>

ውጥረት በመከላከያ (ገረሱ ቱፋ)

በመከላከያ ኃይል ዉስጥ ዉጥረት ነግሷል
በፖለቲካው ውስጥ የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ በመከላከያዉም ዉስጥ ያለዉ ድባብ ጤናኛ እንዳልሆነ ከታማኝ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎች እያረጋገጡ ነዉ።  የፖለቲካው ውጥረት ወደ ግጭት የሚያመራ ከሆነ ህዝባችንን የመካላከል ግዴታ አለብን የሚል ምክክር እና ዝግጅት በሠራዊቱ አባላት መካከል   በስፋት እየተካሄደ እንደሆነ የታመኑ ምንጭች ማምሻውን ገልፀውልኛል።
ምክክሩ በአብዘኛው በአማራና እና በኦሮሞ ተወላጆች በተለይም በታችኛው የወታደሩ ክፍል መካከል እነደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እያንዳንዱ ንዑስ ወታደራዊ አሓድ  በብሔር ተዋፅኦ ላይ ተመስርቶ የተዋቀረ በመሆኑ በሁለቱ ትላልቅ ብሔሮች በኩል እየተነሳ ያለው ጥያቄ  በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሌሎችም ተዛምቶ ሠራዊቱን ወደ መበታታንና ግጭት  ሊያስገባ ይችላል ሲሉ ምንጮቼ ስጋታቸዉን ገልፀውልኛል።
ሁልጊዜም የህዝብ አመፅ ሲኖር መከላከያው ውስጥ ውጥረት መፈጠሩ ያለ ቢሆንም የአሁኑ ሁኔታ ግን በፍፁም የልተለመደ  እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። ሁሉም የመከላከያው አባላት በሚያምኑዋቸው ሰዎች በኩል በየቀኑ በፖለቲካው አካባቢ እየተካሄደ ያለውን ውጥረት በንቃት እየተከታተሉ እንደሆነ ምንጮቼ ነግረዉኛል።
Filed in: Amharic