>
5:13 pm - Monday April 19, 6348

የውጭ ጉዳይ ቃል-አቀባይ በነበሩት አቶ መለሰ አለም የተደበደበው ተከሳሽ የዛሬ የፍ/ቤት ውሎ (በፍሬው ተክሌ ረቡኒ)

* ስነስርአት አድርግ ዳኛ ተከሳሽን
* “አንተ ስነሰርአት ሲኖርህ እኔም ስርአት አደርጋለሁ ቅጠረኞች እንደሆናችሁ አውቃለሁ” – ተከሳሽ ዳኞችን
በእነ ጌታሁን በየነ የክስ መዝገብ 3ኛ ተከሳሽ ሰይፉ አለሙ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው የመከላከያ ምስክር ብይን ለመስጠት ነበር ።
ዳኞች ችሎት ሳይሰየሙ በችሎት ተላላኪ በኩል ሰይፉ አለሙ በማስጠራት በቢሮ በኩል ነው የምናየው ና ተብለሀል ሲባል ተከሳሽ ሰይፉ አለሙ “እኔ መዳኘት የምፈልገው በችሎት በኩል ነው አልመጣም” በማለት መላሽ ሰጥቷል ዳኞች ስላልተሟሉ ነው ስለዚህ ቀጠሮ ለመስጠት ነው የሚል ምክንያት ቢቀርብም “በቢሮ በኩል መቅርብ አልፈልግም” በማለት እምቢ ብሏል ።
በመቀጠልም ዳኞች ችሎት ያስቻሉ  ሲሆን መሀል ዳኛው እንዲህ በማለት ተናግረዋል “ተከሳሽ በዋናነት በቢሮ በኪል እንዲቀርቡ ያስፈለገው ዳኞች ስላልተሟሉ ነው ካልተሟሉ ደግመሞ ችሎት መሰየም አይችሉም፤ ጓዳ ሆኖ ተደብቆ የሚሰራ ነገር የለም፤ በቢሮ ተሰራ በፕላዝማ ተሰራ በችሎት ተሰራ ያው ነው” ካሉ በሆላ የምስክሮች ቃል ስላልተገለበጠ ቀጠሮ ነው የምንሰጠው በማለት ቀጠሮ ሊሰጡ ሲሉ ተከሳሽ ሰይፉ አለሙ “ለምንድን ነው ቀጠሮ የምትሰጡኝ? ከታሰርኩ ሁለት አመቴ ነው፤ እናንተ ቁጥር ብቻ ነው የምትጠሩት፤ ይህ የታወቀ ነው አባሪዎቼ ላይ የጠራችሁትን ቁጥር እኔም ላይ ጥሩ”
 ይሄን ሲል በግራ ዳኛው በኩል በተደጋጋሚ ስነስርአት አድርግ የተባለ ሲሆን ተከሳሽም “አንተ ስነስርአት ሲኖርህ እኔ ስነስርአት አደርጋለሁ፤ ቅጥረኛ እንደሆናችሁ አውቃለሁ ፍረዱ የተባላችሁትን ነው የምትፈርዱት ጓደኞቼ ላይ የጠራችሁትን ቁጥር እኔም ላይ ጥሩ” ሲል የግራ ዳኛው “አስራችሁ አውጡት” የሚል ትእዛዝ ለማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች ሰጥቶ ተከሳሽ ከችሎት እንዲወጣ ተደርጓል ።
በመቀጠልም ዳኞች በልዩነት ተከሳሽ በሌለበት ችሎት በመድፈር የስድስት ወር ፍርድ ፈርደውበታል። ተለዋጭ ሆና የቀረበቸው የቀኝ ዳኛ በቅጣቱ ላይ አልስማማም በማለት በልዩነት ወጥታለች ቀጠሮም ለግንቦት 15/2010 ዓ.ም ተሰጥቷል።
Filed in: Amharic