>
7:32 pm - Wednesday February 8, 2023

ሌቴናት ኮረኔል ዶክተር አብይና የህወሐት ደህንነት መስሪያ ቤት...

ኮ/ል አበበ ገረሱ

ዶክተር አብይ አህመድ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሌቴናት ኮረኔልነት ማዕረግ ያላው በሰራዊቱ ውስጥ ላቅ ባለ ችሎታቸው ምክንያት በእነሳሞራ ጥርስ ውስጥ ገቡ ” ይሄ ኦሮሞ አላሰራን አለ ” እየተባሉ በ ሀሜት እና በአደባባይ ይወገዙ ጄመር ይህን የተገነዘቡ ኦሮሞ ተወላጂ ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ ውስጡን ይቃጠሉ ጄመር ። በኦሮምያ የበላይ አመራርነት የነበሩ የህዋህት ጫማዎች ሙክታር ከድር እና አስቴር ማሞ ደግሞ የኦሮሞን ጥቅም አሳልፈው ከመስጠት በላይ የህዋህት ቃል ሁሉ የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል በመድረግ የወጡበትን ህዝብ በማስቃዪታቼው። በኦሆዴድ ማዕከላዊ ስብሰባ እንዲወገዱ ተደረገ። ህዋህትእሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ተናደደች ፣ ያለ ጉባኤው ስልጣን እንዴት ተደርጎ ሙክታር የህዋህቱ ታዛዥ ይነሳል ብላ ህዋህት ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል ምርጥ የኦሮሞ ልጆች ጉባኤውን በፍጥነት በመጥራት የነሙክታር አስቴርን መባረር አስጸደቀቁ ። ዶ/ር አብይ ከመከላከያ ወደ ኦሮምያ ክልል በመዛዎር ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኑ።

ወደ ጄመርኩት ጉዳይ ልመለስ። ሌቴናት ኮረኔል ዶ/ር አብይ አህመድ በሳይንስ እና ቴክኒዮሎጂ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ በመስሪያ ቤቱ እና በመላ ሀገሪቱ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ማግኜታቼው ያበሳጫቼው እነሳሞራ በመጎንጎን ከሚኒስትርነታቼወ እንዲነሱ አድርገዋቼዋል።

እጂግ የመጠቀ አዕምሮ ባለቤት ነው የሚባሉት ዶክተር አብይ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ መሆኑ የህዋህትን የአንድ ዘር የበላይነት መሞገታቼው እነሳሞራን አንጀታቸውን እንዳሳረረው ይታወቃል።

የህወሐት ደንነት መስሪያ ቤት ዶክተር አብይን የሚከታተሉበት ዋናዋና ምክንያቶች:

1ኛ ዶክተሩ የወያኔ ወታደራዊ ተቋማትን ጠንቅቆ ስላምያውቅ። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ግዜ የባድሜ ሽራሮ ግንባር የጠለፋ ሃላፊ ነበር። ላላይ ዴደ በምባል ቦታ ባል ቦታ 6 ሰዎች ሆኖ በክርው የወታደራዊ ጠለፋ ስራ ላይ እያሉ ከኤርትራ ሰራዊት የተቶከስው መድፍ 5ቱን ጨርሶ እንደ አጋጣሚ ዶክተር አብይ ብቻውም ተርፎዋል። ቀጥሎም ጦርነቱ እከሚያልቅ ድረስ በዝሁ ስራ ስለ ነበር። ወታደራዊ ምስጥሮችን ከማንም በላይ ጠንቅቆ ያውቃል።

2ኛ የአገርቷንም የቴሌኮምንኬሽን መዋቅሮችን ሥስተሙን በሙሉ አብጠርጥሮ ያውቃል። ሌላው የኢንፎርሜሽን መረብ ደንነት በዝያች አገር ያቋቋመው ራሱ ዶክተር አብይ ነው። ሰለዝህ ዶክተሩ የአገርቷን የደንነት ተቋምና መከላካያን እንድሁም ቴሌኮምንኬሽን መስርያ ቤቱን መወቅሮችና አሰራሮችን ጠንቅቆ ስለምያውቅ።
3ኛ አብይ እንደ ለሎች የወያኔ ባላ ስልጣኖች የትምህርት ማስራጃዎችን ከኢንግልዙ ኦፔን ኡኒቬርስቲ በገንዘብ አልገዛም። እራሱን በራሱ አስተምሮ እዝህ ደረጃ ላይ የደረሰና በቂ እውቀት ያለው ስው በመሁኑ ለወደፍት ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል ተብሎ ከምታሰቡት ሰዎች አንዱ በመሆኑ ከወድሁ ለማስቀረትና ኦ ፒ ድ ኦ ሰው የለውም ተብሎ ደብረ ጽዮንን ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ለማምጣት ታስቦ ነው ዶክተር አብይን ከወድሁ ጥርሳቸው ውስጥ ለማስገባት የፈለጉት!

 

Filed in: Amharic