>

ዘርህ ? ካላችሁኝ...” አፈር ነኝ”.... የተሰራሁት ከ”አፈር” ነው!!

ይሄን መልእክት ኦሮሞ: ትግሬ :አማራ :ወላይታ: ኩነማ: ጉራጌ :አፋር ምናምን ንቅናቄ: ምናምን ግንባር: ምናምን ክልል :ምናምን ብሄር: ምናምን ሀይማኖት: የሆነ እንዳያነበው።

ሰው ብቻ ከሆናችሁ አንብቡት ላይክም ኮመንትም ለመስጠት ሰው ብቻ ከሆናችሁ አድርጉት ውስጣችሁ ሌላ ሆኖ ለመዋሸት ምንም አታድርጉ ህሊናን ማጽዳት ከዚህ ይጀምራል።

ማን ነህ? እንዳትሉኝ ብላችሁም እንዳትጠይቁኝ እኔ “እኔው ነኝ” ዘሬም !ሀረጌም! ሲመዘዝ ውሎ ሲመዘዝ ቢያድር በየትኛውም መመዘኛ ብትመዝኑኝ እኔ ማለት “ሰው ነኝ”!! ንጹህ “ሰው” ብቻ። ከምንምጋር ያልተቀላቀለ።

ዘርህ ? ካላችሁኝ…” አፈር ነኝ”…. የተሰራሁት ከ”አፈር” ነው!!። ያኔ ስሰራ እና ወደዚህ ምድር ስመጣ መገኛዬ “አፈር” እንደሆነ ተነገሮኝ ስሄድም ወደዛው እንደምሄድ ተነግሮኝ ነው የመጣሁት። ስለዚህ…….. “ዘሬም ዘር ማንዘሬም አፈር ነው”።!! “ አዳም አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ” የተባለልኝ የዛሬው “ሰው” ! የነገው “አፈር” !ማለት እኔ ነኝ።!!

የመሄጃ ቀናችን እንደ አመጣጣችን ይለያይ እንጂ መገኛችንም መሄጃችንም መጨረሻችንም “”አ…..ፈ…ር…..“” ነው።!! እና ታዲያ ማነህ? የምትሉኝ ምን እንድላችሁ ነው? ከዚህ የተለየ መገኛ ያለው ሰው ካለ እሱ ይንገረኝ። ከአፈር ውጪ ነው የተሰራሁት ዘሬ ይሄ ነው የሚል እስቲ አንድ ሰው? በድፍረት ይንገረኝ።

እናም ባለማወቅ ድንቁርና ለራሳችሁ አጥር እየሰራችሁ በራሳችሁ ድንቁርና ልክ ሰውን የምትመዝኑ ልክ እንደ እናንተ ሰው ደንቁሮ በድንግዝግዝ በጭፍን እንዲሄድ የምትፈልጉ አፈርን ከአፈር ለይታችሁ ትልቁ እና ትንሹ አፈር ብላችሁ ጎራ ለይታችሁ ለምትባሉ በአፈሮች መካከል ብዙ የተከፋፈሉ አፈሮችን ለምታበዙ ከአፈር መካከል ድንጋይ ይሆነ ማንነት ይዛችሁ ለወጣችሁ ሁሉ ይህ የኔ መልእክት ነው።

እመኑኝ…. “አፈር ናችሁ”!!.. ‘’ወደ አፈር’’ ትመለሳላችሁ።!! ስለዚህ በዘር.. በሀይማኖት… በጎሳ… በብሄር… በቀለም… በማንነት… እየከፋፈላችሁ አትሸውዱን። በእናተ ቁማር ውስጥ እኛን እያስገባችሁ እኛን እየጣላችሁ እናንተ እየቆማችሁ…. እኛ እያለቀስን እናንተ እየሳቃችሁ…… እናንተ እየዘፈናችሁ እኛን እያስለቀሳችሁ….. መቼም አብረን አንኖርም እናም አትሸውዱን ሁላችንም እኩል አፈር ነን። ልዩነታችን የተማረ አፈር እና ያልተማረ አፈር ብቻ ስለሆንን ነው።

TST APP.  ተስፍሽ

 

Filed in: Amharic