>

"አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሮሞ መሆኑ ብቻ የኦሮሞን ዘርፈ ብዙ ችግር አይቀርፈውም" ዶክተር ዲማ ነገዖ

[በአቻምየለህ ታምሩ]
ዶክተር አብይ አሕመድን  «የኦሮሞ ተወላጅ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር» እያሉ  የሚያስተጋቡ  ደጋሚዎችን  ስህተት  ከሳምንታት በፊት «ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት»  በሚል ባተምነው ጽሁፍ  ስናርም መቆየታችን ይታወሳል 🙂 ከታች የታተመው ዶክተር ዲማ ባንድ ንግግር ላይ ያቀረቡት ንግግር ነው።
ዶክተር ዲማ ነገዖ ከኦቦ ሌንጮ ለታ፣ ከዶክተር ጌታቸው በጋሻውና ከሻለቃ ዳዊት ጋር   በመሆን  Gabataa Media ቀርበው  ባካሄዱት  ውይይት ላይ የተናገሩት  እውነት  ሰሞኑን አንዳንድ ግለሰቦችና የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ጭምር  ሆን ብለው በሚመስል መልኩ  እየደጋገሙ  የሚያስተጋቡትን ውሸት በድጋሚ የሚያጋልጥ ነው።  እኔም ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በዶሴ እንደሞገትሁት፤ ይኸው  ዶክተር ዲማም ስለኖሩበት ዘመን  እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በደርግም  ሆነ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኦሮሞ ተወላጆች  የሆኑ  ጠቅላይ ሚንስትሮች ነበሯት። ዶክተር ዲማ  የነበረውን እውነት እንዲህ  በመናገራቸው ሳላመሰግናቸው ማለፍ አልሻም። ከታች በታተመው የዶክተር ዲማ ንግግር ሙሉ በሙሉ የምስማማው ዶክተር አብይ የመጀመሪያው የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አለመሆናቸውን ስለተናገሩት ብቻ ሳይሆን  ባጠቃላይ ጠቅላይ  ሚንስትር መሆን ስላለበት   በተናገሩት አስተያየትም ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ።
ይቺን የዶክተር ዲማን ንግግር  ግን   ስለ ዶክተር አብይ በጻፈ ቁጥር  «Ethiopia will have its first ethnic Oromo Prime Minister» እያለ በተደጋጋሚ  ለሚጽፈው ለሎንዶኑ Awol Kassim Allo ጋብዙልኝ 🙂
Filed in: Amharic