቱ ድረስ ወሎ ውስጥ ሲያስተምር ቆይቷል። ታምሩ የአገር ዳር ድንበር ትደፈረ ተብሎ በተካፈለበት የባድመ ውጊያ በሻዕብያ ጥይት ሁለት ቦታ ቆስሎ ሕይወቱን ቢያተርፍም፤ ትናንትና ግን አገር ሰላም ብሎ ከቤቱ በወጣበት ከፋሽስት ወያኔ በተተኮሰ ጥይት ተደብድቦ በግፍ ተገድሎ ሳይመለስ ቀረ። ያበሳጫል!

በትግራይ ፖሊሶች በግፍ የወደቀውን ታምሩ በሪሁንን እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ከሰማዕታት ተርታ የቆመው ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን!

Filed in: Amharic