>
5:13 pm - Monday April 19, 9317

የሞያሌው ግድያ አላማው ህዝብ ላይ ፍርሀት ማንገስ - ምእራባውያኑን በህዝቦች ፍልሰት እና ሽብር ስጋት ውስጥ መክተት ነው!!! (አባይነህ ሀበሻ

ከመከላከያ አባላት በምስጢር የተላከልን መረጃ ነው።
“በሞያሌ የተደረገው ግድያ በከተሞች እና በገጠር ሊወሰዱ የሚገባቸው ህዝብን የማስደንገጥ እርምጃወች ተብለው በዝርዝር ከወጡት ውስጥ አንድ አካል ነው። 
ይህን ግድያ ሊፈፀምባቸው ከወጡ ለጎረቢት ክልሎች እና አገሮች ይቀርባሉ የተባሉ  ከተሞች ውስጥ መተማ፣አሳይታ፣ሞያሌ፣ቡሬ፣ዶሎ፣ሃረር እና አሶሳ ናቸው። በእነዚህ ከተሞች ውስጥ ህገ-መንግስቱን ለማፉረስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ገብተዋል በሚል ሰበብ ጭካኔ የተሞላባቸው ግድያወችን ፈፅሞ የጎረቢት አገሮችን እና ክልሎችን በስደት ማእበል በመናጥ መንግስትን የሚፈታተን ሃይል ሁሉ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል አስፈራርቶ ህዝብን ማሳየት ሲሆን ዋናው አላማው ደግሞ መንግስት ከፈረሰ ሊከሰት የሚችለው የምስራቅ አፉሪካ የህዝብ ስደት ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል ለውጭ መንግስታት አሳይቶ መንግስት የጣለው አስችኳይ አዋጅ እና ቁጥጥር ይህንን አደጋ እንዳይመጣ እና የቀጠናውም የአለምም ችግር እንዳይሆን በመስጋት እንዲቀበሉት ለማድረግ ነው። የመንግስት ሚዲያወችም ሊከሰት የሚችለውን ስደት በተከታታይ ለህዝብ ጆሮ ማቅረብ እንዳለባቸውም ተደርጓል።”
Leaked News አፈትላኪ ዜናዎች
Filed in: Amharic