>
8:34 pm - Wednesday February 8, 2023

«ጀግና እዚህ አዳራሽ የለም! ጀግኖች ያሉት ቃሊቲና ቂሊንጦ ውስጥ ነው » ሃጫሉ ሁንዴሳ! (በዮናስ ሀጎስ)

በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ሊሰራው የነበረውን ዝግጅት «በፀጥታ ምክንያት» ከተሰረዘበት በኋላ ኦህዴዶች ወደ ሚልንየም አዳራሽ አምጥተውት ሲያዘፍኑት ሌላው ቢቀር ምስጋና ቢጤ ጠብቀው ነበረ መሰለኝ።
•°•
ጋሼ ሃጫሉ ግን «ጀግና እዚህ አዳራሽ የለም! ጀግኖች ያሉት ቃሊቲና ቂሊንጦ ውስጥ ነው። ጀግኖች ባዶ እጃቸውን ወጥተው መሳርያ ከያዘው ኃይል ፊት በቆራጥነት እጃቸውን አጣምረዉ የሚቆሙት ናቸው!» ብሎ እስከ ዶቃ ማሰርያቸው ነግሯቸው ተሸበለለ አሉ።
•°•
የኢትዮጵያን ቀጣይ ጀግና የሚያፈራው የኦሮሞ ማሕፀን ስለመሆኑ አሁን እርግጠኝነት እየተሰማኝ ነው። ብራቮ ሃጫሉ!!
•°•
ኦህዴድ በውነቱ ከሕወሐት የተሻለ መሆኑን በዚህ የሚልንየም አዳራሽ ዝግጅት አስመስክሯል። ይሄኔ ዘፋኙ አንድ የትግራይ ተወላጅ ቦታው መቀለ አዳራሹ የሰማዕታት መታሰቢያ አዳራሽ ባለስልጣናቱም የሕወሐት ቢሆኑ ኖሮ ዘፈኑንም ገና ሳይጨርስ ቦታው ቀውጢ በሆነች ነበረ። ኦህዴድ በእውነትም ትራንስፎርም እያደረገ መሆኑን አምኜ መቀበል ግድ ሆኖብኛል።
•°•
ሕወሐትን ተዋት ዝም ብላ ባለችበት ትርገጥ…
•°•
ኦህዴዶች፤ ለውጣችሁ የሚበረታታ ቢሆንም ቅሉ ገና ከኢህአዴግ ቀለም ቅብ ተሃድሶ እንዳልወጣችሁ የሚያሳብቁ ድርጊቶችንም ብታሻሽሉ መልካም ነው። ሰሞኑን ሹም ሽር ብላችሁ አንዱ ሰፈር በዝርፊያ የሚታወቀረ ካድሬን ወደ ሌላ ሰፈር አዛውሮ መሾም ገና ከኢህአዴግ አሰራር በደንብ አለመላቀቃችሁን የሚያሳይ ክስተት ነው። የዩኒቨርሲቲዎቹን ያው ፈጣሪ ያውቃል… እሱ ያስተካክለው እንጂ በናንተ ዓቅም የሚቻል አልሆነም መሰለኝ…ወደ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስንመለስ በሚሊኒየም አዳሽልምራሽ እስከጥግ ዘፍኗል። በተለይ የዘፈኑ ይዘት በብዙ መመዘኛ እንዴት ህወሓት በዝምታ አየችው ከዚህ የምታተርፈው ምን ይሆን?  የሚለው የሚያመራምር ነው።
የሙዚቃው ንጉስ ቴዲ አፍሮን አይንህን አልይ ኢትዮጵያም ያንተ አይደለችም ያለቺው ህወሓት እንደምን ይሄን ፈቀደች? ብአዴን ሰፈርም በግልፅ በአማራ ቴሌቭዥን ቴዲ አፍሮን ለመስማት ማንን እንደምንጠብቅ ልገባንም?
ጋዜጠኞች ማንን እየጠበቁ ነው? የግድ ቀድመን ከሌላ ቴሌቪዥን መስማት ግዴታ ነውን? የሚሉ መረር ያሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። እናም እዚያ ሰፈር ገት ያለው አመራር ከተገኘ የምናየው የምንሰማው ይኖራል። የሁሉም ነገር እንጭፍጫፊዎች ህወሓት ብትወገድ ለኢትዮጵያ በጎ እድል መኖሩን አመላካች ይመስላል።
ሃጫሉ በኦሮሚኛ ዘፈኑ መድረክ ላይ ያቀረበው ወደ አማርኛ ሲተረጎም:-

“ሸልል ሸልል ይሉኛል ምኑን ልሸልል እኔ
ቂልንጦ አይደለም ወይ…
ቃሊቲ አይደለም ወይ….
ከርቸሌ አይደለም ወይ…
ሸልሎ የማይጠግበዉ የሚገኝ ወገኔ፡፡
የፈረሶቻችንን ዝና፣
የጀግኖቻችንን ዝና
አድዋ መቀሌ ይንገረና!
አብሮ መኖር ይሻል ብለን…
መከባበር ይሻል ብለን…
እስከዛሬ ታግሰናል…
ከእንግዲህ ግን ይበቃናል”
==========////========
” ሽልም ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል”

Filed in: Amharic