>
10:18 am - Tuesday May 17, 2022

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከዚህ በኃላ በህወሀት መልካም ፍቃድ የሚወሰንበት ግዜ እያከተመ ነው (ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና) 

 በአሁን ሰአት የኢሀዴግ ስራ አስፈፃሚ ውሳኔ ኦሮሚያ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ከባድ ነው:: እነ አቶ ለማ መገርሳ ያልተስማሙበትን:: እነ ገዱ አምዳርጋቸው ያልተስማሙበትን አማራ ክልል ላይ ተግባራዊ ማድረግ ከባድ ነው:: ከምንም በላይ ኢትዮጵያውስጥ እየተነሳ ያለውን እና እየተደረገ ባለው ጉዳይ ህወሀቶች አሁንም አይናቸውን መግለጥ አይፈልጉም:: የትግራይ የበላይነት የለም ብለው አሁንም ከነ ድንቁርናቸው በአደባባይ ያወራሉ:: አይኑን ለገለጠ ሰው ማመዛዘን ለሚችል ሰው የመምሸትንና የመንጋትን ያህል ፍንትው ያለ ነገር ነው:: ለማን ነው የሚደብቁት? እውነቱን ተጋፍጦ ከዚህ እንዴት እንወጣለን የሚለውን ነገር ከመፈለግ ይልቅ ጨፍነው ነው ያሉት:: በዚህ የጭፍን ወይም የድንቁርና ጉዞ ይህን በኦርሚያ ይህን በአማራ ሌላው ቀርቶ በደቡብ ላይ ተግባራዊ እንዳደርጋለን ቢሉ እንኳን ዛሬ ሌላ ነገር ባይነሳም ቆይቶ ሚከተለው ነገር ለማንም ግልፅ ይመስለኛል:: ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታዎች ብንሄድ ህወሀቶች ከዚህ ከእንብላው ከእንዝረፈው ስግብግብ ባህሪያቸው አልወጡም:: እውነቱንም መጋፈጥ አልፈለጉም በሌላ በኩል ነፃነትን የሚፈልጉ በዛ የሚሉ የቆረጡ ሰዎች መኖራቸው እየታየ ነው:: ስለዚህ ህወሀት ክራንቹን ጥሎ ከዚህ በኃላ በሙሉ እግሩ ይቆማል ብዬ አላስብም:: የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከዚህ በኃላ በህወሀት መልካም ፍቃድ የሚወሰንበት ግዜ እያከተመ ነው::

ጋዜጠኛ ሲሳይ በእፍታ ዝግጅት ላይ ከተናገራቸው ውስጥ ቃል በቃል የወሰደ

ከ- ናትናኤል

Filed in: Amharic