ከኣርቱ የህወሃት ልጆች ኣንዱ ኦህዴድ ነዉ፥፥ ኦህዴድ በልጅነት ዘመኑ የአሳዳጊ አባቱን ምክርና ተግሳፅ እየሰማ ያደገ ታማኝ ልጅ ነበር፥፥ ከእዉነተኛ ወላጆቹ ፍቅር ተለይቶ ያደገ ይህ ልጅ ድርጊቱ ሁሉ አሳዳጊ አባቱን ለማስደሰት ነበር፥፥ በርግጥ የአሳዳጊ አባቱን ሃሜት እየሰማ ስላደገ በወላጅ ቤተሰቦቹ ላይ ጨካኝ ነበር፥፥ ዛሬ ግን ኦህዴድ ወጣት ነዉ፥፥ ያውም የአሳዳጊ አባቱን ክፋትና ጭካኔን በአይን በብረቱ ያየ ጎሮምሳ ወጣት፥ ከአሳዳጊ አባቱ ተደብቆ ከወላጅ ቤተሰቡ ልጆች ጋር መዋል የጀመረ የ27 ዓመት ጎሮምሳ፥፥ ዛሬ ይሄንን ጎሮምሳ መዋሸትም ሆነ ማታለል ከቶ አይሞከርም፥፤ ውሎው ከናቱ ልጆች ጋር ሆኗል፥፥ የጉዲፋቻ አባቱ በወላጆቹ ላይ እያደረሳቸው የነበረዉና ያለው በደል በደንብ አድርጎ የገባዉ ወጣት ነዉ፥፥ መቼም የጉዲፋቻ ልጅ ነብስ ስያዉቅ ለምን ማለቱ ኣይቀርም፥፥ ወላጅ ቤተሰቦቹን ማጠያየቁ ኣይቀርም፥፥ ከአሁን በኋላ የዝህን ልጅ ዉሎ መቆጣጠር አይቻልም፥፥ አለመቆጣጠሩም አደጋ ኣለዉ፥፥ የኦህዴድ ወንድሞችና እህቶች ንብ ናቸው፥፥ በመንጋ ነው የሚናደፉት፥፥ ዛሬ ህወሃትን ያ የበረሃ ጀግንነቱ ከድቶታል፥፥ ጥርሱ ሁሉ ወልቆ የጃጀ አንበሳ ሆኗል፥፥ እነዝያ በሽሬ፥ በናቅፋ፥ በሽራሮ፥ በአዲዳእሮ እንደ ጥንቼል ስሽሎከለኩ የነበሩ ጉልበቶች ዛሬ ዝለዋል፥፥ ከጮማና ከመጠጥ የተነሳ የኮሌስትሮል ተጠቂ ሆኗል፥፥ የፊንፊኔን ክትፎና ፍሪምባ ለምዶ ዛሬ ደደቢትን ልያስታዉስ ከቶ አይቻለዉም፥፥ ደግሞ ህወሃት መዉለድ የማይችል መካን ነዉ፥፥ ከአሁን በኋላ ዕድሉ በጉዲፋቻ ልጆቹ እጅ ላይ ነች፥፥ ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው ክፉ ስለነበር ምን እንደሚጠብቀዉ ያዉቃል፥፥ በስተርጅና ፍርሃት ተጠናዉቶታል፥፥ በር ዘግተዉ በዉርስ ላይ ማዉራት ከጀመሩ ከራረሙ፥፥ ኦህዴድን ማዉረስ አይፈልግም፥፥ ከቀሩት ከጉዲፋቻ ልጆቹ ለአንደኛዉ ታማኝ ተናዞ እንዳይሞት እንዳልኳችሁ የኦህዴድ ቤተሰቦች:ወንድም እህቶቹ ቀላል የሚባሉ አይደሉም፥፥ ዛሬ ኦህዴድ ብቻውን አይደለም፥፥ እናም ጊዜው ለህወሃት የምጥ ጊዜ ነዉ፥፥ ዛሬ ህወሃት ጀግንነትን በስም እንጂ በተግባር ረስቶታል፥፥ ድሎትን የለመዱ አካላቶቹ ዳግም በረሃን አይዳፈሩም፥፥ እናማ በሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ከጉዲፋቻ ልጁ ጋር መተናነቅ ከተያያዙ ዉሎ አድሯል፥፥ v
ህወሃት ጀግና ነዉ፤፤ የማይካድ ሃቅ፥ (አብዲ ፊጤ)
Filed in: Amharic